ከሰኞ ጀምሮ ለሦስት ቀናት የሚቆይ የስራ ማቆም አድማ እንደሚካሄድ ተገለጸ

ከሰኞ ጀምሮ ለሦስት ቀናት የሚቆይ የስራ ማቆም አድማ እንደሚካሄድ ተገለጸ

/ኢትዮጵያ ነገ/ ከሚቀጥለው ሰኞ ጀምሮ ለሦስት ቀናት የሚቆይ የስራ ማቆም አድማ እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡ አድማው በሚደረግባቸው ቀናት ውስጥ ምንም ዓይነት የስራ እንቅስቃሴ እንደማይካሄድ ተገልጿል፡፡

በቄሮዎች እንደተጠራ የተነገረለት የሦስት ቀናቱ ህዝባዊ የስራ ማቆም አድማ በኦሮሚያ ክልል ብቻ ሳይሆን በመላው ኢትዮጵያ ተግባራዊ እንዲሆን ጥሪ መቅረቡንም ለማወቅ ተችሏል፡፡ በህወሓት አገዛዝ የተገሸገሸ ሁሉ በስራ ማቆም አድማው እንዲካፈል ተጠይቋል።

አድማው በሚተገበርባቸው ከተሞች የሚካሄዱ የትራንስፖርትም ሆነ የንግድ እንቅስቃሴዎች እንደሚገቱ የሚጠቁመው የአድማው መርሐ-ግበር፤ ሌሎች ህዝባዊ እንቅስቃሴዎችም እንደማይኖሩ ይገልጻል፡፡

በመሆኑም የአድማው ተሳታፊዎች ለሦስት ቀናት የሚሆን የምግብም ሆነ ሌሎች አስፈላጊ ሸቀጦችን እንዲያሰናዳ አዘጋጆቹ አሳስበዋል።የስራ ማቆም አድማው በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው

የህዝባዊ ተቃውሞው አካል እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፤ አድማውን ማካሄድ ያስፈለገውም የህወሓትን አገዛዝ ለማስጨነቅና ስልጣን እንዲለቅ ለማስገደድ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በቅርቡ ስራ የጀመረው የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመርም አገልግሎት እንዳይሰጥ ቄሮዎች(ወጣቶች) አስጠቅቀዋል። ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በኦሮሚያና አማራ ክልሎች በተለያየ ጊዜ የተሳካ ህዝባዊ የስራ ማቆም አድማ መደረጉ የሚታወስ ነው።

LEAVE A REPLY