ሕወሃት በጠረጴዛ ዙሪያ እየተሸነፈ ነዉ!/ገረሱ ቱፋ/

ሕወሃት በጠረጴዛ ዙሪያ እየተሸነፈ ነዉ!/ገረሱ ቱፋ/

አሁን እየተካሄደ ባለዉ የኢህአዲግ ሥራ አስፈጻሚ ውይይት ላይ ሕወሃት በጠረጴዛ ዙሪያ እየተሸነፈ እንደሆነ ከውስጥ የወጣ መረጃ ደርሶኛል። #ኦህዴድ እና #ብአዴን በጋራ በመቆማቸው በሕወሃት ላይ ድል እየተቀዳጁ:እንደሆነ መረጃዎቼ ያስረዳሉ።

በመሆኑም ሁለቱ እስከ መረሻው በዚሁህብረት ከቀጠሉ ለተሻለ ድል እንደሚበቁ ምንጮቼ ያላቸዉን ጠንካራ እምነት ጨምረው ገልፀውልኛል። ስብሰባው ዛሬ ማምሻውንም ይቀጥላል። በሌላ በኩል ኃይለማርያም ደሳለኝ የሕወሃት ሰዎች ሁለቱ ድርጅቶች ቀሪዉን ሁለት አመት ሳትጨርስ ስልጣንህን ሊቀሙህ ነው ስላሉት የኦሮሞንና የአማራን ጉዳይ እንደ ሁለተኛ ዜጋ ጉዳይ እየተመለከተው ነዉ።

በትላንትናው ዕለት በቴሌቪዥን ቀርቦ ያነበበው መግለጫ የዚሁ ነጸብራቅ እንደሆነና መግለጫዉ አስቀድሞ በሕወሃት ተፅፎ እንደተሰጠው ምንጮቼ ጠቁመዋል። ኃይለማርያም የተፈጠሩ ችግሮችን ያቀረበበት ቅደመ ተከተልና በንባቡ ውስጥ በኦሮሞ ላይ የደረሰውን እልቂት አኮስሶ በሶማሌ ላይ ደረሰ ያለውን ግድያ አፅንኦት ሰጥቶ ያቀረበበት ሂደት አቋሙን ግልጽ እንደሚያደርገዉ ምንጮቼ አልሸሸጉም። ከኃይለማርያም ደሳለኝ መግለጫ ብቻ ሳይሆን ቀደም ሲልም ከተለያዩ ምንጮች በሁለቱ ወንድማማች የሶማሌና የኦሮሞ ህዝቦች ላይ የደረሰውን ዕልቂት ሰምተናል።

ይሁንና ኃይለማርያም ደሳለኝ የተከሰተዉን ዕልቂት ሲገልፅ የጨለንቆውን በሁለተኛ ደረጃ ላይ አቅርቦ ማንበቡና ዝቅተኛ አፅንኦት መስጠቱ ድርጊቱን ያስፈፀሙ አካላት ጽሁፉን አዘጋጅተው እንደሰጡት ከሚያመለክቱ ማሳያዎች አንዱ ነው ሲሉ ምንጮቼ ገልፀውልኛል። በተጨማርም የኦሮሚያ እና የ አማራ ክልል የፓራላማ አባላት በዛሬው ዕለት እንደ ሀገሪቷ ጠቅላይ ሚንስትር እና የጦሩ ጠቅላይ አዛዥ፤ እየሆነ ስላለውሁኔታ ለፓራላማው ቀርቦ እድገልጽ ተጠይቆ ጊዜ የለኝም ብሎ መቅረቱእየተፈፀመ ላለው ሁሉ ከህግ ተጠያቅነት እንደማያመልጥ ተገልፆዋል።

ምንጮቼ አክለውም አብዲ ኢሌ እና ጄኔራል ገብሬ ዲላ ይህ ድርጊት ከመፈፀሙ በፊት ከኃይለማርያም ጋር እንደነበሩና ይህም ኃይለማርያም ራሱ በወንጀሉ እጁ እንዳላበት እንደሚያሳይ ገልጸዋል። ከዚህም በተጨማሪ በሶማሌ ወገኖቻችን ላይ እልቂቱ ሲቀነባበር ስልኮች እናመንገዶች እንደተዘጉ፣ ይህ ዘግናኝ እልቂት ሲፈፀምም ፎቶ እንደተነሳ፣ በቪዲዮ እንደተቀዳ፣ በኋላ ደግሞ ሄሊኮፕተር ከዚያ 30 በላይ ሲመላለስ እንደነበርና በአካባቢው የነበሩ የኦሮሚያ ፖሊስ አባላት ማየታቸዉ ተገልጿል።

የተቀዳውም ቪዲዮ አላማ የኦሮሚያን አመራር አባላት ስም ለማጠልሸት በንፁሃን ደም የሚደረግ ጨዋታ እንደሆነ ታውቆዋል።ምንም እንኳን ኃይለማርያም ደሳለኝን ህወሃቶች እየተገዳደሩአቸዉ ያሉትን ኦህዴድንና ብአዴንን ለማጥቃት ቢጠቀሙበትም ዕድሉ ኖሯቸው ወደሚቀጥለው ደረጃ ከተሻገሩ እሱንም አሽቀንጥረዉ ጥለዉ በሌላ ተላላኪ እንደሚተኩት ምንጮቼ በርግጠኝነት ነገረውኛል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሕወሃት በጠረጴዛ ዙሪያ ከተሸነፈ ነገሮችን ወደማያባራ እልቂት ሊወስደዉ ስለሚችል በኦሮሚያ እና በአማራ ክልል የሚደረጉ ሁሉም አይነት ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች በሁለቱ ክልል በሚገኙ የፀጥታ አካላት በአይነ ቁራኛ መጠበቅ እንዳለባቸው እና በፌደራል መከላከያ እናፌደራል ፖሊስ የሚገኙ ከ65% የሚበልጡ የሁለቱ ብሔር አባላት ከህዝባቸው ጋር ቆመው እልቅቱን መከላክል እንዳለባቸው እነዚሁ ምንጭች ያሳስባሉ።

በመጨረሻም ህወሃት የንዑሳን የበላይነትን ለማስቀጠልና የብዙኃኑን ህዝብ ድምፅ ለማፈን የሚያደርገው ጥረት ሀገሪቷን ወደ አደጋ ሊያመራ ስለሚቺል ዲያስፖራው በያለበት እየመጣ ስላለው አደጋ ለለጋሽ ሃገሮች ማሳስብ እንዳለበት ተገልጿል።

LEAVE A REPLY