በወያኔ መራሹ አገዛዝ ላይ ያነጣጠርው ትግል በእጅጉ ይቀጥል! /ከሙሉቀን ገበየው/

በወያኔ መራሹ አገዛዝ ላይ ያነጣጠርው ትግል በእጅጉ ይቀጥል! /ከሙሉቀን ገበየው/

ኢትዮጲያውያን ከሩብ-ምእተ አመታት በላይ በዘለቀው የሕወሃት (ወያኔ) አገዛዝ እየተሰቃዩ ነው። በጥላቻ መሃጸን የተጸነሰው ከትግራይ የበቀለው የጥቂቶች ስብስብ ሕወሃት፤ እጅግ በረቀቀ አስከፊ አገዛዝ ስልቱ ኢትዮጲያውያንን እየጨቆነ ይግኛል።

ሕወሃት፡ ሲጸንስ ጀምሮ በጸረ-አንድነት፣ በመከፋፈል፣ በጥላቻ ተራራ የተሞላ ለራሱ ጥቅም ብቻ የቆመ ጥገኛ አገዛዝ ነው። ኢትዮጵያውያን በእናት አገራቸው የሚገባቸውን መሰረታዊና ተፈጥⶂዊ የሰእባዊ መብትን የረገጠ ኢ-ዲሞክራሳዊ አገዛዝን የመሰረተ ነው።

ሕወሃት፡ በጥቂት ትግራውያንና በኤርትራ መገንጠል በሚያምኑ የቤተስብ አባሎች የበላይነት የተመሰረተ ስብስብ ነው። 6 % የኢትዮጲያን ህዝብ የሚሆነውን የትግራይን ህዝብ እንኳ በፍጹም አይወከልም። በትግርይ ህዝብ ቀሚስ ስር ተደብቆ ራሱን የትግraይ ህዝብ ተውካይ አድርጎ ግን በአዳባbaይ ይፎክራል።

አብዛኛው በትግራይ የሚኖር ህዝብ በፍርሃትና በድርብ ጭቆና ስር ወድቋል። ወያኔን ከመደገፍ ውጪ ሌላ አማራጭ አልተፈቀደለትም። ነገር ግን ከትግራይ ውጪ በአብዛኛዊ የኢትዮጲያ ክፍል የሚኖርው ና በውጭ አገር የሚኖሩት ትግሬዎች አብዛኞቹ የስራአቱ ተጠቃሚ ናቸው። ወያኔ በኢትዮጲያውያን ለይ የሚፈጽመውን እስራት፣ግድያ እንድ ጠበቃ የሚከራከሩለት እነሱ ሲሆኑ አገዛዙ እንዲቀጥል የማያደርጉት ቅጥፈት የለም።

ወያኔ በስውር ጥበቡ የሃሰት ፌደራላዊ አስተዳድር መስረትኩ እያለ የራሱን ሰዎች ከበስትጀርባ አስቀምጦ፤ የጎሳ ተውⷎዮችን ፊትለፊት እያሳየ፤ በጦር መሳረያ ጉልበት ሀይል አገዛዙን ቀጥⶀል። በ ከፋፈልህ ግዛው ዘዴው እየተጠቀመ፡ የጥላቻ መርዝ እየነሰነሰ፣ አንዱን ጎሳ ባንዱ ላየ እያሰንሳ፣ እያጣላ፣ በሃይማኖት ልዩነት ግጭት እየፈጠረ እድሜውን አራዝሟል። በዚህ ተንኮል ስልቱ ብዙ ኢትዮጲያውያንን እያፈናቀለ፣ቤት አልባ እያደረገ፣ ከስራ እያስወገደ፣ንብረት እየዘረፈ ከሃገር እንዲሰደዱ አድርጓል።

ባለፉት 27 አመታት፡ ሕወሃት ሰራዊቱን፣ ኤኮኖሚ አውታሩን፣ የደህነንት ክፍሉን፣መገናኘውን ከፍል እንዲሁም የማህበርሰቡን ዋና ዋና ከፍል በማስፈራርትና በማሰቃየት በጉልበት ተቖጣጥሮታል። “አንድ ለ አምስት” በሚለው የስለላ መዋቅሩ ተበትቦ ህዝቡን እንዳይተንፈስ ቢያደርገም አሁን ግን እንዲያ ሊቀጠል አይችልም።

በፋሽስታዊ የጭከና አገዛዙ የጥላቻ፣ የመከፋፈል፣የጥርጣሬ እና የሃስት ማንነትና ታሪክ በውስጣችን ዘርቷል። ብዙሃኑን ከፋፍሎ፣እርስ በርስ አናክሶና በጥላቻ እንዲጠባብቅ አድርጎ ለራሱ የሚያመቸውን የጥቂቶች አገዛዝ ዘርግቷል። ይሄ ወያኔ እንኳን ከስልጣን ከወርደ ቦኋላ ፈተና የሚሆነን መርዝ ነስንሶብናል።

ይህን የጥገኛ አገዛዝ ለመጣል የኢትዮጲያ ህዝብ በሰላማዊ መንገድ ከጅምሩ ታግሏል። ወያኔ ግን በ”ከፋፍልህ ግዛው” ዘዴው እየትጠቀመ ሲያከሽፈውና ሲያፈነው ኖሯል። ለአብነትም የ 1997 ምርጫ ተከትሎ የተነሳውን የህዝብ ሰላማዊ ጥያቄ በ አስራትና ደም በማፈሰስ ተወጦታል።

ባለፉት 2 አመታት በአዲሱ ትውልድ ሰላማዊ የትግል እንቅስቃሴ ወያኔ ተንቀጥቅጦል። ወያኔ ስልጣን ላይ ከወጣ ጀምሮ እንኳን የተወለዱት ወጣቶች የአገዛዙን የክፋት ፖሊሲ፣ ፍልስፍና አፈና በእጅጉ ፈትነውታል።

በአገር እና በውጭ ሃገር የተሰማሩ የአገዛዙ የፕሮፓጋንዳ ተቀጣሪዎች የሚደልቁት ከበሮ በሃሰት፤ በተራ ወሬ፣በማጭበርበር፣ በቅጥፈት፣ በማጋነን፣ በጥርጣሬ እንዲሁም በማስፈራርት ላይ የተምሰረተ በ ቅዥት እንድሚዘባርቅ አይምሮውን እንደሳተ ሰው ሆነው ተገኝተዋል። የህዝቡን ትግል ለማኮላሸት ገንዝብ የሚከፍላቸው እበላ ባዮች አስመሳይ መሰሪዎችን ተጠቅሞ ነው።

ኢትዮጲያውያን ከፊትለፊታቸው የተደቀነውን የወያኔ ትልቅ እንቅፋት ለማለፍ ብልሃት፣ ዘዴና ጥበብ እንዲሁም ትግስትና ሰባዊነትን መላበስ አለብን። ባለፉት አስር አመታት ከስራናቸው ስህተት መማር አለብን። በህብረትና በመተባብር እየስራን ትግሉን ከዳር ማድርስ አለብን። የተባበርና የተደራጀ ህዝባዊ የሆነ ከያንዳዱ ብሄር፣ ጎሳ፣ ሃይማኖት፣ የትምህርት ደርጃ፣ የእድሜ፣ የጾታ፣ የችሎታ፣ የሃብት ገደብ ሳይኖር ግፊት ብናደርግ ሕወሃትን ከፍጻሜ እናደርሰዋለን።

ከሚተናንቀን ግላዊነት፣ የጎሳ ማሃብር፣ እንዲሁም የፖለቲካ አመልካክት ወጣ ብለን ኢትዮጲያዊ ሰው መሆን (ኢትዮጲያ በምትባል ውድ ሃገር በአምላክ ፈቃድ ተፈጥረናልና አለበልዚያማ በኢትዮጲያ ባልተወልድን ነበር) አለብን። ኧምሮችንን ግልጽ አድርገን ጆራችንን ከፈተን የአብዛኛው ኢትዮጲያውያንን ጥያቄ እናዳምጥ። በጭለማ የተሸሸገውን ብርሃን ያሳየናል። ከጥላቻ፣ ፍርሃትና ከጠላትነት አራንቋ ያወጠናል። ከጨልማ ዋሻ ዳር ከምታንጸባርቀው የነጻነት ብርሃን ያደርሰናል። ህብረትና ተባብሮ መስራት ብቻ ነው ከተደቀንበን ፈትና የሚያወጣን።

ባለፈው 27 አመታት የተነፈግነውን ነጻነት የምናገኝበት ቀን ተዳርሷል። በኢትዮጲያን ላይ የተዘራው የጥላቻ፣ የመከፋፈልና የጥርጣሬ ደምና የሚጠራብት ግዜ ቀርቧል፤ የነጻነት አየር ከዳር ይነፍሳል። ነጻነትና እኩልነት ያለባት አዲስ አገር ተቃርባለች። በየትኛውም መስክ ያሉ ኢትዮጲያውያን ይህን ትግል ተባብርው ካዳር ማድርስ ይጠበቅባቸዋል።

የወደፊት እድላችንን ለመወስን በምናደርገው ትግል ፊት፤ ለፊትቻን የተጋርጠውን ፈተና ለመወጣት ስንፍጨርጨር ለወያኔ እንዲሁም ለታሪካዊ ጠላቶቻችን (ከቅርብም ከሩቅም) የሚርዳ ክፈተት እንዳይኖር መጠንቀቅ አለበን።

በህዝብ ትግል መትንፈሻ ያጣው ወያኔ ትግሉን ለማቀዝቀዝና ለማቆም ከሰማይ በታች ያለ ተስፋና የውሸት ቃል ቢጋባም፡ ከመሰርቱ ወያኔ አጭበርባሪ፣ ቀጣፊና ቃሉን የማይጠብቅ መሆኑን በማውቅ የወያኔ ፍጻሜ እስኪደርስ ድርስ ትግሉን በመቀጠል በወያኔ ፍጽሜ ነው ነጻነታችንን የምናረጋግጠው።

ኢትዮጲያን ሆይ፤ ይህን እውንታ አውቀን የጸረ-ህወሃት ትግሉን አፋፍመን መቀጠል አለበን። ሕወሃት ገድል አፋፍ ላይ ስላለ ዘረ፣ ሃይማኖት፣ ጾታ፣ እድሜ፣ የአካል ብቃት፣ ሃብት፣ የትምሀርት ደርጃ ሳንል ተባብርን መገፈተርና ፍጻሜውን ማድረስ አለብን።

የመንግስት ሰራትኛ ሆይ፤ ለመብትህ ለነጻነትህ ተነስ። የስራ አድማ አድርግህ የወያኔን አከርካሪ አጥንት አሽመደምድው።

ተማሪዎችና መምህራኖች። ወያኔ ለነፈጋችሁ የሰበአዊ መብትና የእኩል ዜግነት ተነሱ። እናንተን አግልሎ የተለየ ጥቅማጥቅሙን “ለምርጦቹ ና ለደጋፊዎች” አድርጎታል።

ዲፕሎማት ሆይ። ከህወሃት ሚሲዮኖቹ አገልጋይንት ውጡና ህዝባችሁን ተቀላቀሉ። የወያኔ ወንጀልንና የክፋት አድራጎት ለአለም አስታውቁ ፤ አጋልጡ።

ነጋዴዎች ሆይ፤ እናንተን ከውድድር ሜዳ አስወጥቶ በጉልበቱ ተመክቶ በዘራፊ ካምፓኒዎቹ (እንድ ኤፈርት ያሉ) እየተጠቀመ የአገሪቱን ንግድ ሁሉ ተቆጣጥሮ አስችግሮትኋልና ለመብታችሁ ተነሱ።

የፖሊስ ሰራዊት ሆይ፡ አንተን እየተጠቀመ ወንድምህን እንድታስር፣ በሃሰት እንድትከስ ፣ እንዲሁም እንድትገድል የሚያደርገህን ይህን ግፍኛ ሕወሃት እንቢ በለው።

የአገር መከላከያ ሰርዊት ሆይ። ያነተ ድርሻ አገር ሊወር የመጣን የውጭ ወራሪን ሰራዎት መመከት እንጂ ወንድምህን ግደል ሲልህ አይሆንም በለው። እንደ እንሰሳ ልንዳህ የሚለወን የሕወሃት ጂኔራሎችና የበላይ ሹሞች ላይ ጠምንጃህን አዙር እንጂ ወገነህን አተንካ። ሰከን በል።

የሃይማኖት አባቶች ና መሪዎች ሆይ፤ ስለ እውነት ቁሙ። ስለ ፈጣሪ ‘በጎች’ ቁሙ። የሚደርሰውን በድል ይቁም በሉ። ለሐይማኖት ተከታይ ልጆቻችሁ እግዚሃቤር የሰጣቸውን መብት ሲነፈጉ፣ ሲጨፈጨፉ አይሆንም በሉ።በከፋፋዩ፣ ባርመኔው፣በገዳዩ ህወሃት ላይ ተነሱ።

ገበሬዎች ሆይ፤ መሬታችሁን ነጥቆ ለራሱ ባደርገው ህወሃት ላይ ተነሱ። የተሻለ ገንዝብ ሲያይ ለውጭ ዚጋ መሬታችሁን ሽጦ በምሬታቹህ ላይ ‘ባርይ’ እንድትሆኑ በሚያደርጋችሁ ወያኔ ላይ ተነሱ። በእግዚሃቤር ጸጋ በላባችሁ የምታመርቱብትን መሬት ስትሉ ወያኔን በቃ በሉት።

ጋዜጠኞች፣ ጸሃፊያን፣ የሚዲያ ሰውች ሆይ፤ ስለ ህዝባችሁ፣ ስል ሃገራችሁ ስትሉ አገራችንን የውስጥ ቅኝ ግዛት በያዛት ሕወሃት ላይ ተነሱ። እራሳችሁንና አካባቢያችሁን እንዳትገልጹ መብታችሁን በነፍጋችሁ ወያኔ ላይ ተነሱ።

ሙሁራኖች ሆይ፤ በስቃይ ላይ ያለውን ወገናችሁን አግዙት። መንገዱን፣ ህወሃትን ማፈርሻ ስልቱን ለህዝባችሁ አስተመሩ። ዘዴወን፣ መፍቴውን የተሻለ አገር መገንቢያ ሂደቱን ጠቁሙት።

ተቀዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ሆይ፤ በመካከላችሁ ያለውን ልዩነት አጥቡ ና በጸረ-ወያኔ ትግሉ ተባበሩ። በህወሃት የማታለያ ድራማ አትከፋፈሉ። ስለ ህዝባችሁና አገራችሁ ስትሉ ተነሱ። ወገናችሁን ምሩት፤ መንግዱን አሳዩት።

ከሁሉም ጎሳ የተወለድን ኢትዮጲውያን ሆይ፤ ኢትዮጲያ አገራችን የለቅሶና የዋይታ የሞት አገር ሆናለች። እናቾት ያለቅሳሉ፡ ወጣቶች የፊት ተስፋቸውን ተነፈጉ። የሕወሃትን አስከፊ ወረራና አገዛዝ እንድጥንቱ አባቶቻችን ተባብርን እንመክተው። እግዚሃቤር የሰጠንን ነጻነታችንን እናስከብር። በሕወሃት ላይ ተነሱ!
ባፋፍ ላይ የቆመውን ትንፋሽ ያጠርውን ወያኔ ግዜ አንስጠው። ከፊትለፊታችን ያለውን ድላችንን አናስንጥቅ።
በወያኔ የታሰሩትን፣ የታርዙትን የተሰዉትን ወገኖቻችን ደም እንዲሁ ፈሶ አይቀርም።

ለኛም ለልጆቻችንም ተስፋ የምትሆን አዲስ አገር እንገንባ!

LEAVE A REPLY