የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት የ3 ቀን ውሎ

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት የ3 ቀን ውሎ

/በጌታቸው ሺፈራው/
~ዛሬ ታህሳስ 13/2010 ዓም፣ ተከሳሾች ችሎት ውስጥ ተገኝተዋል። ሆኖም ዳኞች ባለመገኘታቸው ተከሳሾች ወደ ቂሊንጦ ተመልሰዋል።

~ታህሳስ 12/2010 ዓም በችሎቱ ቀጠሮ የነበራቸው ተከሳሾች ፍርድ ቤቱ ውስጥ ከሚገኘው የእስኞች ጊዜያዊ ማቆያ እንዲቀመጡ ተደርጎ በየተራ ወደ ችሎት እየገቡ ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ስለተፈለገ፣ እስረኞቹ ሁላችንም በችሎት ገብተን ነው ጉዳያችን መታየት ያለበት፣ በመዝገብ ተነጣጥለን ወደ ችሎት አንገባም በሚል ተነጣጥለው እንዲገቡ ሲጠየቁ ተቃውመው ወደ ቂሊንጦ ተመልሰዋል። ዳኞችም ቀጠሮም ሳይሰጡ ተመልሰዋል።

~ታህሳስ 11/2010 ዓ•ም
° በጠዋቱ የፍርድ ቤት የስራ ሰዓት እነ ጎይቶም ርስቃይ ላቀረቡት የክስ መቃወሚያ ብይን ይነበብ ሲባል፣ ተከሳሾቹ፣ ብይኑ ከመነበቡ በፊት ሀሳብ እንዳላቸው በመግለፅ እንዲናገሩ ጠየቁ። ፍርድ ቤቱ በበኩሉ ብይኑ የተሰራ ስለሆነ ይነበብ ሲል ተከሳሾች በዳኛ ዘርዓይ ወ/ ሰንበት መዳኘት እንደማይፈልጉ ገልፀዋል።

ፍርድ ቤቱም ተቃውሞ በተነሳባቸው ዳኛ ዘርዓይ አማካኝነት ብይኑን ማንበብ ቀጠለ። ተከሳሾች ፊታቸውን በማዞር፣ ጆሯቸውን በእጃቸው በመድፈን ችሎቱን “አናይም፣ አንሰማም” ብለው ተቃውመዋል። ተከሳሾቹም ችሎቱን አናይም፣ አንሰማም ብለው ብይኑ ተነቧል።

ታህሳስ 11/2010 ዓም በፍርድ ቤቱ የከሰዓት የስራ ጊዜ እነ የሻገር ወ/ ሚካኤል (35) ተከሳሾችም የመቃወሚያ ብይን ለማንበብ ስማቸው ሲጠራ አብዛኛዎች “አቤት” ባለማለታቸው ችሎት ውስጥ እያሉ “አልቀረቡም” ተብለው በፍርድ ቤቱ ተመዝግበዋል። ተቃውሞ የተነሳባቸው ዳኛ ዘርዓይ ብይን ለማንበብ ሲሞክሩ ተከሳሾቹ ባሰሙት ተቃውሞ ብይኑ ሳይነበብ ቀርቷል። ቀድመው ወደ ችሎት የገቡት ችሎት ታዳሚዎች እንዲወጡ፣ ውጭ የነበሩትም እንዳይገቡ ተደርጓል።

LEAVE A REPLY