በአምቦ ከተማ የአጋዚ ወታደሮች ህዝቡን እየጨፈጨፉ ነው

በአምቦ ከተማ የአጋዚ ወታደሮች ህዝቡን እየጨፈጨፉ ነው

/ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦  ከሁለት ቀን በፊት ህገ-ወጥ ስኳር የጫኑ ሰባት ተሽከርካሪዎች በአምቦ ከተማ አቋርጠው ለማለፍ ሲሞክሩ በቄሮዎችና ፖሊሶች ተይዘው በከተማዋ ወደሚገኘው ጅንአድ ቅጥር ግቢ ውስጥ እንዲቆሙ መደረጋቸውንና ከትናንት ጀምሮ በአምቦና ጉደር ከተሞች ህዝቡ መንገዶችን ዘግቷል።

የታገቱትን መኪኖችና የተዘጉ መንገዶችን ለማስከፈት ዛሬ ጥዋት ወደ አምቦ ያቀናዉ የአጋዚ ወታደር ተኩስ በመክፈት ከ10 በላይ ሰዎችን መግደሉንና ከ20 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በጠና መቁሰላቸውን የአምቦ ከተማ የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጋዲሳ ደሳለኝ ለዶይቼ ቬለ ገልጸዋል።

ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት አምቦ ከተማ የጦር አውድማ ሆናለች። የአምቦ ዩኒቨርሲቱ ተማሪዎች ሌሊቱን መንገድ ዘግተው ያደሩ ሲሆን አራት ተማሪዎችም በአጋዚ ወታደሮች በጥይት ተደብድበው መገደላቸውን ተዘግቧል።

በኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ህዝባዊ እንቅስቃሴዎች አምቦ ከተማ ላለፉት ሦስት ዓመታት ያለሟቋረጥ ከፍተኛ ትንቅንቅ እያደረገች እንደምትገኝ ይታወቃል።

LEAVE A REPLY