በኦሮሚያ ክልል በህገ-ወጥ ንግድ ሲሳተፉ የተያዙ ሰዎች እስከ 12 ዓመት ተፈርደባቸው

በኦሮሚያ ክልል በህገ-ወጥ ንግድ ሲሳተፉ የተያዙ ሰዎች እስከ 12 ዓመት ተፈርደባቸው

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፦ በኦሮሚያ ክልል በህገወጥ መንገድ የተለያዩ እቃዎችን ሲያስተላልፉ ነበር የተባሉ የመንግስት ወታደሮች በእስራት ተቀጡ። የቢሾፍቱ(ደብረዘይት) የተሰየመው ችሎት በድርጊቱ የተሳተፉ ግለሰቦችን ከ6 እስከ 12 ዓመት በሚደርስ እስራት ቀጥቷል።

ባለፈው ህዳር ወር በምዕራብ ኦሮሚያ ክልል በሀገር መከላከያ ተሽከርካሪ ሻምበል ግደይ ተክሉ የተባለ የህወሓት አባል ህገ-ወጥ (ኮንትሮባንድ) ስኳር ሲያዘዋውር አንዲሁም በፌደራል መኪና ከአወዳይ ወደ ጅጅጋ የስርዓቱ(ህወሓት) ታማኝ ወታደሮች በህ-ገወጥ መንገድ ጫት ሲያሸጋግር በኦሮሚያ ፖሊስ መያዛቸው ይታወሳል። ለህ-ገወጥ አገልግሎት የዋለው ወታደራዊ ተሽከርካሪም ተወርሶ ለኦሮሚያ ክልል ገቢ እንዲደረግ ተበይኗል።

በተለይም በምስራቅ ሐረርጌ አድርጎ በሶማሌ ክልል አቋርጦ ወደ ውጭ ሀገር በድብቅ የሚወጡ ዶላሮች የዚሁ የኮንትሮባንድ ወንጀል አንድ አካል መሆናቸውን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተጋለጠ ይገኛል።ባለፈው ነሐሴ ወርም አዋሽ ሰባት ከ550 ሺህ ዶላር በላይ ሲያሸሹ የተያዙ ሰዎች በእስራት መቀጣታቸውንና ገንዘቡም ከሶማሌ ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች እንዲውል የምዕራብ ሐረርጌ ዞን ፍርድ ቤት መወሰኑ ይታወቃል።

LEAVE A REPLY