ከሦስት ዓመታት በኋላ አስቴር ስዩም ተፈታች

ከሦስት ዓመታት በኋላ አስቴር ስዩም ተፈታች

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፦ ከሦስት ዓመታት በፊት በ“ሽብርተኝነት ድርጊት ተሳትፎ አድርጋለች” በሚል ተይዛ የፌዴራሉ አቃቤ ህግ በ2001 ዓ.ም የወጣውን የጸረ-ሽብር አዋጅ ቁጥር 7(1)ን በመተላለፍ “ከግንቦት ሰባት ዓመራር አባላት ጋር መገናኘት” በሚል የሀሰት ክስ መስርቶባት አራት ዓመት እንደተፈረደባት ይታወቃል።

አስቴር ስዩም ማዕከላዊ ለአራት ወራት በቆየችበት ጊዜ ልክ እንደሌሎቹ በእሷ ላይም በዘሯ፣በፆታዋና በፖለቲካ አመለካከቷ ምክንያት ከፍተኛ ስቃይ ተፈጽሞባታል። ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ከተዘዋወረች በሗላም በቤተሰብና ጓደኞቿ እንዳትጎበኝ ከፍተኛ ጫና ይደረግባት ነበር።

አስቴር ሦስት ዓመታትን በግፍ እስራት አሳልፋ ዛሬ መፈታቷ ታውቋል።በመንግስት ቀጭን ትዕዛዝ የፈረሰው አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ አባል እንደነበረችም ይታወቃል።

LEAVE A REPLY