የስራ ማቆም አድማው ዛሬ ተጀምሯል፤ እነ በቀለ ገርባ

የስራ ማቆም አድማው ዛሬ ተጀምሯል፤ እነ በቀለ ገርባ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፦ ለሦስት ቀናት የተጠራው የስራ ማቆም አድማ በኦሮሚያ በርካታ ከተሞች ዛሬ ተጀምሯል። በኦሮሚያ ክልል በርካታ ከተሞች የስራ ማቆም አድማውን ተከትሎ የመንግስት መስሪያ ቤቶችም ሆነ የግለሰቦች የንግድ ድርጅቶች አገልግሎት መስጠት አቋርጠዋል።

በአምቦ፣ጉደር፣ወሊሶ፣ጅማ፣ነቀምት፣ መቱ፣ አርሲ፣ ሻሸመኔ፣ ሂርና፣ ሐረማያ፣ ድሬዳዋ፣ ባሌ ሮቤና በሌሎች በርካታ ከተሞች ህዝብ በነቂስ ወደ አደባባይ በመውጣ “ወያኔ ይውረድ፣ ንጹሃን ዜጎችን መግድል ይቁም፣ የህሊና እስረኞች ካለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈቱ” የሚሉ መፎክሮች የታጀበ የተቃውሞ ሰልፍ እንደተደረገ ተገልጿል።

በአዲስ አበባ ዙሪያ በቡራዩ፣ ለገጣፎና ሰበታ ከተሞችም የስራ ማቆም አድማው ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ ታውቋል። በባሌ ዞን ማዳ ወላቡ ከተማ የአጋዚ ወታደሮች በነዋሪው ላይ ተኩስ በመክፈት በርካታ ሰዎች እንደተጎዱ መረጃዎች እየወጡ ነው። ከአዲስ አበባ ሐረር፣ ድሬዳዋና ሀዋሳ የትራንስፖርት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል።

በሌላ በኩል ትናንት ማምሻውን የአቶ በቀለ ገርባ፣ ጉርሜሳ አያና፣ አዲሱ ቡላላ፣ ደጀኔ ጣፋ፣ ጌቱ ጋሩማ፣ ተስፋዬ ሊበንና በየነ ሩዳ ክሳቸው እንዲቋረጥ መወሰኑን ለስርዓቱ ቅርብ የሆኑ ሚዲያዎች ይፋ አድርገዋል።

LEAVE A REPLY