ሰበር ዜና-በአማራ እና ትግራይ ክልሎች ሳይፈታ የቆየው የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ በስምምነት ተፈታ...

ሰበር ዜና-በአማራ እና ትግራይ ክልሎች ሳይፈታ የቆየው የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ በስምምነት ተፈታ ተባለ

/ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦ ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ የወልቃይት፣ ጠገዴና ጠለምት ህዝብ የማንነት ጥያቄ በማንሳት ከፍተኛ ዋጋ እንደከፈለበት ይታወቃል። በሽህ የሚቆጠር ህዝብ የህይወት ዋጋ ከፍሏል። በአስር ሽዎች የሚቆጠሩት ከቀያቸው ተፈናቅለዋል።

ኮሚቴዎችን ጨምሮ በርካታ የወልቃይትና ጎንደር አካባቢ ተወላጆች አሁንም በእስር ቤቶች እየማቀቁ ይገኛሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ የአማራ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት የሁለቱ ከልሎች መካከል የነበረውን አለመግባባት “በስምምነት” ተፈቷል ብሎናል።

“በአማራ ክልል እና ትግራይ ክልል መካከል ሳይፈታ የቆየው የወሰን ጉዳይ በህዝብ ተሳትፎ እና በስምምነት በዛሬው እለት ተፈታ፡፡

በአማራ ክልል ጠገዴ እና በትግራይ ክልል ጸገዴ ወረዳ መካከል የነበረው ለረጅም ዓመታት ሳይፈታ የቆየ የወሰን ጉዳይ በዛሬው እለት በጠገዴ ወረዳ ቅራቅር ከተማ ላይ የአማራ ክልል እና የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድሮች በተገኙበት በተደረሰ ስምምነት ተፈቷል፡፡

በዚህም መሰረት ለረጅም ዓመታት ሲያወዛግቡ የነበሩት በግጨው በረሀ የሚገኙት የማይምቧ ፣ ሰላንዴ እና የአየር ማረፊያ ሰፋፊ የእርሻና ኢንቨስትመንት ቦታዎች ወደ አማራ ክልል ጠገዴ ወረዳ ተከልለዋል፡፡ እንዲሁም በግጨው እና በጎቤ የሚገኙ የትግሬኛ ተናጋሪዎች ያሉባቸው ሁለት የመኖሪያ መንደሮች አካባቢዎች ደግሞ ወደ ትግራይ ክልል ጸገዴ ወረዳ ተከልለዋል፡፡

ወደ ትግራይ ክልል ጸገዴ ወረዳ በተካለሉት ሁለት የመኖሪያ መንደሮች ዙሪያ የሚገኙ ቦታዎች በአማራ ከልል ውስጥ እንዲካለሉ ተደርጓል፡፡

በዚህም መሰረት ለረጅም ጊዜያት ሲያወዛግቡ የነበሩት ሳፋፊ የእርሻ እና የኢንቨስትመንት ቦታዎች ሙሉ በሙሉ ወደ አማራ ክልል የጠገዴ ወረደ እዲካለሉ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

ወደ አማራ ክልል በተከለሉ ቦታዎች ላይ የሚኖሩ የትግራይ ክልል ተወላጆች የሚያከናውኗቸው ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች በሙሉ በአማራ ክልል ህግ የሚተደዳዳረሩ መሆኑ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ ዝርዝር መረጃውን እናቀርባለን።”

በዜና ስዓታችን ይዘን እንቀርባለን፡፡” የአማራ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት

LEAVE A REPLY