ለችግሮች፣ መፍትሄ በኪሱ የሆነው ጋዜጠኛ – ውብሸት ታዬ!

ለችግሮች፣ መፍትሄ በኪሱ የሆነው ጋዜጠኛ – ውብሸት ታዬ!

/በኤልያስ ገብሩ/

ውቤ፣ “ካለበት ጊዜ …አርቆ ወደፊት ማየት የቻለ፣ በስራው የተግባር ጋዜጠኛ መሄን የቻለ ነው።” ብል ከግፍ እስሩ በፊት የነበሩ የተግባር ስራዎቹ ህያው ምስክሮች ናቸው። .

…የውብሸት የሰላ ብዕር፣ የሟቹን ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ልብ የሚያርድ ነበር። ውብሸትን መለስ አይረሳውም። እግር በእግር ተከታትሎ፣ እኩይ ስራዎቹን በብዕሩ እያከሸፈ አስቸግሮታልና። የውቤን የጋዜጠኝነት ስራና የአገዛዙን እኩይ-ግብረ መልስ፣ በወቅቱ ባልደረቦቹ የነበርን እናውቀዋለን። “ካላረፍክ፣ ልጅህ ፍትህን ገድለን እናሳይሃለን!” የሚሉ ዘግናኝ ዛቻዎች ደርሰውበት ጭምር በድፍረት ስራውን ሲሰራ የነበረ ጋዜጠኛ ነው።

..ውብሸትን፣ ቀድሞ የመረዳት ተፈጥሯዊና ሙያዊ ልምዱ፣ ነገርን ከስር መሰረቱ ተንትኖ የማስረዳት ብቃቱ፣ መረጃ ላይ ተንተርሶ በምክንያት የመተቸት አቅሙ …ለግፍ እስር ዳርጎታል። ለዚህም ነው፣ በጸረ-ሽብርተኝነት አዋጁ ቀዳሚ ሰለባ የሆነው። ሰኔ 12 ቀን 2003 ዓ.ም ከታሰረ ጀምሮ፣ ዛሬም ድረስ በግፍ እስር ላይ ይገኛል። ህወሃት/ኢህአዴግ፣ የውብሸትን ቅስም ለመስበር ዕቅዱ ነው፣ ግን አልቻለም። ለምን? ውቤ ታጋሽና ብርቱ በመሆኑ!

…በወቅቱ ውብሸት፣ የእነ መለስ ዜናዊን፣ የበረከት ስምኦንንና ጀሌዎቻቸውን የሴራ የፖለቲካ አካሄድ፣ በፍጥነት ተረድቶ በብዕሩ አጸፋ የሚመልስ ትንታግ ጋዜጠኛ ነበር። ስለሚሰራው ስራ መረጃ የማሰስ ትጋቱና ብቃቱ፣ እንዲሁ በቀላሉ አይነገርም። ከራሱም አልፎ፣ አብረነው ለምንሰራ ባልደረቦቹ ጭምር፣ ለስራ የሚጠቅሙ መረጃዎችን ቀድሞ በመረዳት፣ ጠረጴዛችን ላይ በማስቀመጥ ያስገርመን ነበር። ለችግሮች ሁሉ መፍትሄ በኪሱ ነው – ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ!

ይህንን አርቆ አላሚ ጋዜጠኛ ፍቱልን! …ለነገዋ ኢትዮጵያ ያሻታል። የጋዜጠኝነት ሙያንም በተግባር ወደፊት የማራመድ እምቅ አቅም አለው! …

#ታላቅ አክብሮት፣ ለውብሸት ታዬ!

LEAVE A REPLY