አማራ በብሄር ስለመደራጀት ምላሽ በፌስ ቡክ ገጿ /ፍቅርተ መሰረት/

አማራ በብሄር ስለመደራጀት ምላሽ በፌስ ቡክ ገጿ /ፍቅርተ መሰረት/

ሰሞኑን በተክለሚካኣኤል አበበ የተፃፈ፣ በአማራ በብሄር መደራጀት ላይ ያለውን ትችት የገለጸበት አርቲክል አነበብኩ። ከትችቶቹ ውስጥ፣ የኢትዮጵያን ህልውና አደጋ ለይ የጥላል፣ እኛን (ከአማራ ክልል ውጪ የተውለዱ/የሚኖሩ አማራውች) አጣብቂኝ ውስጥ የከታል—ይህን ጹሁፍ ተከትሎ፣ አቻሜለህ ታምሩ በፌስቡክ ገጹ ላይ በሰጠው መልስ፣ ተክለሚካኣኤል ያነሳችው ትችቶች መሰረተ ቢስ እና አማራው ለምን እንዲደራጅ እንዳስፈለገ ካለመረዳት የመጣ ነው ካለ በሆላ፣ አማራ የሚደራጅበትን አላማ እንደዚህ ገልጸታል።

“የአማራ ክልል ኢትዮጵያ ናት። አማራ የሚደራጀው ወያኔ ባበጀለት አጥር ለመታገት ሳይሆን በሰፊዋ ኢትዮጵያ ያለ ገደብ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን እኩል እንደሰው ተከብሮ ለመኖር ነው። የአማራ መደራጀት ግብ ይህ ነው። ከዚህ የተለየ ፍቺም ሆነ ትርጉም የለውም።”……………….”የአማራ የሚደራጀው ስለዚህ ቅዱስ ተግባር ነው!” ግን በርግጥ፣ እያየናቸው ያሉት የአማራ ድርጅቶች፣ አቻሜለህ የመሰከረላቸውን የቅድስና ተግባር እየሰሩ ነው ውይ? በስፋት ማህበራው ሚዲያው ላይ ያሉትን ቤተ-አማራን እና ዳግማዊ መዐሕድን ብንፈትሽ፦

ቤተ-አማራ፡ በግልጸ ጽንፈኛ አማሮች አንደሆኑ እና የአማራ መንግስት ለማቁቁም የሚሰሩ መሆናችውን የሚናገሩ ናችው።
ዳግማዊ መዐሕድ: የነዚህ ፖለቲካ አቁም ደግሞ (ኢሳት ላይ ከአመራሮቹ የሰማሁት)፣ የብሄር ፖለቲካ አሽንፎል፣ ኢትዮጵያ እየተበታተነች ነው፣አማራም ወደ ቤቱ መሰብሰብ ይሻለዋል፣ ሁሉንም የሚያሳትፍ መንግስት በድርድር የሚመሰረት ከሆነ፣ አማራን ወክለን ያኔ እንሳተፋለን የሚል ነው። ማን ያን መድረክ አዘጋጅቶ እንዲጠራቸው እንዳሰቡ ግልጽ ባየሆንም።

እነዚህ ድርጅቶች፣ በተግባርም ህዝብ ለህዝብ ለማቀራረብ፣ ጥርጣሬን ለመቀነስ እና መግባባት ለመፍጠር የሚያደርጉት እንቅስቃሴ አይታይም። የባሱኑ፣ የአማራውን የነጻነት ትግል ከሌላው ህዝብ ትግል ነትሎ የማቅረብ፣ ህብረብሄር የሆኑ ተቆአማት እና የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ጠብ የመፍጠር አዝማምያ የታይባችዋል። በዚህ አካሄድ አማራ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር በኩልነት የሚኖርባትን ሀገር ለመገንባት እንዴት የችላሉ?
አቻሜለህም እራሱም ቢሆን ፣ OMN ላይ፣ ተስማምተን መኖር ካልቻልን፣ እንደመጨረሻ አማራጭ ጥሩ ጎሮቤት ሆነን መኖር የምንችልበትን ሁኔታ አስባለሁ ሲል ሰምቸዋለሁ። የጋራ ሃገራቸውን ተስማምተው ማቆም ያቃታቸው ህዝቦች፣ ተገነጣጥለው ጥሩ ጉርብትና ሲፈጥሩ በየት ሃገር እንዳየ እሱ ያውቃል። የአቻሜለህ ጥሩ ጉርብትና ቲውሪ ተሳካ ብንል እንኩአን፣ ተክለሚካኣኤል እንደ ሰጋው፣ ነጌሌ ቦረና የተወለደን አማራ፣ በገዛ ሃገሩ ዲያስፖራ ያደርገዋል። ጎጃም የተውለደውን ደግሞ ሃገር ያሳጣዋል። አያድርገው እና ኢትዮጵያ የመከፋፈል አደጋ ቢገጥማት ግን ሁላችንንም የሚጠብቀን ከዚህ እጅግ የከፋ፣ በደንበር እና በጥቅም ግጭት የተነሳ ለሚፈጠር የርስ በርስ ጦርነት፣ አልፎም ለውጭ አሽባሪ ሃይሎች ጥቃት ተጋላጭነት ነው።

ለአማራውም ሆነ ለተቀረው ኢትዮጵያዊ የሚያስፈልገው ፓለቲከኛ፣ ጥብቅ ትስስራችን እና የተጋረጠብንን አደጋ በምላቱ የተረዳ፣ ያለ ምንም ወለም ዘለም፣ መፍትሄው በኢትዮጵያ መአቀፍ ውስጥ፣ ለሁሉም ዜጋ እና ማህበረሰብ የሚሆን ዲሞክራሲያው ስርአት መዝርጋት ነው ብሎ የሚያምን፣ ለዛም ማንንም ሳየጠብቅ፣ ሃላፊነት እና ተነሳሽነት ውስዶ የሚሰራ ነው።በዚህ መልኩ የሚንከሳቀስ የአማራ ድርጅት እስካሁን አላየሁም።እንዲህ አይነት የአማራ የፖለቲካ ድርጅት የመፈጠር እደሉም አነስተኛ ይመስለእኛል።ለምን? አንዲህ አይነት አቁዋም ያልው አማራ ምርጫው ህብረብሄር አደረጃጀት ስለሆነ።

LEAVE A REPLY