ሳውዲ አረቢያ ኢትዮጵያዊያንን በግዳጅ እያስወጣች ነው

ሳውዲ አረቢያ ኢትዮጵያዊያንን በግዳጅ እያስወጣች ነው

/ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦ የሳዑዲ አረብያ መንግሥት ያለ ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ በሀገሪቱ የሚገኙ የውጭ ሀገር ዜጎችን በግዳጅ ወደየ ሀገራቸው መመለስ መጀመሩ ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ትናንት እንዳስታወቀው ሳውዲ አረቢያ ባለፉት ትንሽ ቀናት ብቻ ከአንድ ሺህ ሦስት መቶ(1300) በላይ ኢትዮጵያዊያንን በግዳጅ ወደ ሀገር ቤት እንደመለሰች አስታውቋል።

ሳወዲ አረቢያም ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ሳይኖራቸው በሀገሯ የሚኖሩ የውጭ ሀገር ዜጎችን በሚቀጥሉት ሦስት ወራት ውስጥ ሙሉ በሙሉ አስወጥታ እንደምትጨርስ መግለጿን የሀገሪቱ የሚዲያ ተቋማት እየዘገቡ ነው።

ሙሉጌታ ተሾመ ለ17 ዓመታት በሳውዲ አረቢያ እንደኖረ ገልጾ “ከዚህ በፊትም ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውን የውጭ ሀገር ዜጎች በሀይል የማስወጣት ልምድ ሳውዲ አረቢያ ቢኖራትም እንደ ዘንድሮ እጅግ የከፋ እርምጃ አይቶ እንደማያውቅ ለኢትዮጵያ ነገ ገልጿል።  ቀንና ሌሊት ፍተሻው ተጠናክሮ መቀጠሉንና ህጋዊ የመኖርያ ፈቃድ ይዘውም ከእግልት እንዳላዳናቸው በሳውዲ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ገልጸዋል።

የሳውዲ መንግሥት በሀገሪቱ ህጋዊ የመኖርያ ፈቃድ የሌላቸዉ የዉጭ ዜጎች በ90 ቀን ዉስጥ ወደየሀገራቸዉ እንዲመለሱ የሚደነግግ የምህረት አዋጅ ባለፈው መጋቢት ወር ካወጣ በሗላ፤ አዋጁን ከሁለት ጊዜ በላይ ተራዝሞ ተጠናቋል።የምህረት አዋጁን ተከትሎ 70 ሺህ ኢትዮጵያዊያን በፈቃደኝነት ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው የተገለጸ ሲሆን አሁንም ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ያለ ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ በሳውዲ እንደሚገኙ ሂዩማን ራይትስ ዎች ባለፈው መስከረም ወር መግለጹ ይታወቃል።

LEAVE A REPLY