ገጣሚ ማህሙድ እንድሪስ ለተመስገን

ገጣሚ ማህሙድ እንድሪስ ለተመስገን

ክህደት ነበር እንጂ
ውሽት ነበር እንጂ
ህሊናን አውሮ
አካልን ጠፍሮ አንገት የሚያስደፋ
መች ያስከስስ ነበር
መች ያሳስር ነበር
እውነትን ተጋፍጦ መናገር በይፋ
ተመልከት ጀግናውን
እስር እንግልቱን
ስቃይ ፈተናውን
ትዕቢት ድንፋታውን
እምነቱን ጠብቆ አልፎታል በምፀት
ከህሊና ውግዘት
ከማንነት ወድቀት
ከስብእና ንቅዘት
ታሳሪው ነጻ ነው — አሳሪው ተፀፀት ።
— — — —

ተበዳይ ተከሳሽ የቀለም እስረኛ ሲሄድ ቀና ብሎ
መከረኛ አሳሪ እግር እግሩን ሲከተል እርሳስ አቀባብሎ
ስጋት ስጋ ለብሶ ውድቀት ስኬት መስሎ
ገለባው ቢቆለል ከስንዴው ተሽሎ
ንፋስ የመጣ ለት ይቋቋማል ችሎ ?

LEAVE A REPLY