የተወካዮች ምክር ቤት “ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ” አዳዲስ የስራ ሀላፊዎችን ሾመ

የተወካዮች ምክር ቤት “ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ” አዳዲስ የስራ ሀላፊዎችን ሾመ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፦ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢና ሰባት የቦርድ አባለትን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበው ማፀደቃቸው ታወቀ።

በዚህ መሰረት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ አምባሳደር ሳሚያ ዘካሪያ በመሆን መሾማቸው ታውቋል። አምባሳደር ሳሚያ ከ1972 እስከ 1998ዓ.ም ድረስ በማዕከላዊ ስታስትቲክስ ኤጀንሲ ውስጥ ዳሬክተር ሆነው ለረጅም ዓመታት መስራታቸው ተነግሯል።

በአሁኑ ጊዜም በኦሮሚያ ክልል የህገ መንግስት ትርጉም ኮሚሽን ጽህፈት ቤት ሀላፊ ነበሩ የተባሉት አቶ ደሞዜ ማሜ ደግሞ ምክትል ሰብሳቢ ሆነው ተሹመዋል።የቦርድ አባላት ሆነው የተቀመጡት ደግሞ ወ/ሮ የሺሃረግ ዳምጤ፣ ፕሮፌሰር ፋንቴ አባይ፣ ወ/ሮ ፀሀይ መንክር፣ አቶ ተካልኝ ገ/ሥላሴ፣ አቶ ጀማል መሐመድና አቶ ሀብቴ ፍቻላ መሆናቸው ታውቋል።

አምሳደር ሳሚያ ዘካሪያ ከ1998 አስከ 2009ዓ.ም የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲን ዋና ዳሬክተር በነበሩበት ወቅት “የአማራ ህዝብ” በ2.4 ሚሊዮን ቀንሶ በመገኘቱ ከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ ገብተው ነበር። ወ/ሮ ሳሚያ በናይጀሪያ አምባሳደር ሆነው እየሰሩ እንደነበረም ተጠቅሷል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የህወሓት አንድ ቅርጫፍ መስሪያ ቤት እንደሆነና በነፃ ምርጫ ስም የስርዓቱን እድሜ ማራዘሚያ ነው በሚል በኢትዮጵያ ህዝብ በኩል አመኔታ እንደሌለው ይታወቃል።

LEAVE A REPLY