በአዲስ አበባ ቆሼ በድጋሚ የሰው ህይወት አጠፋ

በአዲስ አበባ ቆሼ በድጋሚ የሰው ህይወት አጠፋ

/ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦ በተለምዶ ቆሼ እየተባለ የሚጠራው የአዲስ አበባ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቦታ በድጋሚ ተንዶ የአንድ ሰው ህይወት አጠፋ። ሐሙስ እኩለ-ቀን በአካባቢው የነበሩ ሁለት ሰዎች ላይ ተንዶ አንዱ መሞቱ ሲረጋገጥ ስለ ሁለተኛው ሰው ማወቅ እንዳልተቻለ ታውቋል። 34 ሄክታር ስፋት እንዳለው የሚነገርለት ቆሼ ከ57 ዐመታት በላይ አገልግሎት ሰጥቷል።

ባለፈው መጋቢት ወር የቆሻሻው ክምር በዙሪያው ባሉ ቤቶች ላይ ተንዶ ከ115 ሰዎች በላይ እንደሞቱና በሺህ የሚቆጠሩ ዜጎችን ቤት አልባ ማድረጉ የሚታወቅ ነው።

LEAVE A REPLY