የቴዲ አፍሮ የመጀመሪያ ኮንሰርት በባህር ዳር ጥር 12 ቀን ሊታይ ነው!

የቴዲ አፍሮ የመጀመሪያ ኮንሰርት በባህር ዳር ጥር 12 ቀን ሊታይ ነው!

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፦ እውቁ የሙዚቃ ሰው ቴዎድሮስ ካሳሁን አለም አቀፍ እውቅና የተጎናጸፈውን ‘ኢትዮጵያ’ የተሰኘውን አልበም ካውጣ በሁዋላ በአዲስ አበባ የተለያዩ ቦታዎች ሊያቀርብ የነበረው ኮንሰርት ግልጽ ባልተደረጉ ምክንያቶች ሲከለከል እንደንበር ይታወቃል

የ’ኢትዮጵያ’ አልበሙ ምረቃና ኮንስርቶቹ በአዲስ አበባ እንዳይታዩ የፖልቲካ ሰዎች ጫና ምክንያት እንደተከለከለ የሚታመን ሲሆን ዛሬ ቴዲ አፍሮ በፌስ ብክ ገጹ ይፋ እንዳደረገው የአማራ ክልል የባህር ዳር መስተዳድር በሰጠው ፈቃድ መሰረት “ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር ”
የመጀመሪያው ኮንሰርት በባሕር ዳር ከተማ ጥር 12 ቀን በባህር ዳር ታላቁ ብሄራዊ ስታዲዮም ኮንሰርቱን እንደሚያሳይ አስታውቅዋል.

ቴዲ አፍሮ በፌስ ብክ ገጹ ይፋ ያደረገበት እንደሚከተለው ቀርቡዋል

ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር
የመጀመሪያው ኮንሰርት በባሕር ዳር

ቅዳሜ ጥር 12 ቀን በአማራ ክልላዊ መንግሥት ዋና ከተማ በሆነችው በውቧ ባሕር ዳር ከተማ ከ80 ሺሕ ሕዝብ በላይ ማስተናገድ በሚችለው በታላቁ ብሄራዊ ስታዲየም ከአቡጊዳ ባንድ ጋር የሙዚቃ ዝግጅቴን እንዳቀርብ ለአማራ ክልላዊ መንግስት፣ ለባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤትና ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት ጥያቄያችንን አቅርበን የነበረ ሲሆን ፤ ጥያቄያችንን የተመለከቱት ሁሉም አካላት ያለ አንዳች ቢሮክራሲና እንግልት በጠየቅነው ቦታና ዕለት የሙዚቃ ድግሳችንን ለቱሪስት መስህቧ ባሕር ዳር ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች፣ ከመላው የአገራችን ክፍል ለሚመጡት የሙዚቃ አፍቃሪዎችና አለም አቀፍ ቱሪስቶች ማቅረብ እንድንችል የፈቀዱልን በመሆኑ ታላቅ ደስታ ተሰምቶናል።

እኔም ወደ ሙዚቃው አለም ከገባሁበት በተለይም የመጀመሪዬ አልበሜ ከሆነችው አቡጊዳ ጀምሮ በቅርብ እስካሳተምኩት 5ኛው አለበሜ “ኢትዮጵያ” ድረስ ከፍተኛ ፍቅር የለገሰኝን የሙዚቃ አፍቃሪ ለማስደሰት ከአቡጊዳ ባንድ ጋር ከፍተኛ ዝግጅት እያደረግን ስንሆን፤ ቅዳሜ ጥር 12 ቀን ለመገናኘት ያብቃን እላለሁ።

ከሁሉ አስቀድሞ ይህ ሁሉ ይሆን ዘንድ ፈቃዱ የሆነውን ቅዱስ እግዚአብሄርን ክብር መስጋና ይድረሰው እያልኩ ፤ ለጥያቄያችን አወንታዊ መልስ በመስጠትና ጥር 12 ቀን የምናቀርበው የሙዚቃ ኮንሰርት የተሳካ እንዲሆን ከፍተኛ ድጋፍ ላደረጉልን፡
ለአማራ ክልላዊ መንግስት
ለባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት
በዚህ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ርብርብ ላደረጋችሁት ለባሕር ዳር ከተማና አካባባዋ ወጣቶች ከፍተኛ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ ይህ የሙዚቃ ዝግጅታችን በሌሎችም የአገራችን ከተሞች የሚቀጥል ሲሆን ጊዜው ሲፈቅድ ዝግጅታችንን የምናቀርብባቸውን ቦታዎችና ቀኑን እናሳውቃለን።

ባሕር ዳር ጥር 12 ቀን በታላቁ ብሔራዊ ስታዲዬም በሰላም ያገናኘን !

ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)

 

LEAVE A REPLY