በአዲስ አበባ ከተማ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈተና የወሰዱ መምህራን አስደጋጭ ውጤት አስመዘገቡ...

በአዲስ አበባ ከተማ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈተና የወሰዱ መምህራን አስደጋጭ ውጤት አስመዘገቡ ተባለ

/ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦ በአዲስ አበባ ከተማ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈተና የወሰዱ መምህራን አስደንጋጭ ውጤት ማሰመዝገባቸው ተነገረ። ፈተናውን ከወሰዱ 5 ሺህ 167 የመጀመሪያ ደረጃ መምህራን ውስጥ 961 መምህራን ብቻ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ መቻላቸውን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ገልጿል፡፡

ከ2005 እስከ 2008 ዓ.ም ለተከታታይ ዓመታት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈተና ከወሰዱት 18.8 በመቶ የሚሆኑት ብቻ የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸው ታውቋል። የመምህራኑ የሙያ ብቃት ማነስ የትምህርት ፖሊሲው ምን ያህል ውጤት እንዳላመጣ ማሳያ ነውም ተብሏል።ለምዘና የሚወጣው አብዛኛው ፈተናም ከሳይንሳዊ የ”መማር ማስተማር” መርህ በእጅጉ የራቀና ፖለቲካ እንደሆነ መምህራኑ ይናገራሉ።

ህወሓት/ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘ ጀምሮ በስርዓተ-ትምህርቱ ላይ የተለያዩ በደሎች ፈጽሟል።በ1942 በ32 መምህራን በዳግማዊ ሚኒሊክ ትምህርት ቤት የተቋቋመውን የኢትዮጵያ መምህራን ማህበርን ከማፍረስ ጀምሮ ከሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እስከ ዩኒቨርሲቲ ድረስ የትምህርት መስጫ ተቋማትን የአንድ ፓርቲ መፈንጫ በመሆናቸው በኢትዮጵያ የብዛቱን ያህል “ጥራት” ማምጣት አልተቻለም።

LEAVE A REPLY