“ብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት” በሀገሪቱ ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ላይ እየመከረ ነው ተባለ

“ብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት” በሀገሪቱ ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ላይ እየመከረ ነው ተባለ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፦ “የኢትዮጵያ ብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት” በሀገሪቱ ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ላይ እየመከረ ነው ተባለ

በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራው “የኢትዮጵያ ብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት” በሀገሪቱ የጸጥታ ሁኔታ ላይ በዛሬው እለት እየመከረ እንደሚገኝ ተገለጸ። በጠቅላይ ሚኒስትር ፅሕፈት ቤት ውስጥ እየመከረ የሚገኘው ምክር ቤቱ የክል የጸጥታ ሀላፊዎች የየክልሎቻቸውን የጸጥታ ሁኔታ ሪፖርት ማድረጋቸውም ታውቋል። በውይይቱ ላይም ከፍተኛ የመንግስት ባለሰስልጣናት፣ የፌደራልና የክልል የፀጥታ አካላትና የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች እንደታደሙበት ተገልጿል። ውይይቱን በተመለከተ የመከላከያ ሚኒስትሩ ዛሬ ከሰዓት በሗላ መግለጫ እንደሚሰጡም ይጠበቃል፡፡

ምክር ቤቱ የመጀመሪያ ስብሰባውን ባለፈው ጥቅምት ወር አካሂዶ “የሀገሪቱን የጸጥታ ችግር ይፈታል” ያለውን እቅድ በማውጣት በመላ ሀገሪቱ ለመተግበር ቢወስንም ህዝቡ እያካሄደ ባለው እቢተኝነትና በኢህአዴግ አባል ድርጅቶች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ተግባራዊ ማድረግ እንደተሳነው በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ መገለጹ ይታወሳል። በም/ቤቱ የጸጥታ እቅድ ውስጥ “ህጋዊ ያልሆኑ ሰልፎችን መቆጣጠር፤ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው መመለስ” ና ሌሎች እቅዶች የተካተቱበት እንደነበረ የሚታወስ ነው።

LEAVE A REPLY