“ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ አይፈታም” የዝዋይ እስር ቤት ሀላፊዎች

“ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ አይፈታም” የዝዋይ እስር ቤት ሀላፊዎች

/ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦ የፍትህና የልዕልና ጋዜጦች፤ የአዲስ ታይምና ፋክት መጽሄቶች ባለቤትና አዘጋጅ የነበረው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በፃፋቸው ጹሁፎች ብቻ ተከሶ የሦስት ዓመታት እስር በፍርደ ገምድልነቱ በሚታወቀው የኢትዮጵያ ፍ/ቤት ተወስኖበት ወደ እስር እንደተጣለ የሚታወቅ ሲሆን ዛሬ የሶስት አመታት የእስር ጊዜው ቢያጠናቅቅም የዝዋይ እስር ቤት ከዚህ በፊት እንደሚያደርገው ሁሉ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እንደማይፈታ ለተመስገን ወንድም ታሪኩ ደሳለኝ አሳውቀዋል።

ጋዜጠኞችን በማሰርና ሚዲያን በማፈን ከአለም ግምባር ቀደም ከሆኑት ሃገራት አንዷ ኢትዮጵያ መሆኗን የአለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ሲ.ፒ.ጀ በየ ጊዜው በሚያወጣው መግለጫ ያሳውቃል። በአሁኑ ወቅትም ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጨምሮ ከ14 በላይ ጋዜጦች በእስር ቤት እየማቀቁ ይገኛሉ።

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወንድም ታሪኩ ደሳለኝ ዛሬ በዝዋይ እስር ቤት ከተገኘ በሗላ በፌስ ቡክ ገጹ ላይ የሚከተለውን ለቋል።

“መንግስት የፈረደውን የፍርድ ቤት ሙሉ የ3 አመት እስር ያለ አመክሮ ዛሬ የጨረሰው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በእራሳቸው ፍርድ አሰጣጥ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ዛሬ መፈታት ሲኖርበት የዝዋይ እስር ቤት ሀላፊዎች ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን አልፈታም ብለዋል። ይህ ሁኔታ ቀድሞም የተመስገን እስር ፖለቲካ እንደነበር ተጨማሪ ማረጋገጫ ነው።

ትላንት ጥቅምት 2/2010ዓም ተሜን ጠይቄው ስወጣ እግረ መንገዴን እስረኛ አስተዳደር ገብቼ እስሩን ስለሚጨርስ ሰው ላናግራችሁ ነበር ስል አንዱ ሰው “ላጣራልህ” ብሎ ሲነሳ “ስሙን ልንገርህ” ስለው “አቃለሁ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ አይደል” ብሎኝ ወጣ አይ ያውቀዋል ያቁኛል ማለት ነው ብዬ አጣርቶ እስኪመጣ ጠበኩት። ይህ ሰው የስራ ሀላፊነቱን የማላውቀው ጊጡ የተባለ ሰው ነው። እንደመጣ እያየኝ ተመስገን ነገ ነው የሚፈታው አለኝ ሰምቼው ወጣሁ። ለነገሩ ባይለኝም ቢለኝም የተፈረደበትን ሙሉ 3 አመት የሚጨርሰው ነገ ጥቅምት 3 ነው አለኝ። ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ መንግስት በፍርድ ቤቱ የወሰነበትን እስር ቢጨርስም አሁን ደግሞ የእስር ቤቱን ሌላ እስር ጀምሯል። እንግዲህ የተመስገን ህይወት በተመለከተ የዝዋይ እስር ቤት አስተዳደሮች ሀለፊነቱን ይወስዳል ነው። ተመስገን ላይ የሚደርሰው ነገርስ ሁሉ ያሳስበናል።”

LEAVE A REPLY