የጉራ ፋርዳ ወረዳ የጸጥታ ሀላፊን ጨምሮ 15 ሰዎች እስከ እድሜ ልክ እስራት...

የጉራ ፋርዳ ወረዳ የጸጥታ ሀላፊን ጨምሮ 15 ሰዎች እስከ እድሜ ልክ እስራት ተፈረደባቸው

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፦ በቤንች ማጂ ዞን ጉራ ፋርዳ ወረዳ በ2007ዓ.ም በአማራ ተወላጆች ላይ ባደረሱት ጉዳት የህይወትና የንብረት ውድመት ተጠያቂ በመሆናቸው የወረዳው የጸጥታ አስተዳድር ሀላፊን ጨምሮ ሌሎች 15 የስራ ሀላፊዎችና ግለሰቦች ላይ እስከ እድሜ ልክ የሚደረስ ጽኑ እስራት እንደተላለፈባቸው ታወቀ።ጉዳያቸው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ የወንጀል ችሎት ሲታይ የቆየ ሲሆን ከመስከረም እስከ ጥቅምት 2007ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ለ43 ንጹሃን ዜጎችና 12 የፌዴራል ፖሊስ አባላት ህይወታቸውን እንዲያጡ ያደረጉ እንዲሁም በሰባቱ ላይም ከፍተኛ የአካል ጉዳት እንዲደርስ ማድረጋቸውን በክሳቸው ላይ ተገልጿል።

ተከሳሾቹም 1ኛ. ፃዲቅ የራ ዘይስ የጉራ ፈርዳ ወረዳ ሚሊሻ—እድሜ ልክ እስራት

2ኛ. አርሶ አደር ካብትኔ ሳራ—22 ዓመት ጽኑ እስራት

3ኛ. አርሶ አደር ጋጉ ጫዳ—– እድሜ ልክ እስራት

4ኛ. ከበደ ለኩዩ የወረዳው ፀጥታ አስተዳደር ሀላፊ—-19 ዓመት ጽኑ እስራት

5ኛ. ረዳት ኢንስፔክተር ምስክር ሀጅዋቀ የወረዳው የፖሊስ አዛዥ—-19 ዓመት ጽኑ እስራት

6ኛ. ምርሳ ታየ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ—-18 ዓመት ጽኑ እስራት

ከጉራ ፋርዳ ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ ከ20 ሺህ በላይ አማራ መፈናቀል ከፌዴራል መንግስቱ ጋር በመሆን ከፍተኛ ሚና የነበራቸው እንደሆኑም መረጃዎች ይጠቁማሉ።በወቅቱ የአማራ ተወላጆች ከጉራ ፋርዳ በጅምላ መፈናቀላቸውን ተከትሎ የወቅቱ የደቡብ ክልል አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ ሽፈራው ሽጉጤና ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት አቶ መለስ ዜናዊ “ደን መንጣሪዎች” ናቸው በማለት የዜጎችን መፈናቀል ህጋዊ ሽፋን ለመስጠት መሞከራቸው የሚታወስ ነው።

LEAVE A REPLY