ጀርመናዊ ቱሪስት ኢትዮጵያ ውስጥ ተገደለ

ጀርመናዊ ቱሪስት ኢትዮጵያ ውስጥ ተገደለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፦ በአፋር ክልል አፍዴራ አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች በተሰነዘረ ጥቃት የአንድ ሰው ህይወት አለፈ።

የበርካታ ቱሪስቶች መዳረሻ በሆነው ኤርታሌ አካባቢ ትናንት ማምሻውን በተፈጸመ ጥቃት አንድ ጀርመናዊ ሲገደል፤ አብሮ የነበረ አንድ ኢትዮጵያዊም በጽኑ መቁሰሉ ታውቋል። ቱሪስቱ የተገደለው ከሌሎች ጓደኞቹ በመለየት ፎቶ ግራፍ በማንሳት ላይ እያለ እንደሆነም ታውቋል። የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዛሬ ባወጣው መግለጫ አንድ ዜጋቸው በሰሜን ኢትዮጵያ ውስጥ መገደሉን ማረጋገጡንና ሁኔታውን ትኩረት ሰጥቶ እየተከታተለው እንደሆነ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግስት ዜግነቱ ገና ያልተለየ አንድ ቱሪስት መገደሉን አምኖ የግድያውን ሁኔታ እያጣራና ገዳዮቹን ለመያዝ እየሰራ መሆኑን ABC NEWS ዘግቧል። ኤርታሌ በኤርትራ አዋሳኝ አካባቢ የሚገኝ በመሆኑ ከዚህ በፊትም በተለያየ ጊዜ በርካታ የውጭ ሀገር ዜጎች መገደላቸው የሚታወቅ ነው።

LEAVE A REPLY