የጁምኣው አርበኛ! !!! መንግስቱ ዘገዬ

የጁምኣው አርበኛ! !!! መንግስቱ ዘገዬ

እንዴት ነህ አህመዲን፤
ገሞራው ከታቢ ። የጁምኣው አርበኛ ፤
አውቀዋለሁ እኔ ፤
አልሃምዱ ሚለውን ፤ ያንተን አማርኛ ፤
ዱኣማ ይዘናል፤ አላረፍንም እኛ ።

እንዴት ነህ ፈራኡል፤ የአህመዲን አሳሪ ፤
እንጃልህ ዘንድሮ ፤
እንደቆላ ሽፍታ ፤ አጥተሃል መካሪ ።

ከቁስል ላይ ቁስል ፤ ሃጃ ላያወጣ ፤
እንዴት የጦቢያ ልጅ ፤
ያውም የጀበል ልጅ ፤ በቁስል ይቀጣ? ???

ተራራው ቢከመር ፤
ገደሉ ቢከመር ፤ ያው ላንድ ሰሞን ነው ፤
አትጠራጠሩኝ ፤
ባህሩን ሰንጥቆ ፤
በመሃል የሚሄድ፤ ነቢዩ ሙሳ ነው! !!!!
ይኸው ነው!!!!!
ወላሂ ይኸው ነው! !!!!!

LEAVE A REPLY