የቅማንት የማንነት እንቅስቃሴ እንዴት ሊፈጠር ቻለ? ዓላማውስ ምንድን ነው? /ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን...

የቅማንት የማንነት እንቅስቃሴ እንዴት ሊፈጠር ቻለ? ዓላማውስ ምንድን ነው? /ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው/

“””….ወያኔ እንደሚለው “ወልቃይትን ወደ ትግራይ እንዲከለል ያደረኩት ሕገመንግሥቴ ቋንቋን መሠረት ያደረገ የራስ ገዝ (የፌዴራል) የአሥተዳደር አከላለል ሥርዓትን መሠረት ያደረገ ስለሆነ ነው” ይላል፡፡ እንደ ሕጉ ይሄ የሚሆነው ታዲያ በሕዝብ ፍላጎት ፈቃድና ይሁንታ መሆኑን አስምሩልኝ፡፡ የሕዝብ ፍላጎት መሆኑ የሚረጋገጠውም በነጻ የሕዝብ ውሳኔ ድምፅ አሰጣጥ ነው፡፡ ወያኔ ወልቃይትን ሑመራን ራያንና ሌሎችን ወደ ትግራይ ሲከልል ግን የወልቃይትን የሑመራን የራያን ሕዝብ ፈቃድ ፍላጎትና ይሁንታ ጠይቆና አግኝቶ አልነበረም ወደ ትግራይ የከለላቸው፡፡ ይሄ አንዱ ውንብድናና ሕገ ወጥነቱ ነው፡፡ ሌላውና የሚገርመው ግን ከወልቃይቴዎች ሁሉም ባይሆኑም ትግርኛ ተናጋሪ የሆኑ እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ትግርኛንም የሚናገሩት ወልቃይቴዎች “ትግርኛን እንናገር እንጅ ማንነታችን ግን አማራ ነው!” እያሉ እያለ ወያኔ ወልቃይትን የትግራይ ለማድረግ የሚረዳው ታሪካዊ መረጃ እንደሌለው ጠንቅቆ ያውቃልና ትግርኛ መናገራቸውን ብቻ ምቹ ምክንያት አድርጎ መሬቱን ለመውሰድ ስለፈለገ በዚሁ ነጠላና ያልተሟላ ምክንያት ወደ ትግራይ ሊከልላቸው ቻለ፡፡

እዚህ ላይ ነው እንግዲህ ችግሩ፤ ምክንያቱም ቋንቋ በመናገር ከሆነማ የሌላ ብሔረሰብ ተወላጅ ሆኖ ግን አማርኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋው የሆነ ምናልባትም ከኢትዮጵያ ሕዝብ ከፊል የሚሆን አለና እነዚህ ዜጎችም “አማራ ናቹህ!” ይባሉና ከአማራ ሕዝብ ጋር ይቆጠሯ እንግዳው??? ወያኔ እንደሚለው ዋና መስፈርቱ ቋንቋ ከሆነ ታዲያ ቅማንቶች ቋንቋቸው አማርኛ ሆኖ እያለ እንዴት የራስ ገዝ አሥተዳደር ሊፈቀድላቸው ቻለ? ወልቃይቶች አማርኛ ተናጋሪ ቢሆኑም ትግርኛ ይናገራሉና “ትግሬ ናቸው!” ተብለው ወደ ትግራይ እንዲከለሉ ከተደረገ ምነዋ ታዲያ ቅማንቶች ቋንቋቸው አማርኛ በመሆኑ “አማራ ናቸው!” ተብለው በአማራ እንደተከለሉ እንዲቀሩ አልተደረገ???

ቅማንቶች ቋንቋቸው አሁን ላይ ቢጠፋም የራሳቸው ቋንቋ እንደነበራቸው ይነገራል፡፡ “ቅማንት ነን!” የሚሉ ወገኖች አሁን ላይ አማርኛ ተናጋሪ ቢሆኑም ሕጋቸውን በተጻረረ መልኩ አማርኛ ተናጋሪነታቸው ከአማራ ተለይተው የራሳቸውን ክልል እንዲመሠርቱ ከመደረግ አልተገቱም፡፡ እንዲህም የሚደረግ ከሆነ ታዲያ የኛ የብሔር ብሔረሰቦች ሕልውናና መብት ተቆርቋሪው ወያኔ ይልቁንም ትግራይ ውስጥ ላሉት የራሳቸው ቋንቋ ላላቸው ለኢሮብና ለኩናማ መሬታቸው በዛሬዋ ትግራይ እንዲጠቃለል ለተደረጉትም ለአፋርም፣ ለአገውም፣ ለአማራም ምነዋ ታዲያ የራስገዝ አሥተዳደር ሳትፈቀጅላቸው ቀረሽ? ነው ወይስ አደይ ትግራይ ላይ ሲሆን ይሄ መብትና ነጻነት የምትይው ነገር አይሠራም ወያኔ ሆይ??? ቁጥራቸው እንደሆነ ከፊሎቹ የክልል አሥተዳደር መብት ከሰጠሻቸው በጠባቧ የሐረር ከተማ ካሉት አንድ የኳስ (የቅሪላ) ሜዳን እንኳ ከማይሞሉት ጥቂት ቁጥር ካላቸው ሐረሪዎች ይበልጣሉ እንጅ አያንሱ!!

ወያኔ ሆይ! ወልቃይት ላይ ቋንቋን ዋነኛ መስፈርት ካደረግሽና ለሕዝቡ የ “ትግሬ አይደለንም!” ጩኸት ወይም ተቃውሞ “መስሚያ የለኝም!” ካልሽ እንዴት ሆኖ ነው ቅማንት ላይ ቋንቋን ጨርሶ ከመሥፈርት ሳታስገቢ፣ የሕዝቡ ፍላጎት በሕዝበ ውሳኔ ሳይረጋገጥ መጀመሪያ 42 ቀበሌ በኋላም ለይስሙላም እንኳ ቢሆን የክልሉ ምክር ቤት ሳይመክርበት 21 ቀበሌ ልትሰጭ የቻልሽው??? ዳሩ በወልቃይትና በሌሎቹም ወረዳዎች ነባሩን ሕዝብ ሁሉ ፈጅተሽና አሳደሽ በመጨረስ ትግሬን አምተሽ አስፍረሽበታልና እንዲያው ነገሩን አልኩ እንጅ ሕዝበ ውሳኔ ብትፈቅጅም እንኳ ሀገሬውን ተወላጁን የሚጠቅም ውጤት አይገኝም!”””

ይሄ ከዚህ በላይ ያነበባቹህት ጽሑፍ አምና “የፋሺስት ወያኔ የከፋ ወራዳ ማንነቱና የሚጠብቀው ደሞዙ!” በሚል ርእስ በጻፍኩት ጽሑፍ ላይ ያነሣሁት ሐሳብ ነበረ፡፡ ሕገ ወጡና ወንበዴው ወያኔ ግን ለኃይል ወይም ለጉልበት እንጅ ለሕግና ለአመክንዮ የበላይነት ፈጽሞ የማይገዛ የማይቀበል የአጉራዘለል የወሮበላ ቡድን በመሆኑ በጉልበቱ ሕገወጥ የሆነ ሸፍጠኛ ድርጊቱን ለመገመት በማይታሰብ መልኩ መፈጸሙን በከፍተኛ ትጋት እየገፋበት ይገኛል፡፡

በመሆኑም ዛሬ ላይ ወያኔ በቅማንት የማንነት ጥያቄ ሽፋን አስቀድሞ በሕገወጥ መንገድ ከሰጣቸው 63 ቀበሌዎች በተጨማሪ 12 ቀበሌዎችን ጨምሮ ለመስጠት የይስሙላ ሕዝበ ውሳኔ ለማድረግ ያለቀበሌያቸው የምርጫ ወረቀት ማደልን ጨምሮ ሽፍጥና ሸሩን ተያይዞታል፡፡ በዚህ የቅማንት ማንነት እንቅስቃሴ የወያኔ ፍላጎት የጎንደር መሬቶችን ወስዶ በቀጥታ ከላይ ከትግራይ ጋር ከታች ደግሞ ከቤንሻንጉል ጉምዝ ጋር ለማገናኘት በማስላት ወደጎንና ወደታች ያሉትን የጎንደር ወረዳዎችን አለፋን፣ ጣቁሳን፣ በለሳንና ሌሎች ወረዳዎችን በመተው ቅማንት ጨርሶ የሌለባቸውን ወረዳዎችንም ሳይቀር አካቶ መተማን፣ ቋራን፣ ጭልጋን፣ ላይ አርማጭሆን፣ ወገራን፣ ደንቢያን፣ ጎንደር ከተማን፣ የጎንደር ዙሪያ ወረዳን ቀበሌዎች ወስዶ የቅማንት የራስ ገዝ ክልል አድርጎ በመከለል ወያኔ በቅርብ ርቀት ለሚያያት ታላቋ ትግራይ አካል ለማድረግ በርትቶ እየሠራ ይገኛል፡፡ ወያኔ እሱ ሊገዛት የማይችላት ኢትዮጵያ እስካልመጣች ጊዜ ድረስ ግን ሁሉንም ነገር እየዘረፈ ለሚያስባት ታላቋ ትግራይ ሀብት ያከማቻል ምቹ ሁኔታዎችን እየፈጠረ ይቆያል እንጅ በምንም ተአምር ቢሆን በራሱ ጊዜ እገነጠላለሁ አይልም፡፡ እሱ ሊገዛት የማይችላት ኢትዮጵያ የመጣች ዕለት ግን ኢትዮጵያን አፈራርሶ ይቻሉም አይቻሉ አጋር ድርጅቶቸ ለሚላቸው ለሌሎቹ የጥፋት ኃይሎች ከፋፍሎ አድሎ ታላቋ ትግራይን ይዞ ለመገንጠል ነው እያሰበ ያለው፡፡ ወያኔ ይሄንን የሚያደርገው የትግራይ ሕዝብ ለሚለው ስለሚያስብና ተጠቃሚ እንደሚያደርገውም እርግጠኛ ስለሆነ እንዳይመስላቹህ፡፡ ነገር ግን በሠራቸው የሀገር ክህደት ወንጀሎች፣ በሕዝብ ላይ በፈጸማቸው የዘር ማጥፋት ወንጀሎችና አስከፊ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ከመጠየቅ እራሱን ለማዳን፣ የበቀል እርምጃን ሊወስበት የሚችልን ኃይል በመፍራት የሚያጠቃው የበረታ ኃይል እንዳይኖር ለማድረግ እና እንደ ባንዳነቱ፣ እንደ ጠላትነቱ፣ እንደ ቅጥረኛነቱ ኢትዮጵያን በማፈራረስ የኢትዮጵያን ሕዝብ ለመበቀል ካለው የደነቆረና ሰይጣናዊ አስተሳሰቡ የተነሣ እንጅ፡፡

ብዙዎቻቹህ ይህ የቅማንት የማንነት እንቅስቃሴ በሕዝቡ ተነሣሽነት የተጀመረና የተደገፈ ይመስላቹህ ይሆናል፡፡ ነገሩ ግን ፈጽሞ እንዲያ አይደለም፡፡ ወያኔ ይሄንን እንቅስቃሴ እዚህ ደረጃ ላይ ለማድረስ በሥልጣን ዘመኑ ያላደረገው ነገር አልነበረም፡፡ ሥልጣን ከያዘ ጊዜ ጀምሮ በአንድ ጎናቸው ትግሬ ሆነው ከቅማንት የተወለዱ ግለሰቦችን እያነፈነፈ እያሰሰ ከያሉበት ካሰበሰበ በኋላ ብአዴን ውስጥ ሰግስጎ በማስገባት፣ በተለይ በጎንደር ከተማ ከንቲባነትና የፍርድ ቤቶች ዳኛነት በመሾም፣ በተለያየ የሥልጣን እርከኖች ላይ በማስቀመጥ የጎንደርን ሕዝብ እንዴት አድርገው እንዲያስመርሩት እንዳደረገ ልነግራቹህ አልችልም፡፡ የጎንደር ሕዝብ በእነኝህ ዲቃሎች ክፉ ሥራና የአሥተዳደር በደል ምክንያት የግዱን በቅማንት ማኅበረሰብ ላይ መረር ያለ ጥላቻና ቂም እንዲያድርበት ሲደረግ ቆይቷል፡፡

ወያኔ እነኝህን ከጉያው አድርጎ ሲያሠለጥናቸውና ስኳር ሲያልሳቸው የቆዩትን ዲቃሎቹን በማሠማራት ነበር የቅማንት የማንነት እንቅስቃሴን የጀመረው፡፡ ይሁንና ሕዝቡ ተጋብቶ ተዋልዶ የኖረ በመሆኑ ይሄንን የማንነት እንቅስቃሴ የተባለን ነገር ፈጽሞ ሊቀበለው አልቻለም ነበረ፡፡ የሕዝቡ ምላሽ እንዲህ መሆኑ ያበሳጨው ወያኔ የቅማንት ማኅበረሰብ ይሄንን እንቅስቃሴ እንዲቀላቀል ለማድረግ ሲል አንድ ሰይጣናዊ ዘዴ ዘየደና ቡችላው ብአዴን እንዲፈጽመው አደረገ፡፡ ዘዴው ምን ነበር መሰላቹህ ብአዴን ለአማራ የተቆረቆረ በመምሰል በአማራ ስም በመዝመት በዚህ የቅማንት የማንነት እንቅስቃሴ ፈጽሞ የሌሉበትን የማኅበረሰቡ መሪዎችንና ታዋቂ ግለሰቦችን በእንቅስቃሴው አንቀሳቃሽነት እየከሰሰ የተለያየ ጥቃትና እንግልት በሰፊው እንዲፈጽምባቸው ተደረገ፡፡ በዚህም ሸፍጠኛ ሰፊ ጥቃትም የቅማንት ማኅበረሰብ ተገዶ አማራ እንደበደለው እንዲያስብ ተደረገና ማኅበረሰቡን እልህ ውስጥ ጨመረው፡፡ ብአዴን በአማራ ስም ይሄንን ግፍ በቅማንት ማኅበረሰብ ላይ በሚፈጽምበት ጊዜ በርካታ የቅማንት ተወላጆችን ገሏል፣ አስሯል፣ ደብድቧል፣ አንገላቷል ወዘተረፈ. መጨረሻም ላይ ምንም እንኳ ይሄንን የቅማንት ማንነት እንቅስቃሴን በሁሉም የቅማንት ማኅበረሰብ አባላት እንዲደገፍ ማድረግ ባይችልን አሁን ያለበት ደረጃ ላይ ሊያደርሰው ቻለ፡፡

ይሁንና ወያኔ ይሄንን የሚያደርገው ለቅማንት ማኅበረሰብ አስቦ ተቆርቁሮ ተጨንቆ፣ እሱ እንደሚያላዝነው ለብሔረሰቦችና ጎሳዎች ህልውና፣ መብት፣ ጥቅምና ነጻነት የቆመና የታመነ ስለሆነ ነው ወይ? ብለን የጠየቅን እንደሆነ በፍጹም በዚህ ምክንያት እንዳልሆነ በቀላሉ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ወያኔ ክልል አንድ ብሎ በሚጠራው በትግራይ ውስጥ ከላይ የጠቀስናቸው እስከ7 የሚደርሱ ጎሳዎችና የተለያዩ ማኅበረሰቦች አባላት አሉ፡፡ አንዳንዶቹ ቋንቋቸው ጠፍቶ ትግርኛ ተናጋሪ ሆነዋል፡፡ ቀሪዎቹም ቋንቋ ቢኖራቸውም በቋንቋቸው የመማር የመዳኘት የመስተናገድ፣ እራስን በራስ የማስተዳደር መብት ፈጽሞ እንዳያገኙ ተደርገው የተቀመጡ ናቸው፡፡

ለእነኝህ ጎሳዎችና ማኅበረሰቦች አደይ ትግራይ ማንነታቸው ላይ ከፍተኛ ጥቃት የሚፈጸምባት ወኅኒ ቤት ናት፡፡ በመሆኑም ክልሌ በሚለው ትግራይ እንዲህ ዓይነት ኢሰብአዊ ግፍ በጎሳዎችና ማኅበረሰቦች ላይ ኢሰብአዊና አንባገነናዊ ጥቃት የሚፈጽመው ወያኔ ዛሬ የቅማንት፣ ነገ ደግሞ የአገው፣ ከነገ ወዲያ የአርጎባ ወዘተረፈ. እያለ የማንነት እንቅስቃሴን የአማራ ክልል ብሎ በሚጠራው የሀገሪቱ ክፍል ውስጥ የሚቀሰቅሰው ለብሔረሰቦችና ጎሳዎች መብት በማሰብና ለማንነት ጥያቄ ታማኝ ጠበቃ ሆኖ ሳይሆን ለራሱ ግፍ የተሞላበት ሸፍጠኛ ጥቅሙ፣ አማራን ለማዳከምና በአማራ ላይ ጠላት ለመፍጠር ላለው ዕኩይ ዓላማ ሲል እያደረገው ያለ የጥፋት እንቅስቃሴ መሆኑን ማንም በቀላሉ ሊረዳው የሚችለው ሀቅ ነው፡፡

ጥያቄው ይሄንን የቅማንት ማንነት እንቅስቃሴን እየደገፉ ያሉ ወገኖቻችን ይሄንን ያውቃሉ ወይ ነው? እንቅስቃሴውን እየመሩና እያንቀሳቀሱ ያሉት ከቅማንት የተወለዱ የትግሬ ዲቃሎች በወያኔነታቸው ፀረ ኢትዮጵያና ፀረ ሕዝብ ዓላማ ያነገቡ በመሆናቸው ጉዳዩ ለሰይጣናዊ ሸር የሚደረግ መሆኑ የሚያሳስባቸው አይደሉምና ጥያቄውን እያነሣሁ ያለሁት መጠቀሚያ ለሆነው ለምስኪኑ ሕዝብ ነው፡፡

ተሳስቶ የወያኔ መጠቀሚያ በመሆን ይሄንን የማንነት እንቅስቃሴ ደግፎ እየተንቀሳቀሰ ላለው የቅማንት ማኅበረሰብ ወገናችን ላስጨብጥ የምሻቸው ቁምነገር አሉ፡፡ እነኝህን ነጥቦች እያንዳንዱ የማኅበረሰቡ ተወላጅ በአንክሮ እንዲመለከታቸው እማጸናለሁ ፦

1ኛ. በግልጽ መረዳት እንደሚቻለው ወያኔ ይሄንን በትጋት እያደረገ ያለው በእናንተ ስም መሬት ወስዶ ወደትግራይ ለመቀላቀል መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ወያኔ ነገ ይሄንን ካደረገ በኋላ የኢሮቦችን፣ የኩናማዎችንና የሌሎቹንም ማንነት አጥፍቶ በትግሬ ማንነት እንዲዋጡና እንዲጠፉ እንዳደረገ ሁሉ እናንተንም እንዲህ አድርጎ እንደሚያጠፋቹህና መሬታቹህን ወርሶ እንደሚቀር ለማወቅ በግልጽ የሚታይ ያፈጠጠ ሀቅ በመሆኑ ይሄንን ከወዲሁ ለመረዳት ነቢይነትን የሚጠይቅ ጉዳይ አይደለም፡፡ ይሄ ግፍ እንዲፈጸምባቹህ ትፈልጋላቹህ ወይ?

2ኛ. እውነትና የሚጠቅማቹህም መስሏቹህ ከወያኔ ጋር በዚህ እንቅስቃሴ ስትተባበሩ ኢትዮጵያ ምስቅልቅልና መገነጣጠል ውስጥ እንዳትገባ የጥፋት ኃይሉን እየታገለ ካለው፣ አብሯቹህ ከኖረው፣ ክፉ ደጉን አብሯቹህ <sp

LEAVE A REPLY