አንድ እስረኛ ሁለት ፖሊሶችን ገድሎ፤ሦስት አቆሰለ

አንድ እስረኛ ሁለት ፖሊሶችን ገድሎ፤ሦስት አቆሰለ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፦ በጋምቤላ ከተማ አንድ እስረኛ ከማረፊያ ቤት ወደ ፍርድ ቤት እየተወሰደ እያለ ከአጃቢ ፖሊሶች የአንዱን መሳሪያ በመንጠቅ ሁለቱን ገድሎ ሌሎች ሦስት ሰዎችን አቆሰለ።

እሰረኛው አጃቢ ፖሊሶችን ከገደለ በሗላ ለማምለጥ ሲሞክር በክልሉ የፀጥታ ኃይሎች መገደሉን የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አከነ ኦፓዳ ማረጋገጣቸውን ሪፖርተር ዘግቧል።

ላለፉት 26 ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ በሰፈነው ኢ-ፍታሃዊነት፤የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዲሁም የዘር ማጥፋት ወንጀል ከተፈጸመባቸው አካባቢዎች አንዱ ጋምቤላ ክልል ሲሆን የነባሩን ህዝብ መሬት እየተነጠቀ ለህወሓት አባላትና ዘመድ አዝማድ መሰጠቱ የክልሉ ህዝብ ሲቃወመው መቆየቱ ይታወቃል።

በ1996ዓ.ም በአኝዋኮች ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል መፈጸሙን የተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት ማረጋገጣቸው የሚታወስ ነው።

LEAVE A REPLY