የኢትዮጵያ የዘር ፖለቲካ /ቢኒያም አባተ/

የኢትዮጵያ የዘር ፖለቲካ /ቢኒያም አባተ/

የኢትዮጵያ መንግስት እያራመደ ባለው የዘርና ፖለቲካ የተነሳ በኢትዮጵያ ታሪክ ከመቸውም ጊዜ በላቀ እና ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የወያኔ መንግስት አሁን የኢትዮጵያን ህዝብ በሁሉም የኢትዮጵያ ክልልና አካባቢ ሕዝቡ ኢትዮጵያዊነቱን እንዳያይ በዘር ከፋፍሎታል፡:

ስርዓቱ ኢትዮጵያን የመሰነጣጠቅ ሴራው አሁን ላይ ስር እየሰደደ መጥቶ በኦህዴድ፣ ብአዴንና ደህዴድን የመሳሰሉ የወያኔ ተላላኪዎች ተጨምረውበት በእነዚህ የኢትዮጵያን ሕዝብ ደም መጣጭ ድርጅቶች በኩል እየተተገበረ ያለውን ኢትዮጵያን የመሰነጣጠቅ ለራሳቸውየሚጠቅማቸውን ለህዝባችን እና ሃገራችን ግን ብሄርተኝነትን ተክለውብን ምኞታቸውን እያሳኩ ይገኛሉ፡:

ይህ የወያኔ የዘረኝነት ፖለቲካ መዘዝ ስር እየሰደደ በጣም በአሳሳቢ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እጅግ አስከፊና አሳዛኝ የሆኑ የተለያዩ ችግሮች እየወለደ፤ ጸብና ግጭቶችን እያበራከተ የዜጎችን ሕይወት በቀላሉ እየቀጠፈና የሕዝቦችን ሀብት በማውደም፣ቤቶችን በማቃጠል መጥፎ ክስተት እየተከሰተ ይገኛል።

በምሳሌነት ለመጥቀስ የሕወሃት/ኢህአዴግ መስራቾች እና ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ቀንደኛ ደጋፊዎች ሁሉም ነገር የሚመለከቱት በብሄር መነጽር ነው፡፡ ፖለቲካ ድጋፍ እና ተቃውሟቸው በብሄር ነው፡፡ ስራ እና አሰራራቸው በብሄር የተመሰረተ ነው፡፡ ከራሳቸው አልፈው የሁሉም ሰው ስራና አሰራር በብሄር ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ይፈልጋሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ላለፈው ሩብ ክፍለ ዘመን እንደተመለከትነው በተለይ በሀገሪቱ አብላጫ ድምጽ ባላቸው የአማራ እና የኦሮሞ ሕዝቦች መካከል የነበረውን ታሪክ ልዪነትና ቁርሾ በመቆስቆስ ቂምና ጥላቻ ለማስፋፋት ጥረት አድርገዋል፡፡

ለዚህም አማራውን ዝም ካልነው አያስቀምጠንም” የሚለው የመለስ መፈክር በቂ ምስክር ሲሆን ይህንን የሚያረጋግጡም በርካታ የምስልና የድምፅ ቅጅዎች በተለያዩ ነፃነት ናፋቂ የየትኛውም ብሄር ታጋዮች እጅ ይገኛል፡፡ ከዚህ በፊት ኢትዮጵያን ሲመሩ የነበሩት መሪዎች ሁሉ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር በማስከበረ ሕዝቡም አንድነቱን ጠብቆ እንዲኖር ብዙ መስዋትነትን ከፍለዋል፡፡

ሕወሃት/ኢህአዴግ አሁን የያዘው ስትራቴጂ የከፋፈለውን ህዝብ የበለጠ በመከፋፈልና የመለያያ ታሪኮችን እንደመልካም አስተማሪ ታሪክ በመምዘዝ እና አደባባይ በማውጣት አንዱን ከአንዱ በማፋጀት እራሱ መሄዱን ሳይጀምር ሌሎች በየአቅጣጫው እንዲሄዱ በማድረግ የተዳከመች ኢትዮጵያ የተፈረካከሰች ኢትዮጵያ ማየት ነው፡፡

አንድ ልናውቀው የሚገባ እውነት ይህች ሃገር በፍጹም ልትበታተንና ልትጠፋ አትችልም:: አብዛኞቹ የሕወሃት/ኢህአዴግ አመራሮችና ደጋፊዎች የአማራ እና የኦሮሞ ህዝብ ትብብርና አንድነት ሲመለከቱ ቁጭት እና ቅዥት የሚዳረጉበት መሰረታዊ ምክንያት የዚህ አፓርታይድ ስርዓት ተጠቃሚ ስለሆኑ ነው፡፡ በአጠቃላይ የአማራና ኦሮሞ ትብብር ሕወሃቶችን ለቁጭት እና ለቅዥት የሚዳርገው ፖለቲካዎ ስርዓቱ አፓርታይድ ስለሆነ ነው፡፡ ህዝቡም የወያኔ የዘር ፖለቲካ ማስፈጸሚያ እንዳይሆን ሊጠነቀቅ ይገባል፡፡

LEAVE A REPLY