ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ዛሬ ጠዋት ተፈታ

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ዛሬ ጠዋት ተፈታ

/ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ያለ አመክሮ የሦስት ዓመት የእስር ጊዜውን አርብ እለት ቢያጠናቅቅም የዝዋይ እስር ቤት ሀላፊዎች እንደማይፈታ ከገለጹ በሗላ ዛሬ ጠዋት ተፈቷል።

ተመስገን በመንግስት የተወሰነበትን የሶስት ዓመታት ሲጨርስ አለመፈታቱን ተከትሎ ከትናንት ቅዳሜ ጠዋት ጀምሮ የርሀብ አድማ ላይ እንደነበረ ቤተሰቦቹ ገልጸው ነበር።

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በፍትህ ጋዜጣ በፃፋቸው ሦስት ጹሁፎች “ህገ መንግስቱን በኃይል ለመናድ እና አመጽ ለማነሳሳት” የሚል ክስ ተመስርቶበት ያለፉትን ሦስት ዓመታት በግፍ እስር ቤት አሳልፏል።

የዝዋይ እስር ቤት ሀላፊዎች ህክምና በመከልከልና በጨለማ ክፍል ለብቻው በማሰር የተለያየ ግፍ እንደፈጸሙበት የሚታወቅ ሲሆን ከእስር ቤት ሲወጣም በጣም ከስቶና ጠቁሮ ታይቷል።

LEAVE A REPLY