“እንቁጣጣሽ” በሚ ለው ሙዚቃዋ የምትታወቀው ድምፃዊት ዘሪቱ ጌታሁን ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች

“እንቁጣጣሽ” በሚ ለው ሙዚቃዋ የምትታወቀው ድምፃዊት ዘሪቱ ጌታሁን ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች

/ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦ ድምፃዊት ዘሪቱ ጌታሁን ባደረባት ህመም ምክንያት በለገሀር ጠቅላላ ሆስፒታል በህክምና ስትረዳ ቆይታ በዛሬው እለት ከረፋዱ ሦስት ሰዓት ላይ ህይወቷ ማለፉ ታውቋል። ድምፃዊት ዘሪቱ ጌታሁን በ1940ዎቹ አካባቢ በወሎ ክፍለ ሀገር “ኩታ በር” በተባለ አካባቢ እንደተወለደች የህይወት ታሪኳ ያስረዳል። አዲስ ዓመት በመጣ ቁጥር

“እንቁጣጣሽ እንኳን መጣሽ፤

በአበቦች መሐል እንምነሽነሽ………።” የሚለው ዘመን አይሽሬ የሙዚቃ ስራዋ ሁሌም እንደ አዲስ የሚደመጥላት ስራዋ ነው። አርቲስት ዘሪቱ ከ50 ዓመታት በላይ ለኢትዮጵያ ሙዚቃ እድገት የበኩሏን በጎ አስተዋፅዖ ያደረገች ሲሆን እንቁጣጣሽ፣ትዝታ በፖስታ፣ የጥበብ አበባ፣ እቴ ያገሬ ልጅና በሌሎች የሙዚቃ ስራዎቿ ትታወቃለች።

ለቀናት በፊትም አጋፋው አርቲስት ሀብተሚካኤል ደምሴ በደረሰበት ከባድ የመኪና አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት በሞት መለየቱ የሚታወቅ ነው።

ለአርቲስት ዘሪቱ ጌታሁን ቤተሰቦችና አድናቂዎች በሙሉ  መጽናናትን እንመኛለን።

ኢትዩጵያ ነገ ዝግጅት ክፍል /ኢነዝክ/

LEAVE A REPLY