የመለስ ዜናዊ ደብዳቤ ከሙታን መንፍስ ሰፈር /ከሙሉቀን ገበየሁ/

የመለስ ዜናዊ ደብዳቤ ከሙታን መንፍስ ሰፈር /ከሙሉቀን ገበየሁ/

የትግል ጓደኞቼ፣ የሕወሃት አመራር አባላትና ለተከታዮቻችን በኢሕአዴግ ደርጅት ስም ከፍትኛ የስልጣን ቦታ ለሰጥናችሁ ሁሉ። እነሆ ባካል ከትለየኋችሁ ጥቂት አመታት አለፈ። እንድምን አላችሁ? ከተለይኋችሁ ወራት ጀምሮ ቀንና ለሊት ሳይቀር የኔን ህልም እንደመምርያችሁ አድርጋችሁ ስትምሉ ስትግዘቱ እንድነበር በመንፈስ ካለሁበት ቦታ ሆኜ ተካታትዬ ነበር። አሁን ግን ጭንቅ ላይ ስትሆኑ ስሜን እንኳን ለማንሳት ፈርትችኋል፤ እንደውም ረስታችሁኛል።

ይሄ ኋይለማርያም ደሳልኝ የሚባል ሰው “መለስ የጀመርውን ሁሉ እፈጽማልሁ” እያለ ፪ አመት መሉ በግል ጸሎቱ ሁሉ ሳይቀር ሲያንሳኝ እናንተንም ሲያድንቁርችሁ ሰንብቶ፤ ወንበሬን የያዘ መስሎት ሲቀባጥር፡ እነአባይና በርከት፣ እንዲሁም አርከበ ጭንቅላት፣ ምላስና ሆድ ቢሆኑለትም ፈሪና አደርባይ ሆኖ አረፈው። የእኔን ዱካ መከተል ትቶ አይንና ጆሮውን ከፍቶ የህዝቡን ጥያቄ ቢያዳምጥ ይሻለዋል።

ስገዛውና እንድ አሰኘኝ ሳደርገው ከነበርው አገርና ህዝብ በህመም ስቃይና በሞት ከተለየሁ ጀምሮ ያለሁበት ቦታ ሆኜ በምድር ላይ ሆኜ ያሰለፍኩትን ግዜና ወሳኔ ለመመርመር ችያልሁ። እንሆ እናንተም እኔ በኄድኩበት መንገድ ከሄዳችሁ የሚጠብቃችሁ ዋይታና ሰቆቃ ነው።

በእኔ ውሳኔ ምክንያት ህይወታቸውን በአስከፊ ሁኔታ ያጡ ብዙ ኢትዮጲያዋያን መንፈስ እዚህ መንፈሴን በጣም ረብሸውታል። የሰራሁት ድርጊት ሁሉ በአምላክ ፊት ለፈርድ ሲቀርብ እኔን የሚከላከል ምንም የአጋዚ ሰራዊት ወይም ፌድራል ፖሊስ የለም። ወርቅ ህዝብ ብዬ ከሌላው የኢትዮጲያ ህዝብ አስብልጬ የጠራሁት የትግራይ ህዝብ አጠገቤ አልቆመም። በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዝብ ሰውሬ በባንክ አስቅምጬ ቢሆንም እዚህ ምንም አልጠቀመኝም። ሌኒን ወይም ስታሊን ወይም ማኦ ሊያድኑኝ እዚህ አልመጡም።

ስቃዩ የጀምረኝ ገና ከናንት ጋ በምድር ሳልሁ፡ በህመም ተይዤ በቢልጄም አገር ሀኪም ቤት ሳለሁ ነው። ቀዶ ሀክምና ቢደርግልኝ፣ መድሃኒት ቢሰጡኝ በህመም ከመስቃየትና በትኩሳት መንደድ ህሊናዮን በመሳት ስሰቃይ ከርሜ ወደ ሌላው አለም በሞት መለእክ አሸጋጋሪነት ሄጃልሁ። እናንተ በድን ስጋዬን ይዛችሁ አገሩን ሁሉ ማቅ ስታለብሱ፤ እዚህ በመንፈስ ግን የሙታን ሰፈር ተወሰጄ እንደ ስራዬ ወደሚገባኝ የመንፈስ ቦታ አርፍያልሁ። የሚያከብርኝ፣ የሚፈራኝ፣ የሚታዘዘኝ ማንም የለም። የኔን አይንት ስራ በምድር ላይ ከፈጸሙ እርጉም የሰዎች መንፍስ ጋ ተቀላቅዬ የፍርዴን አግኝቼ ዘውትር ለቅሶና ዋይታ ላይ ነኝ።

በልጅነቴ ጀምሮ በልቤ የነገሰው ጥላቻ ህይወቴን በሙሉ አብላሽቶት ቀርቶል። አማራ የሚባል ህዝብ የትግራይንና የኤርትራን ህዝብ በደሉ በሚል የተጋነን ስብቀት ተከትዬ በተለይ ኢትዮጲያ የሚባል አገርን ማፈራረስና የትግራይን የበላይነት ለማንገስ ህይወቴን በሙሉ ደከምኩ። በትግራይና ኤርትራ አንዳንድ ሽማግሌዎች የዘባረቁትን ታሪክ እየሰማሁ አድጌ፤ የአጼ ምኒሊክ ንጉሰ ነግስት መሆን የአጼ ዮሓንስን ዘርና የትግርኛ ተናጋሪን ንግስና ባአማራ ህዝብ ተንኮል ተነጠቅን ብዬ፣ ባለፈ ታሪክ ተከትዬ፣ ህይወቴን በሙሉ ለጥፋት ባከንኩ።

በልጅነቴ ጀምሮ የታመቀውን ጥላቻ ትምህርትና እድሜ ሳይቀይሩት የሞትኩ ሰው እኔ ነኝ። ከአድዋ ተማሪዎች የተለየ እድል ደርሶኝ ጂኔራል ዊንጌት ትምህርት ቤት አዲስ አበባ ስገባ ፡ ሁሉ የኢትዮጲያ ጎሳ በሚኖርባት አዲስ አበባ ሰው መሆን ሲገባኝ፤ እኔ ግን ከኤርትራ ከመጡ በመገንጠል ስሜት የተጠመቁ ተማሪውች ጋ ወግኜ፤ ሌላውን ኢትዪጲያዊ በዝቅተኝነት በማየትና በማገለል የልጅነት ወጣትነቴን ጀምርኩ። ሰው እንድሆን ከፍትኛ ትምህርት የመማር እድል ቢያጋጥመኝም፡ ሀኪም ሆኜ የሰውን ልጅ ጠላት የሆነውን በሽታ እንደመዋጋት ይልቅ ከህክምና ትምህርት ቤት ዩንቭርሲቲ አፈንግጭ ወጥጬ ሌላውን ሰው ለመግደል ወደ ሽፈትነት ሜዳ ገባሁ።በማናወቀውና ከባኋላችን ጋ ከማይስማማው የባእድ ፍልስፍና ተጠምቄ የጥላቻ ልቤና ጉልብቴን አጠንከርኩ።

እንኆ በበርሃ ሜዳ ሆነን ስንቱን የትግራይ ሰው እንደኛ በልቡ ጥላቻ ካላኖርክ ብለን አሰቃየነው። አንተ ፊወዳል ነህ፣ ሃብታም ገበሬ ነህ፣ የኢድዩ ደጋፊ ነህ፣ የደርግ ሰላይ ነህ፣ የድርጅቱን ስራአት አልጠበክም ብለን ስንቱን የትግርይ ህዝብ ጨረስንው?!

በተለይ 1977 ድርቅ ግዜ ፤ከውጭ ርዳታ ለርሃብትኞች የመጣውን እርዳታ ነጥቀን፤ ለመሳሪያና ለድርጅታችን ማሳድጊያ ለኤፈርት ሀብት መስብሰቢያ መሰርት ጣልነው። በእዝያ እርዳታ ህይወታቸው ሊተርፉ ይችሉ የነበሩ ስንት ህጻናትና አርጋውያን እንዲሁም ሴቶች ነፍስ እዚ እርፍት ነስትወኛል፤ ባአምላክ ፊት ይክሱኛል።
በክፋት ታውረን በትግራይ ተራሮች ጉድጓድ ምስን ከነህይወታⶨው ስንቱን ቀብረናል፣አስረናል፣ ገድለናል?!

ወደ መሃል አገር ገብተን የስንቱን ንብርት ዘርፈናል። አዲስ አበባ ገብተን ስልጣን ስንይዝ አገሩን ሁሉ እንዳያምጽብን፣ ሰውን ሁሉ በጎሳ፣ በቋንቋና በሃይማኖት ለይተን በከፋፍልህ ግዛው ዚዴ፤ ስንቱን ህዝብ አስለቀስን። ከመጀምሪያውም በጥላቻ የተናሰንባቸውን አማራ የሚባሉ ህዝብን ያድርገንበት የዘር አድሎ፣ግድያ፣እስራት እንዲሁም ማፈንቀል፣ ዘር ማምከን አሁን እዚህ ሁኜ ስራችንን ስመረመርው በምን አይነት ጥላቻ ታውርን፣ አገር ምድሩን ስናጥፋ እንደነበር ታውቆኛል።

አገር አይገንጠልም ብለው የተንሱትን የዩንቨርሲቲ ተማሪውችን በመግደል ጀምርን፤ ስንቱን አስረን፣ አሰቃየን ከሃገር አባረርን። እነ ፕሮፌስር አስራትን አስረን፣ አሰቃይተን ገደልን። የስንቱን ንብርት፣ መሬት፣ ሃብት ዘረፍን። አልመነውና አየተነው የማናወቀውን ሃብት ለብቻችን ዘረፈን፣ ቃርመን፣ ስንቱን ባዶ አደርግን ከጎዳና ጣልነው?!

ምርጫ 1997 ራስችን አውጀን፤ ህዝቡ በምርጫ አልፈልገንም ሲለን ስንቱን ሰላማዊ ህዝብ ለሰልፍ እንደወጣ በአጋዚ ሰራዊት አስጨርስነው? ስንቱንስ በእስር ቤት አጎርነው፡ ከሃገር እንዲሸሽ አድርግነው?!

ሕዝቡ ሲያብርና አንድ ሲሆን ፡ በስልጥናችን እንዳይመጣ በጎሳና ሀይማኖት፣ የሃስት ታሪክ እየፈጥርን ስንቱን አጫረስነው? አብሮ በፍቅር ተከባብሮ ሲኖር የነበርን ህዝብ፤ በሃሰት ታሪክና በተጋነን ትንሽ እውነት ይዘን ወደጠላትነት ለውጠን አጫረስነው ። አቲዮጲያዊነት የሚለውን የሐገር ፍቅርና መንፍስን ከህዝቡ ልብ ወስጥ ለማውጣት ስንቱን ተንኮል አደርግነው?! ባንዲራውን አውርደን፤ ታሪኩን አንኳሰንና ለውጠን ማንነቱን እንዲጥራጥር አደርገነው?!

እግዚኋቤር የሰጠውንና አባቶቹ ከጠላት ጠብቀው ያስርከቡትን ምድር እና መሬት እኛ ባዋጅ ቀምተነው በሃይልና ጉልበት የኢትዮጲያ መሬት ሁሉ የመንግስት ነው ብለን የኛ አደርግነው። ስንቱን ገበሬ መሬቱን አስለቀቀን፤ አልደግፈከነም ብለን የሚገባውን ከልከልነው። ኑሮው የተመሰርተበትን፣ ከቅድም አያቶⶩ ጀምሮ የሚጠቀምበትን መሬት ለባልሃብት ሸጥንበት፤ሰንቱን ከቤቱ አስወጥቱን ከጎዳና ጣልነው ?!

እኔም ቢሆን አብርውኝ በርሃ ሜዳ የወረዱትን ጓዶቼን ስልጣኔን ይነጥቃሉ ብዬ ስንቱን አሳደድኩ፤ አሰርኩ፤ አግር አስለቀኩ። ሚስቴንማ ከማንም በላይ ሾሜ በአገሩ ሁሉ ንጉስና ንግስት ሆንባችሁ። የስንቱን ንብርት ዘረፍን።ኤፈርት በሚባል ድርጅት ስንቱ ከንግድ አወጣን፣ ከባንክ በብድር ስም በህጋዊነት የ ህዝብ ገንዝብ ዘርፈን። በዘርኝነት መንፍስ ተጠምቀን ስንቱን የትግራይ ተወላጅ ካድሬና የድርጅቱ ደጋፊን ባለስልጣን ሃብታም አድርገን በህዝቡ ላይ አለቃ አደርግነበት?!

እንግዲህ ይህን ድብዳቤ የምጽፈላችሁ በሕወሃት አመራር ላይ ያላችሁ እንዲሁም ኢሕአዴግ ስም ስልጣን የሰጥናችሁ ደጋፊዎቻችን የኔን መሰል ጥላቻ በልባችሁ ነግሶ አሁን ደርስ አልጥገብ ባይነት እየምራችሁ ወደገደል እንዲምወስዳችሁ ተገልጽሎኛልና የሚጥብቃችሁ ስቃይና ዋይታ መሆኑን ልነግራችሁ ስለፈለኩ ይህን ደብዳቤ ጻፍኩ። ከትንሽ ዘመን ቦኋል ህዝቡ አስሮ ያኖራችኋል፣ ይግድልችኋል፤ ከፊሎቻቹ ሁ በበሽታ እንደ እኔ ተሰቃይታችሁ ትሞታላችሁ፤ ከዚያም አልፎ ስትሞቱ መንፋስችሁ እዚ ለፍርድ ቀርቦ ዋይታና ሰቆቃ ውስጥ ዝንተ አለም ትኖራላችሁ።

የተበደለ፣ የመረርው፣ የተጨቆነ ህዝብ ተነስቶባችኋል። ማሰሩ፣መግደሉ፣ማፈናቀሉ ሁሉ ሊገድበው አልቻለም።የሚሻልወን ይልቁንም ልንግርችሁና ህይወታችሁን እና መንፈሳችሁን የማዳን እድል ብትጠቀሙ እምክራለሁ። የምትኮሩበት ሰራዊትና የደህንነት ክፍል፤ የዘርፋችሁት ሀብትና ገንዝብ፣ በአድሎ የጠቀማችሁት ሰውና ህዝብ ሁሉ እናንተን ተከትሎ አይመጣም። ብቻችሁን ነው ወደዚኛው የመንፈስ አለም የምትመጡት።

ስናፈርስ የከርመነውን አገር፣ ስንዝርፍ የነበርውን ንብርትና ሃብት መልሱ። መርዝ እየንሰንስን ያጋጨነውን ጎሳና ህዝብ አስታርቁ፤ በጉልበት የያዝነውን ስልጣን እና ዙፋን ለህዝቡ በሚገባው ህጋዊ አስራር መልሱ። እናንተም ያሰቀየማችሁትን ህዝብ ይቅርታ ጠይቃችሁ ወደ ፈጣሪያችሁ ተመለሱ። ንሳሃ ገብታችሁ ከፈጣሪያችሁ ተታርቁና ከሚጥብቃችሁ ዘላለማዊ ዋይታና ሰቆቃ እራሳችሁን አድኑ! የኢትዮጲያ ህዝብም ምናልባት ይቅር ይላችሁ ይሆናል።

1

LEAVE A REPLY