‹ሟች ወገኔ ገዳይም ወገኔ!› /ሙሉቀን ተስፋው/

‹ሟች ወገኔ ገዳይም ወገኔ!› /ሙሉቀን ተስፋው/

‹‹ዋናው የቅማንት ሕዝብ ታሪክ እኮ አዲግራት ላይ ነው›› አቶ ነጋ ጌጤ

ወያኔ በ1968 የወጠነውን ፕሮጀክት ቀስ በቀስ እስካሁን ያለማንም ከልካይ ሲያስፈጽም ቆይቷል፡፡ ለምን ያሉትን ሁሉ በሚችለው መጠን ገድሏል፤ አስሯል ወይም ከአገር አባሯል፡፡ ክብር ለሰማዕቶቻችን ይሁንና ይህ መሠሪ ፕሮጀክት ከዚህ በላይ መሔድ አይችልም፡፡ ለዚያም ነው የመጨረሻ የሚላቸውን ካርዶች ሁሉ የሚመዘው፡፡

እንግዲህ ይህ መሰሪ ቡድን ፕሮጀክቱን ከቀረጸበት ጊዜ አንስቶ በወልቃይት ዐማሮች ላይ የበቀል በትሩን አሀዱ ብሎ እስካሁን ድረስ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሲጨፈጭፍና ሕዝብ ሲያጸዳ ቆይቷል፡፡ ለዚህም በተለያየ ጊዜ ከዐማራው ሕዝብ አብራክ የወጡ ባንዳዎችን እንደመሣሪያ በመጠቀም ተዘርዝሮ የማያልቅ ዕልቂትና የዘር ፍጅት ፈጽሟል፡፡ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ደግሞ ባሰለጠናቸውና ተረት ተረት የመሠለ ታሪክ የነገራቸውን ጥቂት ጥቅመኞች በቅማንት ሕዝብ ስም ኮሚቴ በማቋቋም ብዙ ጥፋት አድርሶ አሁን ሌላ ጥፋት ሲደርስ በውስኪ እየተራጩ ለመደሰት በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡

በመሠረቱ የቅማንትን ቋንቋ (በመጥፋት ላይ ያለ) መታደግ ጥቅሙ ለዐማራ ሕዝብ ነው፡፡ ለዚህም የዐማራ ምሁራን ሳያሳልሱ መሥራት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሆኖም ይህን ቅዱስ ተግባር ‹‹እኩይ ግብር›› ያላቸው ሰዎች እንዲጋልቡት መንገዱን አገዛዙ አመቻቸ፡፡ በዚሁ ምክንያት ባለፉት ሁለት ዓመታት የበርካታ ወንድሞቻችን ሕይወት ጠፋ፣ ቤተሰብ ተበታተነ፤ ንብረት ወደመ፡፡ በቀሉ በዚህ ያላበቃው ይህ እኩይ ቡድን እንደ 1985ቱ ሁሉ አዲስ ደም እንዲፈስ ሌላ እቅድ ይዞ መጥቷል፡፡ እኛ ግን ከዚህ በኋላ አንሞኝም፡፡

ከዚህ ላይ መታወቅ ያለበት ጉዳይ ቢኖር የቅማንት ማኅበረሰብ ማለት የዐማራ አንድ አካል እንደሆነ ነው፤ ይህ ማንንም ለማባበል ወይም ለማሞኘት ሳይሆን ከዚህ የተለየም ዕውነታ ስለሌለ ነው፡፡ የቅማንት ‹‹ኮሚቴ›› ነን የሚሉ ሰዎችን የጥላቻ ሰነድ በመመልከት ቅማንት በዐማራ ላይ ተነሳ ማለት አላዋቂነት ነው፡፡ እንዴት ዘመድ በዘመዱ ላይ ወይም አንዱ የአካል ክፍል በሌላኛው አካል ክፍል ላይ ጥላቻን ይሰብካል? እጅ እግር አታስፈልገኝም ይለዋልን? ወይስ ዐይን ጀሮን ከዚህ ሰውነት ተለይ ሊለው ይችላል? የማይሆን ነገር ነው፡፡ ቅማንት ከዐማራ ሕዝብ አንድ አካል ነው፡፡ ይህን ዕውነታ ሁሉም ሊገነዘበው ይገባል፡፡

ኮሚቴ የሚባሉት ለጥቅምና ለሥልጣን የሚሮጡ (እኔ የማውቃቸውን ነው) በሕዝብ ደም የራሳቸውን ጥቅም በርቀት እያዩ ምራቃቸውን የሚያዥረበርቡ ምንደኞች ናቸው፡፡ የራሳቸውን ሕዝብ ክደው ከሌላው ጋር የቆሙ ናቸው፡፡ አላዋቂነታቸውን አገዛዙ ባበጀላቸው ቀዳዳ ሁሉ ሲናገሩ ይስተዋላል፡፡

ለምሳሌ ያክል ይህን እንቅስቃሴ በበላይነት የሚመራው የሕወሓት እጅ አቶ ነጋ ጌጤ ይባላል፡፡ ይህ ሰው ጌቴቹን ለማስደሰት በ19 July 2014 ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ‹‹ዋናው የቅማንት ታሪክ እኮ የነበረው አዲግራት ላይ ነው፡፡ ትግሬ ማለት በቅማንትኛ “ሰው ሳይመጣ” ማለት ነው። ከዚያ ደግሞ እንደርታ ተባለ፤ “ሰው መጣ” ማለት ነው፡፡ “አጋመ” ቅማንትኛ ነው፤ “የኛ ያልሆነ” ማለት ነው፡፡›› በማለት ከትግሬ ጋር ያለውን ቅርርብ ለማሳየት የፈጠራ ተረቱን በድፍረት ተናግሯል፡፡

የቅማንት ታሪክ አዲግራት ነው ሲል ምን ማለቱ እንደሆነ ግልጽ ነው፤ እንኳን ይህችን የዝምብ ጠንጋራ እናውቃለን እንዲሉ፡፡ ሆኖም ይህ የማይሳካ ከንቱ ምኞች ነው፡፡ ተረት አዋቂ የሆነው ይህ ግለሰብ ትግሬ፣ ኤርትራ… ወዘተ የሚሉ ስሞች ሁሉ ቅማንትኛ ናቸው ይላል (ኤርትራ ማለት በግሪክኛ ቀይ መሆኑን አንባቢ ያስተውል)፡፡ እንደ ነጋ ጌጤ ያሉ በጎንደር ዪንቨርሲቲ የሶሲዎሎጅና ሶሻል ወርክ ትምህርት ቤት መምህር የሆነው አቶ ሰማልኝ ክንዴ የፈጠራ ታሪክን በማኅበራዊ ሚዲያ ከመልቀቅ አልፈው በአዲስ ዓመት የታቀደውን ዕልቂት ለመምራት ወደ ገጠር ገብተዋል፡፡

ስለነዚህ እኩይ ቡድኖች ይህን ያክል ካል የዐማራው ሕዝብ (ቅማንትን ጨምሮ ማለቴ ነው) ልናደርጋቸው የሚገቡ ጉዳዮች አሉን፡፡ አገዛዙ እርስ በእርስ እያጫረሰ በአንድ በኩል የበቀል ጥሙን ለማርካት በሌላ በኩል ደግሞ የወልቃይትና የራያን ጉዳይ ለማፈን የዘየደው ዘዴ መሆኑን በመገንዘብ ወደተዘጋጀልን ወጥመድ ከመግባት መቆጠብ ይኖርብናል፡፡

እነዚህ እኩይ ቡድኖች ዓላማቸውን ቢያሳኩ የጥፋት ጉድጓዱን ምን ያክል አርቀው እንደቀበሩት ልናስታውለው ይገባል፡፡ ያ ማለት ከየቦታው ትራንስፖርት ተዘጋጅቶላቸው ከየቦታው ተጠራርተው የሚመጡትን የሞት መልእክተኞች መታገስ አለብን ማለት አይደለም፡፡ በየትኛውም መልኩ እነዚህን ዝም ብለን ማየት የለብንም፤ እነዚህ አካላት ከተሳካላቸው ዋናው ዓላማቸውም በሕዝብ ስቅይት መደሰት ስለሆነ ልንታገሳቸው አይገባም እላለሁ፡፡

LEAVE A REPLY