የኢትዮጵያ ብር የመግዛት አቅም በ15 በመቶ እንዲቀንስ ተደረገ

የኢትዮጵያ ብር የመግዛት አቅም በ15 በመቶ እንዲቀንስ ተደረገ

/ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ  እንዳስታወቀው ከጥቅምት 1/ 2010 ዓ.ም. ጀምሮ የብር የመግዛት አቅም በ15 ፐርሰን እንደሚቀንስ አስታውቋል። በዚህም መሰረት አንድ ዶላር አሁን ካለበት የ23.54 ብር ምንዛሬ ላይ የ3.5 ብር ጭማሪ በማሳየት ወደ 27.04 ብር ይሆናል ተብሏል።

ኤይ ኤም ኤፍ የኢትዮጵያ መንግስት የብርን የመግዛት አቅም ማሻሻያ እንዲያደርግ በተደጋጋሚ ሀሳብ ሲያቀርብ በመቆየቱ፤ አሁን የተደረገው ማሻሻያ ምላሽ ሊሆን እንደሚችልም ተጠቁሟል። የአንድ ሀገር ገንዘብ የመግዛት አቅም የሚቀንሰው (ዲቫሎሽን) ወደ ውጭ የሚላኩ እቃዎች(ኤክስፖርት) እና ወደ ሀገር የሚገቡ የሸቀጥ እቃዎች(ኢምፖርት) አለመመጣጠን ሲኖር እንደሆነ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ያስረዳሉ። ኢትዮጵያ ወደ ውጭ የምትልካቸው በዋናነት ቡና፣ ቆዳና ሌጦ ናቸው።

በምትኩ የግብርና መሳሪያዎችን፣ የአውቶ ሞቲብ መለዋወጫዎችን፣ የግንባታ መሳሪያዎችን፣ አልባሳትንና የመሳሰሉትን እቃዎች ወደ ሀገር ታስገባለች።

እ.ኤ.አ በ2014 አንድ ጥናት እንደጠቆመው ኢትዮጵያ በየዓመቱ እስከ 4 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለእቃዎች ግዥ ወጭ ታደርጋለች። ኤክስፖርት የምታደርገው የሸቀጥ እቃ የግዥዋን ከ7 ፐርሰንት በላይ እንደማይሸፍንም ጥናቱ ያሳያል።

ማሻሻያውን ተከትሎ ሀገሪቱ ከአለም ባንክና ከተለያዩ አበዳሪ ተቋማት ያለባ ከፍተኛ <እዳ> በ15 ፐርሰንት እንደሚጨምር ታውቋል። እንዲሁም በሀገር ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ የዋጋ ግሽበትን ሊያስከትል እንደሚችልም ባለሙያዎች አስታውቀዋል።

የህወሓት የአገዛዝ ቡድን በ1983 ዓ.ም በትረ-ስልጣኑን ሲቆጣጠር አንድ የአሜሪካን ዶላር በ2 ብር ይመነዘር እንደነበረ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

LEAVE A REPLY