የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጥቅምት 30 ሊያደርግ የነበረውም ምርጫ በፊፋ ታገደ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጥቅምት 30 ሊያደርግ የነበረውም ምርጫ በፊፋ ታገደ

/ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጥቅምት 30/2010ዓ.ም ሊያደርግ የነበረው ምርጫ በፊፋ መታገዱን ሪፖርተር የእግሊዝኛው ክፍል ዛሬ ዘገበ። ምርጫው የታገደውም የፊፋን የ”ምርጫ መስፈርቶችን” ያማሏ ባለመሆኑ እንደሆነ ተጠቅሷል።

አሁን ባለው የፌዴሬሽኑ አሰራር ለምርጫ የቀረቡ ተወዳዳሪዎች ያቀረቡት ማመልከቻን የሚመረምረው የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ሲሆን ከመረመረ በኋላ ለምርጫ ኮሚቴው ያቀርባል፡፡ ኮሚቴው የሚቋቋመው ደግሞ የሚሰየመው በጠቅላላ ጉባኤው ወቅት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ከፊፋ የአስተዳደር መርህ ጋር የሚጣረስ በመሆኑ አሰራሩ መሻሻል ይኖርበታል ሲል ፊፋ አሳስቧል፡፡

በዚህም ጥቅምት 30 የሚደረገው ምርጫ በፊፋ ድጋፍ የምርጫ ኮሚቴ እና አስፈላጊ የምርጫ መስፈርቶች ተሟልተው ለፊፋ እስኪቀርቡ ድረስ እንዲራዘም በጥብቅ ማሳሰቡን በፊፋ ዋና ጸኃፊ ፋትማ ሳሞራ የተጻፈው ደብዳቤ ያመለክታል፡፡ለጥቅምት 30/2010ዓ.ም ሊካሄድ በነበረው ምርጫ አምስት ተወዳዳሪዎች የቀረቡ ሱሆን ተካ አስፋው፣አሸብር ወ/ጊዮርጊስ፣አንተነህ ፈለቀና ዳግም ሀግኖክ ነበሩ።

LEAVE A REPLY