የደርግ ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩት አቶ እሸቱ አለሙ የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደባቸው

የደርግ ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩት አቶ እሸቱ አለሙ የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደባቸው

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፦ በቀድሞው የጎጃም ክፍለ ሀገር የደርግ ተወካይ የነበሩት መቶ አለቃ እሸቴ አለሙ በርካታ ወጣቶችን ከህግ ውጭ ለሞት፣ ለእሥራትና ስቃይ ዳርገዋል በሚል ዘ-ሔግ ኔዘርላንድ የሚገኝ አንድ ፍርድ ቤት የእድሜ ልክ እስራት ፈረደባቸው።

የ63 ዓመቱ አዛውንት አቶ እሸቱ አለሙ በ1970ዎቹ አካባቢ ቀይ ጭብር በማለት 75 ሰዎችን በመግደል እንዲሁም ከ220 በላይ የሚሆኑትን ደግሞ ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጭ አስረው ማሰቃየታቸውን የዘ-ሔጉ ፍርድ ቤት በምስክሮችና በሰነድ ማስረጃ አረጋግጦ የእድሜ ልክ እስራት መበየኑን ሮይተርስ ዘግቧል።

የፍርድ ቤቱ ውሳኔ በተለይ በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ ህዝብ በገፍ እየገደሉ፣እያሰሩና እያሰደዱ ለሚገኙት ለህወሓት/ኢህአዴግ ባለስልጣናት በቂ ትምህርት ሊወስዱበት እንደሚገባ በርካታ አስተያየቶች እየተሰጡ ነው።

LEAVE A REPLY