ኢትዮጵያ ወስጥ የሚካሄደውን ህዝባዊ አቢተኝነት ግብጽና ኤርትራ ይደግፉታል ሲል ወያኔ ከሰሰ

ኢትዮጵያ ወስጥ የሚካሄደውን ህዝባዊ አቢተኝነት ግብጽና ኤርትራ ይደግፉታል ሲል ወያኔ ከሰሰ

/ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦ እራሱን “የብሄራዊ ደህንነት” ም/ቤት ብሎ የሚጠራው ተቋም አርብ እለት የመከረበት ሰነድ ይፋ ሆኗል። የጨቋኙን ስርዓተ-መንግስት እድሜ ለማራዘም ደፋ ቀና እያለ የሚገኘው “የደህንነት” መስሪያ ቤት ባለፈው አርብ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ የክልል አስተዳዳሪዎች፣ የፌዴራልና የክልል የጸጥታ አካላት እንዲሁም የወያኔ መከላከያ ሰራዊት ሀላፊዎች የካተቱበት የሀገሪቱን “ወቅታዊ ሁኔታ” በተመለከተ በማለት ወይይት መደረጉን አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠታቸው የሚታወስ ሲሆን ውይይት የተደረገበትን ሰነድ አዲስ ስታንዳር ዛሬ ይፋ አድርጎታል።

ሰነዱ 26 ገፆች ያሉት ሲሆን “ወቅታዊ የሀገራችንን ሁኔታ ትንታኔ መሰረት ያደረገ የጸጥታ እቅድ” የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል። “የሀገራችን ሰላምና መረጋጋት አደጋዎች በአግባቡ በመተንተንና የትኩርት አቅጣጫዎችን በመለየት በመግስት የተነደፈውን ሀገራዊ እቅድ እንዲሳካ እየታዩ ያሉትን ከፍተኛ የማስፈጸም ድክመቶችና የጸጥታ ችግሮች ማስተካከል የግድ” እንደሆነ የሰነዱ ፍሬ ነገር መሆኑን መረዳት ይቻላል።

ይኸው ምክር ቤት ተወያየበትና ለሚቀጥለው አንድ ዓመት ተግባራዊ ይደረጋል የተባለው ሰነድ የኢትዮጵያ ህዝብ እያደረገ ያለውን የፍትህ፣ የነፃነትና የእኩልነት ትግልን በግብጽና በኤርትራ መንግስታት አዝማችነትና ድጋፍ እንዳለው ይከሰሳል። ከተጠቀሱ በርካታ የሰነዱ ግቦች መካከል አንዱ “ህግ-ወጥ” የሚሉትን ሰልፍ በሀይል ማስቆም እንደሆነ ተሰምሮበታል።

LEAVE A REPLY