የአማራና ኦሮሚያ ክልል ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዛሬም አመጽ ላይ ናቸው፤ የሰው ህይወትም ጠፍቷል

የአማራና ኦሮሚያ ክልል ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዛሬም አመጽ ላይ ናቸው፤ የሰው ህይወትም ጠፍቷል

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና፦/ ሰሞኑን የአማራና ኦሮሞ ተማሪዎች በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ መገደላቸውን ተከትሎ ትናንት የተጀመረው የአማራና ኦሮሚያ ክልል ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተቃውሞ ዛሬም እንደቀጠ ነው።በጎንደር፣ወልዲያ፣ባህር ዳር(ዘንዘልማ ካምፓስ)፣ወለጋ(ሻምቡ ካምፓስ)፣አምቦ፣ወሊሶና ኦዳ ቡልቱ ዩኒቨርሲቲዎች ከፍተኛ ተቃውሞ እየተካሄደ ነው።በጎንደር፣ባሕር ዳርና ወልዲያ ዩንቨርሲቲዎች የአጋዚ ወታደሮች የተማሪዎችን ዶርም ሰብረው በመግባት በአሰቃቂ ሁኔታ እየደበደባቸው እንደሚገኝ ታውቋል።

ትናንት ሌሊትም በወለጋ ዩኒቨርሲቲ (ሻምቡ ካምፓስ) ሁለት ተማሪዎች መገደላቸውን የኦሮሚያ መንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።በግጭቱ የተሳተፉና የሰው ህይወት በማጥፋት የተጠረጠሩ በርካታ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ጨምሮ አስታውቋል።

ለሊቱን በአክሱም ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረው ግጭት በርካታ ተማሪዎች ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል መግባታቸውም ታውቋል።ግጭቱ የተነሳበት አዲግራት ዩኒቨርሲቲ አምስተኛ ቀኑን የያዜ ሲሆን ዛሬም መረጋጋት አይታይበትም ተብሏል።በመቀሌ ዩኒቨርሲቲም ውጥረት መንገሱን መረጃዎች ያሳያሉ።

LEAVE A REPLY