በኦሮሚያ ከተሞች ሰሞኑን እየተካሄዱ ያሉ ሰልፎች ዛሬም በስፋት ቀጥለው ዋሉ

በኦሮሚያ ከተሞች ሰሞኑን እየተካሄዱ ያሉ ሰልፎች ዛሬም በስፋት ቀጥለው ዋሉ

/ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦ በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ሰሞኑን እየተካሄዱ ያሉ ህዝባዊ ተቃውሞዎች ዛሬም በስፋት ቀጥለው ውለዋል። ከአዲስ አበባ ከተማ 90 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሰሜን ሸዋ ሙኬ ቱሪ በተባለች ከተማ ከትናንት ጀምሮ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች የተሳተፉበት ታላቅ ህዝባዊ ተቃውሞ ተደርጓል።

ባለፈው ሳምንት በመከላከያ ወታደሮች 4 ሰዎች የተገደሉባት ቡሌ ሆራ( ሀገረ-ማርያም) ዛሬ ማምሻውን የአካባቢው ህዝብ ለተቃውሞ ወደ ጎዳና መውጣቱም ታውቋል። ቁጥሩ እጅግ በርካታ የሆነ ህዝብ የተሳተፈበት ተቃውሞም በጎሬ ከተማ ተካዷል።ሰልፍ በተካሄደባቸው ሁሉም አካባቢዎች “ወያኔ ይውረድ፣የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ፣የኢትዮጵያ-ሶማሌ ክልል ልዩ ሀይል ፖሊስ በዜጎች ላይ እያደረሰ ያለውን በደል ያቁም የሚሉና ሌሎችም በርካታ ጥያቄዎች መነሳታቸውን ምንጮቻችን ጠቁመዋል።

በተለይም በኦሮሚያና አማራ ክልሎች ከሁለት ዓመታት በላያ ያለማቋረጥ እየተደረገ ያለው ህዝባዊ ትግል ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገና አቅም እያገኘ መጥቷል።ህዝባዊ ትግሉን ተከትሎ በስርዓቱ ባለስልጣናት መካከል ከፍተኛ አለመግባባት እየተፈጠረ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ሀገሪቱን ለ26 ዓመታት በበላይነት ሲገዟትና ሲመዘብሯት የኖሩት የህወሓት ባለስልጣናት የበላይነት እየተዳከመ መምጣቱንም ከዚያው ከቤተ-መንግስት የሚወጡ መረጃዎች እየጠቆሙ ነው።

LEAVE A REPLY