ካሽ ውበቱ እና ገብረሃና /ድሜጥሮስ ብርቁ/

ካሽ ውበቱ እና ገብረሃና /ድሜጥሮስ ብርቁ/

ይሄን ነገር ከዚህ በፊት ያነሳሁት መሰለኝ ።

ካሽ ውበቱ እና ገብረሃና እኛ ሰፈር የነበሩ ጎረቤታሞች ነበሩ። ማታ ቀማምሰው ሲገቡ እስካሁን ድረስ ምን እንደሆነ ባላጣራሁት ጉዳይ በዱላ ድብድብ ገጥመው ኖሮ ጧት ላይ ገብረ ሃና ሞተው ይገኛሉ።

ውበቱ እንደ ጂራፍ ከለቀስተኛው ጋር “ወንድሜ ወንድሜ” እያለ ትንሽ ያለቅስና ከሰው መሃል ምንጥቅ ብሎ ወደ ጫካ ይነካዋል።

ወያኔም ራሱ ስንት እና ስንት ሺ ንጹሃን ገድሎ በሰሞኗ ሁኔታ (ውጤቱ ማለት ነው!) እየየውን ይዞታል። ባለፈው ሃያ ዓመት የትግራይን የበላይነት ጭራሽ እዮልኝ ይል የነበረ ቡድን አሁን ከረፈደ በኋላ የትግራይ የበላይነት የለም፤ በትግሬነት ተጠቃሁ ማለት ይዟል። የእምነት ተቋማት እንኳን አልቀሩም የትግራይን የበላይነት ማራመጃ መሳሪያ ለማድረግ ሲሞከር።

ስልጣን ከያዙ ከሃያ ሰባት ዓመታት በኋላ በትግራይ እና በህወሃት ስም የነገዱ አሉ የሚለውም ነጠላ ዜማ ትርጉም የለውም። ሁሉም ነገር ግብ ኖሮት በዕቅድ የተሰራ ጉዳይ ነው። ለምሳሌ ከ40 የሚበልጡ ትግራዮች ተሰባስበው ጋምቤላ ላይ የኢንቨስትመንት መሬት ሲሰጣቸው፤ ኢንቬስትመንቱን የሚያካሂዱበት በሚልዮን የሚቆጠር ብድር ከባንክ ሲመቻችላቸው ፤ የጋምቤላውን መሬቱን እንደያዙ በተበደሩት ገንዘብ አዲስ አበባ ላይ ሌላ መሬት ይዘው ህንጻ ሲስሩበት አጋጣሚ ሊሆን አይችልም። ስንት ተቋማት ናቸው በዚህ ሂደት የተሳተፉት? ስንት የመንግስት አካላት ናቸው የተሳተፉት?ከዚህ በመነሳት ሌላ ያልወጣ የማናውቀውን መገመት ከባድ አይደለም።

ወደ መፍትሄው ስንሄድ የትግራይ ህዝብ ከህወሃት በፊት በሰላም ከኢትዮጵያ ጋር ለዘመናት ኖሯል። ከምንም በላይ ትግራይን የሚጠቅመው ከኢትዮጵያውያን ጋር ተስማምቶ በሰላም እና በጻነት ሳይሸማቀቅ መኖር ነው። ከዚህ ውጭ ያለው አማራጭ ሁሉ ረዥም ርቀት አያስኬድም። ምንም እንኳን ህወሓት ብዙ ነገር ቢመርዝም አሁንም የትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያውያን ጋር በሰላም የመኖር አቅም እንዳለው መዘንጋት የለበትም።

በሰላም ለመኖር ደሞ ፍትሃዊነትን መላበስ ፤ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ ግፍ እና በደል ሲደርስ እንደዜጋ መቃወም ከሚያስፈልጉት ነገሮች ጥቂቶቹ ናቸው። እስከዛሬ ስንት ሺህ ሰላማዊ ዜጋ በህወሃት ጥይት ሲጠበስ ዝም ተብሎ አሁን ከትግራይ ሰው መሞት ሲጀመር ተጠላን ተጠቃን እና የብቀላ ርምጃ መውስድ ነገሩን ያባብሰዋል።

የኢትዮጵያ ህዝብ እይጠየቀ ያለው ፍትህ ነው። ይሄንን በበጎ ህሊና ማየት ያስፈልጋል። ጊዜ ሰጠኝ ተብሎ በሰላም ሰርታችሁ ተዋልዳችሁ ትኖሩበት የበረውን መሬት የኔ ነው ብላችሁ ውሰዱ ስትባሉ ሃይማኖት እና ኅሊና ያለው ሰው እንዴት አድርጎ ተቀብሎ አዎ የኛ ነው ይላል? ወልቃይት አሁን ባለው ሁኔታ ሰላም የሚሰጣችሁ ነገር አይደለም። ጥያቄው ካልተፈታ ነገም ሰላም አታገኙም ፤ የጊዜ ጉዳይ ነው።

ከህወሃት ጋር ሲሰሩም የነበሩት ድርጂቶች (በተለይ ኦፒዲዮ በዚህ ጉዳይ እንደበረታ እየተሰማ ነው) አሁን በኢሃዴግ ስራ አስፈጻሚ ስብሰባ አቀረቡት የተባለው ጉዳይ የትግራይ የበላይነት አለ ነው። ይሄንን መካድም ማድበስበስም አይቻልም። ስለዚህ ትግራይ ከማንም በላይ መጋፈጥ ያለበት ህወሃትን ነው! ትላንት የተፈጠረ ድርጂት ነው። ትግራይ ከህወሃት በፊት እንደሌባ እና እንደዘራፊ ይታይ የነበረበትን ዘመን አላስታውስም። እስከመቸ ነው ህወሃትን የምትሸከሙት?!

አሁን ያለውን ሁኔታ በጦር ኃይል መፍታት አይቻልም። ይሄንን ለህወሃት አስረግጦ መንገር ያለበት የትግራይ ህዝብም ነው።

LEAVE A REPLY