ይድረስ ለኦሮ ሞ የህግ ባለሙያዎች ማህበር /ከደባሱ መሰሉ/

ይድረስ ለኦሮ ሞ የህግ ባለሙያዎች ማህበር /ከደባሱ መሰሉ/

በማህበር መደራጀት ጠቀሜታዉ ብዙ ነው። ዕዉቀትን ጉልበትን እና ሃብትን አሰባሶ ለመሥራት አይነተኛ መሣሪያ ነዉና።

ህብረት ለልማት ፤ ህብረት ለበጎ ሥራ ፤ህብረት ችግርን ለመፍታት ሲዉል እሰየዉ ያስብላል።

ማህበራትን በመመስረት በኩል በኦሮሞ ማህበረሰብ ዉስጥ ከሌላዉ ኢትዮጵያዊ በተለየ የተሻለ እንቅስቃሴ ዪታያል። ይህ የእናንተ ማህበር እና የኦሮሞ ምሁራን ማህበር በምሳሌነት የሚጠቀሱ ናቸዉ።

ማህበር ማቋቋሙ ብቻዉን እንድ መጨረሻ ግብ መታየት ያለበት ግን አይመስለኝም። በተመሠረቱት ማህበራት የተገኙት መልካም ዉጤቶች እንጂ !!

ወደ ተነሳሁበት ጉዳይ ልመለስና በ22-23 ኦክቶበር በሎንዶን ከተማ ዉስጥ አንድ ኮንፈረንስ አዘጋጅታችሁ ነበር።

የኮንፈረንሱም የትኩረት አቅጣጫዎች የሚከተሉት ነበሩ በድህረ ገጻችሁ ላይ እንደሰፈረዉ።

1.በኢትዮጵያ ዉስጥ እየተካሄደ ካለ ህዝባዊ አመጽ የምንወስዳቸዉ በጎ ጎኖች /Positive lessons learned from the ongoing protest/,

 1. ህዝባዊ እንቅስቃሴዉን ወደ መልካም አቅጣጫ ለመቀየር ምን መድረግ አለበት በሚለዉና በሂደቱም የህዝቦችን አንድነት ጠብቆ ለመያዝ የሚያግዙ አዳዲስ ሃሳቦችን ለማመንጨት /New ideas on what has to be done to ensure a positive ending to the movement and maintain the unity of the people in the process./
 2. እየተካሄደ ባለዉ ህዝባዊ አመጽ ምክንያት እየተባባሰ ያለዉን ችግር በመረዳትና በስልጣን ላይ ያለዉ ሃይል ቢወድቅ የኦሮሞ የፖለቲቻ ድርጅቶች ዝግጅታቸዉ ምን ያህል ነዉ /What preparation has been or should be made by Oromo political organizations in anticipation of further crisis including a sudden collapse of the regime./
 3. ያለዉን ችግርና ታሪክንም ከግምት ዉስጥ በማስገባት በሄራዊ መግባባትን በመገንባት በኩል የኦሮሞ ህዝብ ምን የሚማርዉ አለ / What lesson can the Oromo people learn from history to build national consensus including the current ensuing crisis./

በተዘጋጁት የትኩረት አቅጣጫዎች በኩል ምንም ችግር የለም። እሰየዉ በርቱ የሚያስብሉ ናቸዉ።

ስለ ኦሮሞ ህዝብ ብዙ ተብⶀል። የኦሮሞ ህዝብ ጀግና ህዝብ ነዉ፤ የኦሮ ህዝብ ለኢትዮጵያ የጀርባ አጥንት ነዉ፤ የኦሮሞን ህዝብ እንገንጥል ማለት ኦሮሞን አሳንሶ ማየት ነው ፤ ወዘት

እንዳለመታደል ሆኖ ግን ጀግና እየተረሳ ባንዳ የሚወደስበት፤ ስለ አገር አንድነትና ብልጽግና የሚያስብ  የሚሰደብበት ፤ስለ አንድነት የሚሰብክ የሚወገዝበት ስለ መለያየት የሚሰብክ የሚሞካሽበት ዘመን ላይ በመሆናችን  የኦሮሞ ብቻ ሳይሆን የሁሉም የአገራችን ህዝብ ችግር መሠረታዊ መፍትሄ ማግኘት አልቻለም።

እንደሌላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ የኦሮሞ ህዝብ ታግሎና አታግሎ ነጻ የሚያወጣዉ ድርጅት አላገኝም። የሻቢያን እና ዎያኔን ወኔ የተላበሰዉ ኦነግ አንግቦ የተነሳዉ የመገንጠል ፖለቲካ ሻቢያን እና ወያኔን ወደ ግባቸዉ እንዲደርሱ ያገዘ መሆኑ አጠያያቂ ባይሆንም ለኦሮሞ ህዝብ ግን የፈየደዉ ነገር የለም። ይህም የሆነበት ከአነሳሱ መሠረታዊ ችግር የነበረበት በመሆኑ ይመስለኛል ኦሮሞን መገንጠል።

ዘⷝይቶም ቢሆን  ይህን ዕዉነታ ብዚዎቹ የኦሮሞ ልሂቃን አሁን የተረዱት ይመስላል ቢዘገይም። ኮንፈረንሱንም ያዘጋጃችሁት ከዚህ እዉነታ በመነሳት ይመስለኛል።

ጥያቄዉ ግን

 1. ይህ ኮንፈረንስ ግቡን መትⶆአል ትላላችሁ ወይ ነው
 2. ኮንፈረንሱን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻዉ የጥያቄና መልሱን ክፍለ ጊዜ ጨምሮ ተመለከትኩት። የአንድ ጽንፈኛ ንግግር ቀልቤን ሳበዉ። የዚህ ግለሰብ ንግግር የመላ ኢትዮጵያዉያን መነጋገሪያ ለወያኔ ደግሞ ለትግል መቀልበሻ መሳሪያ ሲሆን እያየን ነዉ። ኢትዮጵያዉያንን እያነጋገረ ያለዉ የሰዉየዉ ንግግር ብቻ ነዉ እኔ ግን ከተሰብሳቢዉ ዪሰጥ የነበረዉ የጭብጭባ ድጋፍ ወዴት እየሄድን ነዉ የሚለዉን ጥያቄ እንዳነሳ አድርጎኛል። ከዚህ አንጻር ስብሰባዉ በአክራሪዎች እጅ አልወደቀም ትላላችሁ።
 3. በእንደዚህ ዓይነት ጉዳዮች ላይ ዎያኔ እጁ ረጅም እንደሆነ ይታዎቃል። እሳት ይለኩስና ተመልሶ ደግሞ እሳት አጥፊ ነኝ ይላል። ከዚህ አንጻር በኮንፈረንሱ ላይ የወያኔ እጅ ላለመኖሩ ምን ያህል እርግጠኞች ናችሁ
 4. ከአክራሪዎቹ አንዱ የሆነዉ ግለሰብ ኦሮሞን ነጻ ለማዉጣት ኢትዮጵያ መፍረስ አለባት ዪለናል። ነጻ መዉጣት ሌላ አገር ማፍረስ ሌላ። ማነዉ ይህን መብት ለሱ የሰጠዉ ይህ አነጋገር ከመስመር የወጣ አይደልም ትላላችሁ በዲሞክራሲያዊ አገር ተቀምጦ ስለ ሌላ አገር ማፍረስ መናገርን ዛሬ ዓለም እየተዋጋ ካለዉ ሽብርተኝነት የሚለየዉ ምንድን ነው
 5. ግለሰቡ ከቦረና እስከ ወሎ የተሠማራ አገር አፍራሽ ሠራዊት እንዳለዉ ነግሮናል ይህ ከሆነ ታዲያ ዛሬ የኦሮሞ ወጣቶች በአልሞ ተኳሽ የወያኔ ዘረኞች ሲገደሉ ብዙዎች ወደ ወህኒ ሲጋዙ የሱ ወታደር የትነዉ ያለዉ ። ነው ወይስ አገር ለማፍረስ ካልሆነ ጥብመንጃዉ ጥይት አይተፋም
 6. የ25 ዓመት የመገንጠል ፖለቲካ የት ሲያደርስ አይታችሁ ነዉ ስብሰባ እያዘጋጃችሁ እንደዚህ ዓይነት ከመስመር የወጡ አካሄዶችን የምታስተናግዱት? እንደዚህ ዓይነት ስድ እና ማሠሪያ የሌላቸዉ አስተሳሰቦች እዚያዉ እንደተለመደዉ በህቡዕ እንጂ በአደባባይ የህዝብን ልብ እንዲያቆስሉ መፈቀድ ያለበት አይመስለኝም። ምናልባት የዲሞክራሲ መብት ነዉ ልትሉ ትችሉ ይሆናል ነገር ግን እኮ ዴሞክራሲ የሌላዉን መብት እስካልነካህ ድረስ ነዉ። አገሬን ለማፍረስ ሲዝት እኔ እጄን አጣጥፌ የምቀመጥ ይመስላችኋል? ይህ አካሄድ ግን ወያኔን እንጂ ማንንም አይጠቅምም ለዚህ ነው ኮንፈረንሳችሁ ምን ያህል ከወያኔ የጸዳ ነው የሚል ጥያቄ ከላይ ያቀረብኩት።
 7. ብዙዎቻችን ተሰደናል። በመሰደዳችን ግን ለዚያች አግር ችግር ፈቺዎች ነን ብለን መመጻደቅ የምንችል አይመስለኝም።የትግሉ ባለቤቶች በእሳቱ እየተለበለቡ ያሉት እነ በቀለ ገርባና መራራ ጉዲና እና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ወጣቶች ናⶨዉ። የስደረትኛ ሚና ከድጋፍ ሰጪነት የዘለለ አይመስለኝም። ከዚህ አንጻር ለትግሉ አስተዋጸኦ ለማድረግ ይህ አሁን የያዛችሁት አካሄድ መልካምፍሬ የሚያፈራ ይመስላችኋል?
 8. በመጨረሻም ኮንፈረንሱ እንዲያተኩርባቸዉ ያሰፈራችኋቸዉን ክ1-4 ያሉ ነጥቦች እንዳቀረባችሁ ሁሉ የኮንፈረንሱን ዉጤትስ ለምን አልገመገማችሁም?

እነዚህን እና ሌሎችንም አጠቃላችሁ መልስ እንደምትሰጡኝ ተስፋ አደርጋለሁ ።

በመጨረሻም እንደ አንድ ለኢትዮጵያ በጎ አሳቢ ሁሉም የሃገሬ ጉዳይ ያገባኛል የሚል ዜጋ ወያኔን በመታገል በኩል የድርሻዉን እንዲወጣ ችግሮችን በዉይይት በመፍታት በኩል እራሱን እንዲያዘጋጅ ከዚያም ለሁላችንም የምትሆን የሁላችንም መብት የተጠበቀባት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት በሚያስችለን መንገድ በኩል መንገዳችንን ብንጀምር ጉⶋችን የተቃና ይሆናል ብየ አምናለሁ። ከዚህ ዉጭ ግን አዳራሽ እየሞሉ አገር ለማፍረስ መዶለት እስካሁንም አልጠቀመም ከንግዲህም አይጠቅምም እላለሁ !!!

በሃቀኞች ትግል ሠላማዊት እና ዲኦክራሲያዊት ኢትዮጵያ ትገነባለች

LEAVE A REPLY