የትላንቱ ካሳሁን አድማሱ፤ የዛሬው ዳንኤል አበበ ማነው? /ግርማ እንድሪያስ/

የትላንቱ ካሳሁን አድማሱ፤ የዛሬው ዳንኤል አበበ ማነው? /ግርማ እንድሪያስ/

የዲያስጶራ ይሁዳዎች ክፍል ፪

ባለፈው ብዕሬ ደም ተፍታ ነበር። ደም ያልኩት ብዙ የደሙ፣ የተሰቃዩ ሰዎችን እያወኩኝና የዕውኑን ዓለም ይሁዳዎች መተረክ ስትችል ላይ– ላዩን ብዕሬ ተሽከርክራ ስለነበረ ነው። አጠገባችን ያሉ ”ይሁዳዎችን” መግለጽ ሲቻል፣ የቅዱስ መጽሃፉ ይሁዳ ላይ አተኮረች። አንጀታቸው ቅቤ የጠጣም፣ ቆሽታቸው ያረረም አስተያየታቸውን እንዲልኩ ‘ኢሜሌን‘ አስቀምጨ ነበረ። በርካታ መልዕክቶች ደርሰውኛል። ከረኩት፣ ገፈቱን ከቀመሱት፣ የት–የሌለ ጅቦችን ካስተዋሉት አንባቢዎቼ። አመሰግናለሁ።
«ሟች የገዳይን ሃሳብ ቢያውቅ ኖሮ አብሮት አይሄድም ነበር።» ብዙ ሟቾች ከገዳዮቻቸው ጋር ያዘግማሉ። ደስ የሚለው ግን ገዳዮችም አንድ ዕለት ሟቾች መሆናቸው ነው። ለጊዜው ባለንባት ምድር ይሄ ሃቅ ነው።

እንደመግቢያ

ቃኤል ወንድሙን አቤልን ገደለው። ምን አ ድርጎት?…. ይሄን ስተነትን አልገኝም። ይልቅስ አቤል ዜጎቹ በሃገሩ ልጆች የደረሰበትን የገለጸበት ብዕር መግቢያዬ ባደርገው እመርጣለሁ።
«ቀልድ ያለፈበት ጨዋታ ሆኗል። አሁን ዘውጉ ተቀይሯል። ፍጥጥ–ግጥጥ ያለ ዕውናዊ ድርሰትን መመልከት ጀምረናል። ዓይን – አያየው የለም። አሁን ደግሞ ገራፊዬን አሳየኝ። በኤሌትሪክ ገመድ ጀርባዬ እስኪቀደድ የገረፈኝን፣ በመጥረጊያ እንጨት ውስጥ እግሬን ያነደደኝን፣ እጄ በካቴና ታስሮ ወለል ላይ ያንከባለለኝን፣ ጨለማ ቤት ውስጥ አስገብቶ ከየት እንደመጣ በማላውቀው ጅራፍ አሳሬን ያሳየኝን፣ እናቴን ከመቃብር ጠርቼ ”አንቺ እናቴ ለምን ጥሩ ሁን ብለሽ አሳደግሽኝ? ብዬ እንድወቅሳት ያደረገኝን፣ወንድ…የወንዶች ቁና በካቴና የታሰረን ሰው በእኩለ–ሌሊት ጠርቶ አፉ ውስጥ ጨርቅ ወትፎ የሚደበድብ በዓይኔ በብረቱ አየሁት።» ፌብሪዋሪ 23 ቀን 2016 ። አቤል ዋቤላ የዞን ዘጠኝ ጦማሪ የደረሰበትን መግቢያው ላይ ያሰፈረውን መግቢያዬ አደረኩት።

የሚፈጥረው ስሜት

አቤል የደረሰበትን በብዕሩ ግለት ብቻ የገለጸው አይመስለኝም። ብዕሩ ከገለጸው በላይ ስቃዮችን አ ቤል አሳልፏል። ሌሎችም ወገኖች ዕለት በዕለት የሚደርስባቸው ነው። የአቤልን ብዕር ቡና እየጠጡ ካነበቡ፣ ቡናው እሬት – እሬት ማለቱ አይቀርም። እየበሉም ከሆነ ያለመጡትን መዋጥ አ ይቻልም። እህሉ አፍ ላይ ከመንቀዋለል ውጭ። ክፉዎች ግን ስቃይን አ ሳምረው መሳቅ ይችሉበታል። የ ”ክፉዎች መዝናኛ የሌሎች ስቃይ‘‘ ነውና።

ከብዙ ጊዜያት በኋላ ብዕሬ አንድ – አንድ እያለች የ‘ዲያስጶራ‘ን ይሁዳዎች ለማጋለጥ ወስናለች። ከሰገባዋ ወጥታለች። ዲያስጶራ የጥሩዎችም፣የክፉዎችም መሸሸጊያ (መደበቂያ) በመሆኗ ክፉዎች ”ቁርበት አንጥፉልኝ…” ሲሉ ታነጣጥራለች። ትተኩሳለች። ቁርበት ሳይሹ አርፈው የተደበቁት ”ክፉዎች” ላይ ብዕሬ ኢላማም– አላማም የላትም። ምክንያቱም የተደበቁበት ሃገራቶች እና መንግስታቶች ሃላፊነትና ውሳኔ ነው። ሲያጨበጭቡላቸውም ሆነ፣ ሲቀበሉዋቸው ከማየት ውጭ ምንም ለማለት ህሊናዬም – ብዕሬም አትፈቅድም። ነገር ግን ‘ሁለት ዋሻ‘ ሲይዙ አልፈቅድም። የትላንቱ ሽፍትነታቸው አገርሽቶ ”ቁርበት አንጥፉልኝ” የሚሉ ጅቦች ሲሆኑ አልችልም። ሁለት ዋሻ ያልኩት:- አንዱ ያረፉበት ሃገር ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ተወልደው ባደጉበት ሃገር በመናገራቸው፣ በመኖራቸው፣ በማሰባቸው ሰለባ የሆኑ ዜጎች ባቋቋሙት የተቃዋሚ ድርጅቶች፣ ማህበራቶች ውስጥ መወሸቃቸውን ብቻ ሳይሆን ከፊት– ከፊት መታየታቸው ነው። አንደኛው ዋሻ አያገባኝም የምለው እጃቸው በደም የጨቀየን ወንጀለኛ ማጋለጥም፣ መፍረድም ያረፉበት ሃገር ጉዳይ ነው። ይሄንን ስል በጥቁቱም ቢሆን ያረፉባቸው ሃገሮች የሚሰጡትን ውሳኔ አይቻለሁና ነው። የቀይ ሽብሩ ተዋናይ የነበረው እሸቱ ዓለሙ በኔዘርላንድ እስር ቤት ውስጥ የሚገኘው በኢትዮጵያውያኖች ወይም በጋዜጠኞች ጥቆማና ክስ አ ይደለም። እንደዚያ ቢሆን ”ማሰረጃ ዶት ኮምና”- http://www.masreja.com/ ኦባንግ ሜቶ ብዙ ወንጀለኞችን በፋይልና በመረጃ አ ቅርበው ሲፈረድም ሆነ ሲፈየድ ያየነው የለምና። ለብዕሬ አንድ ማሳያ መስጠቴ አንባቢን ግንዛቤ ለማስጨበጥም ያን ያህልም ምቀኛ ብዕር ከሰገባ ያለማውጣቴን ለማሳየት ነው።

¤ ¤ ¤

ትላንት በስርዓቱ ውስጥ ሰላማዊውን ሰው ቁጭ ብድግ ሲቀጡት፣ አ ቅሉን ሲያሳጡት የነበሩ ሰዎች ”ይቅርታ!” የምትለዋን ቃል ቢደፍሩት እንኳንስ ብዕርን የሚያህል ትልቅ ነገር ከሰገባው መጎተት ቀርቶ ባጨበጨብንላቸው ነበር። ግን ያንን መመልከት የሰማይ ያህል ይርቃል። በዚህ ጉዳይ ወይም በይቅርታ ጠያቂነት የቀድሞውን ፕሬዚዳንት ነጋሶ ጊዳዳ በኔ ውስጥ ትልቅ ስፍራ የምሰጣቸው ናቸው። ለህዝቡ የጠየቁት ይቅርታ ካለሁበት ዲያስጶራ አ ማለውኝ ለውጭ ሃገር መጽሔት ለንባብ አ ብቅቼአ ቸዋለሁ። የተመሰጥኩባቸውና የምረካባቸው ውድ ሰው!.…

እነሆ አንድ ይሁዳ ላሳያችሁ ነው።
የትላንቱ ካሳሁን አድማሱ አበባው፤ የዛሬው ዳንኤል አበበ ማነው?en300x169

”ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ” በሚል ሽፋን ታዋቂ የህግ ባለሙያዎች በ‘ሾኬ‘ ተብለው ከተፈለፈሉት ድዊዎች ውስጥ አንዱ ነው። አንቱ የተባሉ ሰዎችን ጉዳይ በአቃቢ ህግነት ይመለከትና ይተነትን ነበር። ጉዳዩ በዚሁ ሰው ተይዞላቸው ለሞት ከተዳረጉት የፖለቲካ ሰዎችና ጋዜጠኞች ውስጥ በስም መጥቀሱ አስፈላጊ ይመስለኛል። እስከ ሞታቸው ፍጻሜ ጉዳያቸውን ከያዘው ሰለባዎች ውስጥ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ፣ ከፖለቲከኞች ሲጠቀሱ ተስፋዬ ታደሰ ከጋዜጠኞቹ አ ንዱ ነው። ተስፋዬ ታደሰ የመስታወት መጽሔት አዘጋጅና አሳታሚ ነበር። ዶክተር ታዬ ወልደሰማያት ተፈራ አስማረ፣ ዳንኤል ክፍሌ፣ መጽሃፈ ሲራክ፣ መላኩ ታደሰ፣ መላኩ ጸጋዬ፣ እስክንድር ነጋ፣ ሲሳይ አጌና እኔ ግርማ እንድሪያስ ወርቁ አለማየሁ ወዘተ….. ስንቱን በስም ዘርዝሬ እችላለሁ? በዚሁ ”አቃቢ ህግ” በሚል ሽፋን በአራዳ ሁለተኛ ችሎት ጉዳዩ የታየላቸውና የሚንከራተቱ ነበሩ።

ወሽመጥ….

ዕውቁ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ከኢሳት ሆኖ ወደ አ ዲስ አ በባ ስልክ ደወለ። ስልኩን ያነሱት ”ጓል ጎላ” ነበሩ። ወይም ወይዘሮ አዜብ መስፍን።
”ወይዘሮ አዜብ መስፍን?” አለ ሲሳይ አጌና።
ስልኩን ያነሳችው ወይዘሮ አዜብ ” አዜብ አይደለሁም” ስትል ሸመጠጠች። አዜብ – አዜብነቷን እያወቅን ተገረምን። ጠያቂው ሲሳይም ከዚያ በላይ መሄድ አ ልቻለም። ”ድምጽዎት የርስዎ ነው!” ቢላትም ”እኔ አይደለሁም!!” ስትል ደረቀች። ምን ማድረግ ይቻላል?

ዛሬ… የትላንቱ አ ቃቢ ህግ የጋዜጠኞችንና የፖለቲከኞችን ጉዳይ ክሱን በማቀናበርና በማቅረብ ሲያንገላታ የነበረውን ‘‘አንተ ካሳሁን!…” ማለት አ ይቻልም። ዳቦ ሳያስቆርስ ባወጣውና በቀየረው ደንኤል አበበ በተሰኘው ስሙ ሃጢያቱን ሰርዯል። ከምናውቃቸው ወንጀለኞች ለየት የሚያደርገውና ድርቅናውንና ፈጣጣነቱን የምናይበት በድምጽም በምስልም ከፊት– ከፊት መቅደሙንና መድፈሩን ስንመለከት ነው። ዛሬ ወንጀለኛውና ከርሱን በንጹሃኖች እንግልት ሲሞላ የነበረው ሰው የተቃዋሚዎችን መድረክ ከፊት ሆኖ ያሾረዋል። ”ጃስ!…” ይለዋል። እንደትላንቱ አስራ አራትም ሃያ አንድ ቀን ባይጠይቅብንም በተነጠፉለት ”እርጥብ ቁርበቶች” ያስገላምጠናል። ይገላምጠናልም። ”ጅብ ባልታወቀበት ሃገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ….” አለ የሚሉት ያበው ተረት ህይወት ዘርቶ መለ – መላውን ለመመልከት ተገደናል። ለዕውነት መስዋዕትነት የከፈሉትን ዳኛ ወልደሚካኤልን፣ ብርቱካን ሚዴቅሳን በየመድረኮቹ ባናያቸው የማይገርመን ለዚህም ይሆናል።

«በሰነፎች መካከል ከሚገኝ የገዥዎች ጩኽት ይልቅ የጠቢባን ቃል በጸጥታ ትሰማለች።»

በጸጥታቸው ውስጥ የምንሰማቸውን ከላይ ለመነካካት ሞክሬያለሁ። ደፋሮች፣ታታሪዎች፣ለሃገራቸው ቀናኢ አመለካከት ከግንዛቤ ጋር ያላቸው ብዙ ኢትዮጵያውያኖች አውቃለሁኝ። አንቱ የተባሉ የሃሳብ ጎምቱዎች። በዝምታቸው ውስጥ ጩኽታቸው የሚሰሙ ደጀኖች። በአንጻሩም ሆዳሞች፣ ፍጥጥ ያሉና ይሉኝታን የማያውቁ፣ ትላንትና ገድለው፣ አስረው አንገላተው ያልረኩትን እነ ካሳሁን አድማሱ የዛሬው ዳንኤል አበበ ዓይነቶችን ማየት የዲያስጶራ የዕለት ተዕለት ውሎና አዳር መሆኑ አይገርምም። የምተርክላችሁ ይሁዳ ባሁኑ ወቅት በ”ኖርዌይ የዲሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያ” ሊቀመንበርና በነገው ዕለትም በሚካሄደው የኢትዮጵያውያኖች ማህበር አስመራጭ ኮሚቴ ሆኖ የሚሰየመውን ነው። የሚያውቁትም፣ የማያውቁትም ”ወገኖች” ብብታቸው እስኪታይ ድረስ እጃቸውን ያወጡለታል። ጓንቶቻቸውን አውልቀው ያጨበጭቡለታል። ”ሰውየው ይሄ ነበረ” የሚለው ጥቆማና የወገን መረጃን የሚያናንቁ ፈቅደው የተነጠፉ ‘ቁርበቶች’ ሊሆኑ ይችላሉ። ውሃ የሚያነሳ መረጃን አናንቀውታልና። ምክንያቱም በሰነፎች መካከል የተገኘ ገዥ ሆኗልና። ጲላጦስ ክርስቶስ ላይ ከመፍረዱ በፊት ”ምን ላድርገው ይሄን ሰው? ሲላቸው” የጯሂዎች ጩኽት እንደበረከተው ሆኗልና። ለዚያም ነው በርባንን ፈትቶ ክርስቶስን የሰቀለላቸው።

በሃሳብ ወደኋላ – የማልቀርበት ስብሰባ

እንደ ስሙ ታማኝ የሆነው ታማኝ ወደኖርዌይ የመጣው ለህዝብ ዓይንና ጆሮ የሆነውን ኢሳትን ለመታደግና ከነዋሪው ጋር ለመወያየት ነበረ። ቀደም ባሉት የተለያዩ የህዝብ ውይይቶች ላይ እንደዜጋም እንደጋዜጠኛም መሳተፌ ‘እኔ‘ ‘ህሊናዬ‘ና ሙያዬ ”በል” ሲለኝ ነው። ”ሙድ ይበልጣል ከፉድ” እንዲሉ ”ሙዴ”ን እመለከታለሁ። ”ሙድ” ሲተነተን ያሰቡትን፣የፈቀዱትን መሆን ነው። የግል ነጻነት ነው። የግል ግፊት ነው። ያ እኔ ነኝ። ታማኝን ማየት፣መስማት፣ማድመጥ ማጀብ ከ”ሙድም” በላይ ነው – ለኔ። የአቋም ሰው ነውና፣አክብሮትም ፍቅርም ቢኖረኝ ለሃገር የሆነውና የሚሆነውን ስለማውቅ ነው። በኢሳት ዝግጅቶች ላይ መገኘት የሙያ አጋሮቼን በዓይነ – ህሊናም በአካልም የማግኘት ያህል ስሜት በውስጤ ይፈጠራል። ባንድ ቢሮ ውስጥ አምሽተን፣ ያነጋንባቸው ክፉም– ደግም ውጣ – ውረድ ያሳለፍናቸው የነጻ ፕሬስ ሰዎች በውስጡ የታጨቁበት አካልና ”ኢንስቲቲዩሽን” ነው። እንዲህ ያሉ ስብስቦች ላይ በስፍራው ብገኝ እንጂ ብቀር አረካም።ስለዚህም በቦታው ተገኘሁ።

አንድ አጭር ወደመነጋገሪያው ስፍራ ቀረበ። የ”ዲሞክራሲያዊ ለውጥ…..”ሊቀመንበር አቶ ዳንኤል አበበ ተሰኝቶ ነበር የቀረበው። ዓይኔን ብረቱን ተጠራጠርኩ። ይህን ክቡር ስፍራ በሰጡት ሰዎች አዘንኩ። ሁለት ቃላቶች ከቆመበት ”ስታንድ” ላይ ሲናገር በዓይነ – ህሊናዬ ከኖርዌይ አዲስ አበባ ቀጨኔ አራዳ ፍርድ ቤት መጠኩኝ። ”…የተከበረው ፍርድ ቤት በዚህ በታማኝና በተቀሩት ተከሳሾቼ ላይ መረጃዎቼ ሊጠፉ ሲለሚችሉ የሃያ አ ንድ ቀን ቀነ – ቀጠሮ ይሰጠኝና በእስር ቤት ይቆዩልኝ” የሚል ንባብ የሚያነብም መሰለኝ። ከተቀመጥኩበት እንዴት እንደተነሳሁና እንደወጣሁኝ አላውቅም። ስብሰባውን ጥዬ ወጣሁኝ። ወጥቼ ሲጋራ አ ቀጣጥዬም ይሁን እኔ ተቀጣጥዬ አላስታውስም። ቆሽቴ ግን ለራሴ ይሸተኝ ነበር። ‘ወይ – ነዶ‘ አልኩኝ። እንዲያ ሆኜ ነበር ወደቤቴ ያመራሁት። ”የተፈጥሮ አንጎልህ ሊሸከመው ከሚችለው በላይ የሆነውን ነገር በተጨማሪ አንግሎልህ መዝግበው…” እንዲሉ የተሰማኝን ስሜት ማስታወሻዬ ላይ አሰፈርኩት።

ምን ማድረግ ነበረብኝ?

ለሚመለከታቸው ሁሉ መነገር ነበረበትና የትላንቱ ካሳሁን አድማሱ አበባው የዛሬው ዳንኤል አበበን ማንነት እንደዜጋም እንደጋዜጠኛም ለሚመለከታቸውና በአመራር ላይ ለሚገኙት ለመግለጽ ሞከርኩኝ። ”ከወያኔ መረጃ የሚያመጣልን ታላቅ ሰዋችን ነው ተባልኩኝ። ቁልፋችን ነው አሉኝ። ጅቡ ብዙ ቁርበቶች እንዳገኘም ተረዳሁኝ። ከበቂ በላይ መልስ አገኘሁኝ። በሃሳቤ ”ይሁዳ” ቢመላለስብኝና ብከትበው ይሁዳ የዋህ ሆኖ አገኘሁት። የሰበሰበውን ዲናር መበተኑንና መሰቀሉን አወቅሁኝ።የይሁዳን ምግባር ሳሰላስል ”ነፍስ ይማር!” ለማለትም ዳዳኝ።
ጥያቄ አንድ። ወያኔዎች የነሱ የሆነ አቃቢ ህግ ለዚያውም መሪ ተዋናያናቸውን ስሙን ለውጦ በየመድረኩ ሲንጎራደድ ለምን ዝም አ ሉት?
የኔ መልስ። አብሮአቸው ስለሚሰራ።ሌላ ምንም ሊሆን አይችልም። ገና ድሮ ”ትግራይ ኦንላይን” ወይም ”አይጋ ፎረም” ላይ እንመለከተው ነበርና።

1.«ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ሞኝ ነሽ ተላላ
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ» የጎጃም ህዝብ

2. «ዕውነትን ለመናገር አትፍራ። ሃሰትን ለመናገር አትድፈር።» መጽሃፍ ቅዱስ

1.1 በቀድሞው የቅኝ ግዛት ትግል በላይ ዘለቀ ጀግና ነበረ። ትልቅና ከመጀመሪያው ረድፍ ላይ የተሰለፈ ጀግና። የቅኝ ግዛቱ ወረራ በድል በተጠናቀቀ ማግስት ጀግና የተባለው በላይ ዘለቀ በተከበረበት በተወደሰበትና ባስከበራት ሃገር መሪ በስቅላት እንዲሞት (እንዲቀጣ) ተደረገ። ጉዳዩን መንገር ለቀባሪው ማርዳት ይሆናልና ተውኩት። የጎጃም ህዝብም ለትውልድ የሚተርፍ ተረት በጩኽት ሳይሆን በውስጡ አጉረመረመ። በዝምታው ውስጥ የተሰማው ጩኽት ተረት ሆኖ ለትውልድም ተርፎ ይሄው እኛም እያልነው ነው «ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ሞኝ ነሽ ተላላ ….. የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ።»

2.1 በራሳቸውና በግላቸው ህሊናና ዕውነት የሚተማመኑና የሚተገብሩ ሰዎች ሁልጊዜም የሚፈሩት ፍርሃትን ብቻ ነው። ዕውነትን ለመናገር ከርሳቸውን አያስቡም። እዚህ ዓለም ላይ እራቁታቸውን እንደመጡና እራቁታቸውን እንደሚሄዱ ያስተውላሉና ስለዕውነት ይኖራሉ። የሚተኙትም እንቅልፍ ውብ ነው። በዚህ ውስጥ እስክንድር ነጋ የኔ ምሳሌ ነው። እስክንድር ነጋን የምወደው በመታሰሩ አይደለም። ለዕውነት የሚከፍለው መስዋዕትነትና እየከፈለ ያለው ዕውነት ጥግ የለውም። እስክንድር ምሳሌ ነው። የዕውነት አለቃ። የድፍረት ንጉስ። «ዕውነትን ለመናገር አ ትፍራ። ሃሰትን ለመናገር አ ትድፈር።» ሲተነተን እስክንድር ነው።

አበቃሁ ኢሜሌ ይሄውላችሁ:- girma077@gmail.com

LEAVE A REPLY