ጋዜጠኛ ዳርሰማ ሶሪና ካሊድ መሃመድ ተፈቱ

ጋዜጠኛ ዳርሰማ ሶሪና ካሊድ መሃመድ ተፈቱ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፦ ጋዜጠኛ ዳርሰማ ሶሪና ካሊድ መሃመድ ከቃሊቲ እስር ቤት ዛሬ ተፈቱ።

ሁለቱ ጋዜጠኞች የተፈቱት የእስር ጊዜያቸውን ጨርሰው መሆኑ ታውቋል። ዳርሰማና ካሊድ መጋቢት 12/2007ዓ.ም ተይዘው የጸረ-ሽብር አዋጁን አንቀጽ 7/1 እንዲሁም በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀፅ 32/1 እና 38/1 ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ ወንጀል ፈጽመዋል በሚል የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19 ወንጀል ችሎት እያንዳንዳቸውን የሦስት ዓመት ከስድስት ወር እስራት ተፈርዶባቸው ነበር።

ጋዜጠኛ ዳርሰማ ሶሪና ካሊድ መሃመድ ከመታሰራቸው በፊት ራዲዮ ቢላል ላይ ይሰሩ እንደነበር ይታወቃል። ዳርሰማ ሶሪ በጋዜጠኝነት ሙያ ውስጥ ከ18 ዓመታት በላይ በተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ውስጥ ሰርቷል።

LEAVE A REPLY