ህዝባዊ አመፆችን ተከትሎ ገንዘብ ማሸሽ ተጀምሯል፤ 1.6 ሚሉዮን ዶላር በላይ ተያዘ

ህዝባዊ አመፆችን ተከትሎ ገንዘብ ማሸሽ ተጀምሯል፤ 1.6 ሚሉዮን ዶላር በላይ ተያዘ

/ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦ በኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጠረውን ህዝባዊ አመፆች ተከትሎ የሀገሪቱ ገንዘብ በህገ-ወጥ መንገድ መውጣቱን ቀጥሏልየምንዛሪ መጠኑ ወደ 45 ሚሊየን ብር በላይ የሆነ የአሜሪካ ዶላር ወደ ውጭ ሊወጣ ሲል መያዙን የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

ትናንት ጥቅምት 8 /2010 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ተነስቶ በሀረር ባቢሌ መግቢያ ቶጎ ጫሌ ኬላ አካባቢ ድምሩ 1656264 የአሜሪካ ዶላር ወደ ውጭ ሊወጣ ሲል ተይዟል፡፡ዶላሩ ከሐረር ከተማ በሚኒባስ ሲጓጓዝ የነበረ ሲሆን፥ ከሃረር እስከ ቶጎ ጫሌ ድረስ በተለምዶ “ኮስትር”ተብሎ በሚጠራው ተሽከርካሪ ከተጓጓዘ በኋላ በህብረተሰቡ ጥቆማ ቶጎ ጫሌ ኬላ ላይ ተይዟል፡፡

ከዶላሩ በተጨማሪም 580.509 የሳዑዲ ሪያል፣32. 750 የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬትስ ገንዘብ፣ 1.851 የኳታር ገንዘብ ከተጠርጣሪዎቹ ጋር መያዙ ታውቋል። ባለፈው ነሐሴ ወር አዋሽ ሰባት አካባቢ ባለ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ከ551 ሺህ በላይ ዶላር ይዘው የተገኙ ሁለት ግለሰቦች ላይ የምዕራብ ሐረርጌ ዞን በእያንዳንዳቸው የስምንት ዓመታት ጽኑ እስራት እንደበየነባቸው ትናንት ዘግበናል።

በዚህ መሰል ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር በርካታ የሀገሪቱ አንጡራ ሀብት እንደተዘረፈ ይገመታል።የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ባለፍት አስር ዓመታት ብቻ ከ30 ቢሊዮን ዶላር በላይ ዘርፈው ከሀገር እንዳወጡት የተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት አጋልጠዋል።

LEAVE A REPLY