መንግስት ተጨማሪ 70 ሺህ ቶን ስንዴ ለመግዛት ዓለማቀፍ ጨረታ አወጣ

መንግስት ተጨማሪ 70 ሺህ ቶን ስንዴ ለመግዛት ዓለማቀፍ ጨረታ አወጣ

 /ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦ የኢትዮጵያ መንግስት ተጨማሪ 70ሺህ ቶን ስንዴ ለመግዛት አለማቀፍ ጨረታ ማውጣቱ የተገለጸ።

አዲስ አድማስ እንደዘገበው ከጥቂት ቀናት በፊትም 400 ሺህ ቶን ስንዴ በዓለማቀፍ ጨረታ መገዛቱ ታውቋል፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ የወጣው ጫራታ ከዚህ ቀደም የተገዘው ስንዴ በቂ ባለመሆኑ እንደሆነ ተገልልጿል፡፡ የዓለም ባንክ የመረጃ ምንጮች እንደጠቆሙት የዘንድሮ የስንዴ ግዥ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ሲሆን ለግዥው የሚውለው ገንዘብም ከአለም ባንክና ከሌሎች ተቋማት በእርዳታ የተገኘ ነው ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያ በየዓመቱ ከግማሽ ሚሊዮን ቶን በላይ ስንዴ በአለም አቀፍ ገበያ ግዥ እንደምትፈፅም የተገለጸ ሲሆን ይህም ሀገሪቱ እስካሁን በሀገር ውስጥ ምርት የህዝቧን የመቀለብ ፍጆታ መሸፈን እንደተሳናት ያመለክታል ተብሏል፡፡ በግዥ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባው ስንዴ፤ የሀገር ውስጥ ምርት ጉድለትን ለመሸፈን እንደሚውል ይታወቃል፡፡

በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ከ8.9 ሚሊዮን ህዝብ በላይ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልገው እንደሆነ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የእርዳታ አስተባባሪ ቢሮ (ኦቻ) በተደጋጋሚ ሲገልጽ መቆየቱ የሚታወቅ ነው። በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ሶማሌ፣ አፋርና ደቡብ ክልሎች የተከሰተው ይኸው ርሀብ በሚሊዬን የሚቆጠሩ ወገኖችን እያጠቃ ሲሆን በሀገሪቱ ውስጥ በተከሰተው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ምክንያት ለድርቅ ተጎጂዎች እየተደረገ ያለው ድጋፍ አነስተኛ እንደሆነ በተለያየ ጊዜ ተገልጿል።

በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ ሰዎችን ብቻ ሳይሆን በርካታ እንስሳትም እያለቁ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ከኢትዮጵያ በተጨማሪም በኬንያ፣ ደቡብ ሱዳንና ሶማሊያ ተመሳሳይ ድርቅ በመከሰቱ የሰዎች ህይወት በርሀብ እያለፈ መሆኑ ይታወቃል፡፡

LEAVE A REPLY