እናታችን አሁን ቀና በይ /ታሪኩ ድሳለኝ/

እናታችን አሁን ቀና በይ /ታሪኩ ድሳለኝ/

እርጅናዋ እጥፍ ሆኗሉ። ህመም በየለቱ ያስቃስታታል። እምነቷ ግን ጠንካራ ነው። የልጇን ጉዳይ አሳለፋ ለሰጠችው ቅዱሱ ሚካኤል “ህስ የልጄ ነገር እንዴት ነው?” ስትሰለች ትልላለች። መታመሙ ስትሰማ “እኔ ምን አቅም አለኝ ቅዱሱ ሚካኤል አንተው መዳኔት ሁነው” ትላላች። የተቋጠረችውን ሳሀን ይዘን ስንመለስ መጠየቅ እንደተከለከለን ያሰረቸው ዳንቴን አለመፈታቱን አይታ ትረዳለች አሁንም ወደ አምላኳ ቀና እያላች የሷን ህመምና ስቃይ እረስታ “አይ ቅዱሱ ሚካኤል አይ እመቢቲ ማርያም የልጄን ሳቃይ ምነው ዝም አላችሁ ምነው?” ትላለች። አሁን እዚህ የለም የት እንዳለ አናውቅም ብለውን በየእስር ቤቱ ስንዞር እናታች ከሚካኤል እስከ መዳኒዓለም ከመዳኒዓለም እስከ ተክለሀይማኖት ከተክለሀይማኖት እስከ ኪዳንምህርት ቤተክርስቲያን የልጆን ድምፅ እንዲያሰሞት ስትፀልይ ውላ ስትተኛ ታደራለች።

ይቺ ቆራቢ እናት ልጇን ጦሬዋን የግፍ እስር የነጠቃት እናት የቺ ሳትተኛ የተኛች እየመሰለች በሰመመን ልጆን እያየች የሚነጋላት እናት ይቺ ሳትበላ የበላች መስላ የልጇን ስንቅ እንዳይቋረጥ ደፋ ቀና የምትል እናት ይቺ ዓለም ሳይታያት ልጇ ዓለሟ የሆነች እናት ይቺ ከእርጅናም ከህመም በላይ የልጇ ፍቅር ያቆያት እናት ዛሬ በርትቷ ያበረታት ልጇን ልታይ ወዜማው ላይ ቆማለች። ይቺ እናት የብርታቷ መገለጫ የሆናት የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እና የኛ እናት ፋናዬ እርዳቸው ነች። ዛሬ ፆሎቷ ሊሰማ ሰለቷን ልታሰገባ ነገ ስንቅ የለብኝም ብላ ዓይኖን ከድና እስኪነጋ ልትተኛ 2 ቀን ብቻ የቀራት ወዷ እናታችን ነች።

ይህን አስራ አምስት ቀን እናታችን ቤቱን አንዴ ቀለም ስታስቀባ አንዲ የፎቴ ወንበር ጨርቅ ስትለወጥ አንዴ መጋረጃ ሰትለውጥ ስትወርድ ስትወጣ ሰንብታለች። ሠፈራችን “ፊት በር አራት ኪሎ ሥጋ ቤት ሠፈር” ከፈረሰ በኃላ ካባትና ከናታች ጋር አብረው የኖሩ ጎረቤቶቻችን ተበታትነው ግማሹ አልታድ ሠፈር ግማሹ አያት ግማሹ ካሳንችስ ግማሹ ጨርቆስ ግማሹ ገላን የተወሰኑት ደግሞ ጀሞ መኖር ከጀመሩ 5 አመት ቢያልፍቸውም ይጠያየቃሉ የደጋገፋሉ። የፊት በር አራት ኪሎ ጎረቤቶቻችን ተመስገን ከታሰረ ከተወሰነ ወራት በኃል እናታችንን ሰብሳቤ በማድረግ ተመስገንን እንዲያስፈታላቸው የቅዱስ ሚካኤልን ፅዋ መጠጣት ጀምረዋል። ይህን ፅዋ እናታችን ልጄ ሳይፈታ እኔ ቤት አይጠጣም በማለት ተራዋን እያሳለፈች እዚህ ደርሳለች። አሁን ግን የጥቅምት ሚካኤልን ፅዋ ለመጠጣት ፅዋውን ወስዳለች ለዚህም 12 ቀን ይቀራታል።
እናታቸን ከዛሬ ነገ አቀሟ ቢዳከም እርጅናዋ ቢጎትታትም እህመም ቢያስጎነብሳት “የወንድ ልጅ እና ታጠቂ በገመድ ልጅሽን አሞራ እንጂ አይቀብረውም ዘመድ” ሆኖባት ነገሩ መቀነቷን አጥብቃ በፆሎቷና በትግስቷ እዚህ ደርሳለች።

አሞት ያላስታመመችው ዐይኑን ልታይ ሄዳ የተከለችው የቋጠረችውን ምግብ ያልደረሳለት ልጇ ሊፈታ ዛሬ 2 ቀን ይቀረዋል። እናታችን የደስታ አፋፉ ላይ ደርሳለች። እናታችን መቀነቷ አላልታ ልዕለታ ሁለት ቀን ቢቀራትም ምስጋናውንም ስለቷንም እያሰበች “ቅዱስ ሚካኤል እንግዲህ እንተ ታውቃለህ” ማለቷን አላቆመችም።

እናታችን ሆይ”ልጄ የኔ ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ ልጅ ነው” ያልሽው አንቺም እንደ ኢትዮጵያ ሆነሽ እርጅናሽንም ህመምሽንም እረስተሽ ከእስር ቤት እስር ቤት ተመላልሰሽ የጠየቅሽው አንደቀንም ስታጓድዬ ስንቅ እያሰርሽ በእየስር ቤቱ የሰደድሽለት ልጅሽ በሞገስ፣በኩራትና በጀግንነት ከእስር ሊፈታልሽ 2 ቀን ነው እና የቀረው እናታችን ሆይ እባክሽን አሁን እንኳን ቀና በይና ብዙ ነገር ያለው ብዙ የሚነግረንን መክራሽንንም ደስታሽንም ፍቅርሽንም የያዘውን ፈገግታሽን አሳይን።

መስከረም 30/2010ዓም

LEAVE A REPLY