የአሜሪካ ኤምባሲ በቅርቡ የተደካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ የሰው ህይወት መጥፋቱ እንዳሳዘነው ገለጸ

የአሜሪካ ኤምባሲ በቅርቡ የተደካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ የሰው ህይወት መጥፋቱ እንዳሳዘነው ገለጸ

/ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦ በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ኢትዮጵያ ውስጥ በቅርቡ የተደካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ የሰው ህይወት መጥፋቱ እንዳሳዘነው ገለጸ

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ዛሬ ባወጠው መግለጫ በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች ሰሞኑን በተደረጉት ሰላማዊ ሰልፎች ላይ ግድያና ግጭት ማስከተሉ እንዳሳዘነው ገለጸ። ዩናይትድ ስቴትስ ሰላማዊ ሰልፎችን የምትመለከተው ህጋዊ የሀሳብና የፖለቲካ ተሳትፎ መግለጫ እንደሆነ ኤምባሲው ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል፡፡

በቅርቡ በተካሄዱ በርካታ ሰልፈኞች ላይ በሰላማዊ ሁኔታ ሀሳባቸውን መግለጻቸውን እና ይህን እንዲያደርጉም የጸጥታ ኃይሎች መታገሳቸውን በአድናቆት እንደሚመለከተው ኤምባሲው ገልጿል፡፡ ኢትዮጵያውያን አመለካከታቸውን በሰላማዊ መንገድ መግለጻቸውን እንዲቀጥሉም ኤምባሲው እንደሚያበረታታ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ባለስልጣናትም ዜጎች በሰላማዊ መንገድ ሀሳባቸውን እንዲገልጹ መፍቀድ እንዳለበት አሳስቧል፡፡ በአጠቃላይ የአሜሪካ መንግስት ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ገንቢ፣ ሰላማዊና ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ውይይቶችን እንዲያደርጉ ያበረታታል በማለት መግለጫው ጠቅሷል።

በሌላ በኩል የኔዘርላንድና ቤልጂየም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ዜጎቻቸው ወደ ኢትዮጵያ እንዳይጓዙ ማስጠቀቂያ አውጥተዋል።በመላ ሀገሪቱ ህዝባዊ ተቃውሞዎች እየተካሄዱ መሆኑን ጠቅሰው በተለይ በቅርቡ በተከሰተው የሶማሌና ኦሮሚያ ክልሎች ዜጎቻቸው ጉዞ እንዳያደርጉ አስጠቅቀዋል። ከዚህ ቀደምም አሜሪካ፣ ብሪቲሽና ካናዳ ዜጎቻቸው ወደ ኢትዮጵያ ሲጓዙ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሲያሳስቡ መቆየታቸው ይታወሳል።

LEAVE A REPLY