እንኳን ለገና አደረሰን /አሰፋ ጫቦ-ከዳላስ ቴክሳስ/

እንኳን ለገና አደረሰን /አሰፋ ጫቦ-ከዳላስ ቴክሳስ/

የፈረንጅ ገና ዋዜማ ለት በሆንኩት ልጀምር።ሁለት ወዳጆቼ፤አንደኛው ከዚሁ ከቨርጂኒያ ፤ሌላው ከሳሳከችዋን፤ካናዳ ደውሎ ስለበእሉ ትንሽ ተነጋገርን። እነሱም የሚሰማቸውን እኔም የሚሰማን ያዝ ለቀቅ አደርገነው። “ዞር ዞሮ ከቤት!” እንዲሉ ያው ሁሌም  ሚዛኑ የኢትዮጵያ አመትበአላት ናቸው። “ባሻ አሸብር ባሜሪካ “መሆንናችን መስለኝ።

ከካናዳ የደውለው የቁጫ ልጅ ነው። ቆጫ ጋሞ ውስጥ አንድ ወረዳ ነው። እኔ እስከማውቀው ዝነኛነቱ በቅቤ ነበር። አሁን ፤በዚህ “ዙሪያችሁን አጥር እጥራሩና ተካለሉ” በተባለው መሠረት ይመስለኛል “እኛ ቁጫ እንጅ ጋሞ አይደልንም!” አሉ ተባለ። ያ እንደፍጥርጥሩ! እኔ የገረመኝ አምና ይሁን ሀች አምና  ፤አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ “ቁጫ የራሱን እድል የመወሰን መብቱ መከበር አለበት!” የሚል ጽሁፍ አንድ ሁለት ይሁን ሶስት ጊዜ ያነበብኩ ይመስለኛል። ያንን ጽሁፍ አቅራቢ ደግሞ “አገር አቀፍ ፓርቲ” ተብሎ ከተመዘገቡትና ተቃዋሚ ድርጅቶች ከሚባሉት ውስጥ አንዱ ነበር። ተለዋጭ አስተያየት አልተሰጠበትምና የሚቃወሙት ያው ወያኔን ነው ብዬ አስባለሁ። አገር ሁሉ የሚቃወመው፤ ወይም ከሚቃወማቸው የወያኔ ፓልቲካ ዋንኛው “ይህንን በብሔረሰብ ከፍሎ  ማባሉትን አቁሙ!” ነው። አገር አቀፍ ፓርቲ ይህንን ሲደግፍ ደግሞ  ነገረ አለሙ አልገባኝ ይሆን? ወደማለት ወሰደኝ። ምኑን እንደሚደግፉ፤ምኑንስ እንደሚቃወሙ አልገባኝም ለማለት ነው።በዚህ አጋጣሚ አስታወሰኩት።

ከነሱ ጋር ዝርዝር ውስጥ አልገባንም እንጄ እኔ ይህንን የፈርንጅ በአላት፤በተለይም ሕይማኖት ነክ የሆኑትን መንፈሴ አልተላበሰውም::ሙሉ ለሙሉ አልተላበሰውም ማለት ይሻላል። ምርቄን አ ጣጥሜ ከዋጥኩ በኋላ ከአገሬ ስለወጣህ አዲስ ስር ማቆጥቆጥ አልቻልኩምና ሊሆን ይችላል። ይህ አንደኛው ምክንያት ቢሆንም ሌሎችም የሚያጣ አይመስለኝም።

ለምሳሌ ያክል የህንን የገና በዓል እንውስድ።  ፈርንጅና ተከታዮቹ የሱስ ፤እስልምና ተከታዮች ኢሳ ፤ኢትዮጵያዊያን ደግሞ እየሱስ የሚሉት  ልደት ነው። በየትኛውም ቅላጼ ይጠራ እየሱስ እናት አለው ማለት ነው። ልደት የተባለው “ተወለደ!” ለማለት ነውና!  እናቱ ደግሞ ማርያም ነች ። ኦርቶዶክሶቹ ”ድንግል በሕሊናክ ወድንግል በሥስጋኪ!” ይሏታል። ሐዋሪያው ሉቃስም  በወንጌሉ ምዕራፍ አንድን ለማርያም ብቻ ያደርገዋል።  ተራ-ተርታው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተከታይ(The average laity) ማርያምን እንደቤተሰብም ፤እንደጎርቤትም፣ሲበዛም በግል እንደሚያውቋት አስመለው ሲጠሯትና ሲያሞካሽዋት ማየትና መስማት የተለመደ ነው። በዚህ ውስጥ ያደገው አሌክስ “ደብባዳቤ  ለእግዜር!” በሚለው ግጥሙ መደምደሚያ  ላይ :-

“ኧረ እግዜር በናትህ በጭንቅ አማላጇ

ባዘለህ ጀርባዋ ባቀፉህ እጆቿ

ወይ ዝናብ ላክልን ወይ ዝናብ ሁነህ ና

ሙቀት ገደለና!”ይላል።

አባ ህርያቆስ የሚባሉ መንኩሴ ደግሞ “ጎሣ ልብዬ ቃለ ሠናዬ!” የሚል የማርያም ቅዳሴ ደርሰዋል።ቅዳሴ ምስጋና ማለትነው።ቀደሰ አመሰገነ ነውና!ሶርያዊ ሳይሆኑ አይቀሩም። እኔ አልፎ አልፎ“ጎሣ ልብዬ”ን   አዳምጠዋለህ።የድርስቱ ጥልቀትና ምጥቀት የገረመኛል!

ማርያምም በዚሁ በሉቃስ ምዕራፍ አንድ ውስጥ “ከእንግዲህ ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑኛል”ትላለች። ትውልድ ስትል የሰው ዘር ሁሉ ማለት ባይሆንም ክርስቲያን የሆነውን ሁሉ ማለቱ ይመስለኛል። ከሆነም ደግሞ ፈርንጁም እዚያው ትውልድ የሚለው ውስጥ ይጠቃለላል። ካልተጠተቃለለ ደግሞ ትውልድ አይደለንም ማለታቸው  ይሆን? ወይም የሉቃስን ወንግል ምዕራፍ አንድን አላየንም !አልሰማንም !ማለት ይሆን ? ፈረንጅ በማርያም አካባቢ ድርሽ አይልም!ካቶሊኮችንአይጨምርም።ነገሩ “ማን ይመራመር!?” ውስጥ የሚገባ መስለኝ።

አንድ ቀን “ክርስትና በአሜሪካ!”የሚል መፃፌየሚቀር አይመስለኝም።  ይህ ሁሉ ንገርን ነገር ያነሳዋል በሚል እንጅ እምነት ውስጥ ገብቼ ለመዘባረቅ አይደለም። ልገባ እንኳን ብፈልግ እዚያ የሚተራመሰው፤የሚያተራምሰው ብዙ ስልሆነ ክፍት ቦታ የማገኝ አይመስለኝም።

*****

ከውዳጆቼ ጋር ስልኩን ከዘጋሁ በኋላ አንድ ቦታ ለመሔድ Malcom X ና Baylor Hospital  ያለው ባቡር ጣቢያ ቆሚያለህ። የባቡሩ ጣቢያ መነፋሻም(Park) ጭምር ያለው ስለሆነ አልፎ አልፎ መናፈሻው ውስጥ ተቀምጬ አነባለሁ ወይም እቆዝማለሁ። ዛሬ የለውትሮው ጭር ብሎ ነበር።

እንደቆምኩ  SUB አንድ ትልቅ ፈረንጅ የሚንዳውና አጠገቡ የ15 አመት የሚሆነው ወጣት የተቀመጠበት ፊት ለፊት ቀጥ ብሎ ቆመ። በኔ በኩል ያለው ወጣቱ ነው። ፊቱ ላይ ፋገግታ አለው። መስኮቱን ከፍቶ እጁን ወደኔ ዘረጋ። ገርሞኝ ልጨብጠው እጄን ስዘረጋ በጁ የያዘውን ሰጠኝን። የሰው እጅ ያልነካው ሁለት ባለ$20 ነው። አልተዘጋጀሁበትና እንኳን አደረሳችህ(Merry Chistmas) የመሳሰለውን ስል ጉዙፉ አባት ወይም አያት ወጥቶ አቀፎ እንኳን ለገና አደርሰህ (Merry Chirstmas) ተባባልን። ብዙ ጊዜ አይቸው የማላውቀው አዲስ ከፓኮ የወጡ፤የዚህ አካባቢ የማይመስሉ ፈረንጆችነበሩ!

*******

ከሰአት በኋላ የህንን ለልጆቼ ለእመቤት አስፋና ለቡርቱካን ሚደቅሳ ነገርኳቸው።ለእመቤት ደውዬ ነው። ቡርቱካን “እንኳን አደረሰህ !”ለማለት ደውላ ነው።ሁለቱም ተቀራራቢ መልስ የሰጡኝ ይመስለናኛል።አንተ መንፈሴ አልተላበሰውም ስትል የኸው “ውዴት ገሽሽ  ገሽሽ !ብሎ መልእከተኛ መጣብህ የሚል ቃና ያለው መስለኝ። ከሆነ ደግሞ “ማን ይመራመር?”አይነትሊሆን ነው

“ማን ይመራመር፤ማን የመራመር፤

ያንተን ሥራ ያየንተን ግብር፤ማን የመራመር?” ይላል መዲናና ዘለሰኛው።

እኔም እስማማለህ! ብቻ የህንን “የንተን ሥራ !ያንተን ግብር !ማን ይመራመር!?” የሚለው አንድምታም ያለው ይመስለኛል። በአንድምታው ከሔድን ደግሞ “ያንተ ሥራ !”የሚለው ፈጣሪን ማለት ሳይሆን፤ወይም ፈጣሪን ብቻ ማለት ሳይሆን ተፈጥሮን ብሎ መተርጎም የሚቻል ይመስለኛል። ተፈጥሮ አምቃ የያዘችውን ምስጢር ለማዋቅ ጥረቱ ገና በሩን በማንኳኳት ላይ ያለ ይመስላል። እና ልጆቼ ያሉትን በዚያ ትርጉም ጭምር ተቀብያለሁ ለማለት ነው።

*****

ሌላው የዚህ ስሞን ዜና “ከፍተን ብናየው!  የኢሳይያስ አፈወርቂና የኦንግ መስተፋቅር” ብዬ ያጻፍኩት በየድረገጹም በአዲስ አድማስም ወጥቶ ነበር። አንዱ በራዲዮም ያነበበውን በUtube ለጥፎ ነበርና ይህንን በምጽፍበት ጊዜ 148,000 ሰው አዳምጦታል ይላል። ይህ Facebook ፤በአዲስ አድማስና በድረገጻት ያነበበውን ሳይጨምር ማለት ነው። እንደሚነገረኝ ከአንባቢዎችና አድማጮች ውስጥ ብዙ ኤርትራውያን እንዳሉበት ነው።ይ ህ፣ለኔ፣ ማህበራዊ ገጽ የሚባለው የሚሰራውን ትንግርት የሚነገረኝ ነው።

የማሕበራዊ ገጽ ነገር ከተነሳ አይቀር ኢትዮጵያ ለተሰኑ ወራት ተዘግቶ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትራቸው አቶ ደሳለኝን ኃይለማርያም  የማሕበራዊ ገጾች አደገኝነት ለተባበሩት መንግስታት አባላት አገሮችም ያስርዱት መስለኝ።

አቶ ደሳለኝኃይለማርያም እውነታቸውን ነው።ሊፈሩትም ሊዘጉትም ተገቢ ነበር! በአንጻራዊ አመለካከት ማለቴ ነው። ይህንን አረብ ጥቢ! Arab Spring  ያተባለውን ፤ከጥቂት አመታት በፊት ብዙ መሪዎችን ያናወጠው ትዝ ብሏቸው ሊሆን ይችላል። የቱኒዚያው የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዚን ኤል ኣብዲን በን አሊ ዛሬ በሕወት አሉ ወይስ እዚያው  ሳኡዲ እንደተወሸቁ ናቸው ? የግብጹስ ሁሲን ሙባረክን በወያኔ ቋንቋ “ከራይ ሰብሳቢዎች”፤ማለትም ዘራፊዎቹ ዛሬ የት ነው ያሉት?

አሁን ወደጦሴና ጥንቡሳሰ ልግባ

ፕሮፌር አየለ በከሪ አንድ የግእዝ ማእከል የገበኘውን CNN ታሪካዊ ብሎ አቀረበው። እኔ፤ያንን Utube በFacebook  ግርግዳዬ ላይ ለጠፍኩት። ብዙ ወዳጆቼ ጎበኙት! አደነቁ አስትያየትም ሰጡ! ከነዚህ ውስጥ አንዱ፣ ዳግማዊ ተሾመ የተባለ” ባይሆን አርፈህ ስለጨንቻ ብትጽፍ አይበቃህም?” የሚል አስተያየት ሰጠ።ሁለትየጥያቄ ምልክትም አድርጓል። የFacebook  ጥሩነነቱ” ወዳጅ Friend” መስሎ የመጣውን “ቅርብኝ  (Unfriend)ማለት ሴኮንዶች ነው የሚወስደው። በዚህ መሠረት ዳግማዊ ተሾመን “ቅርብኝ!” አልኩት።

ሳሰበው ሰሙ አይመስለኝም። የዚህ አዲሱ  Facebookላይ ከተፈለፈሉት” የአማራ ነጻ አውጭ!” ነን ክሚሉት፣ወደዘመነ ማሣፍንት ተጓዦች አንድ ሳይሆን የሚቀር አይመስለኝም።” ግዕዝ የኛ ነውና ለአንተ ምንህ ነው?” እንደማለት። “የአ ክሱም ሐውልት ለዎላይታው ምኑ ነው?” እንዲል መለስ ዜናዊ። ክ2009  እስከ 1855  ዘመነ መሣፍንት ድረስ መጓዝ አልችልምና ዳግማዊ ተሾመን “እዚያ  ይሙቅህ!” ብዬ አስናበትኩት።  ተክኖሎጅ ጥሩ ነገር! ወጣ ውረድ ይግባኝ የሌለበት!

****

ሌላው በዚህ “ከፍተን ብናየው..!”ብዬ በጻፍኩት ላይ አንዱ “ሽማግሌና ሕጻን አንድ ነው!” የሚል አስተያየት ሰጠ። “ቅርብኝ(Unfriend)” ልበለው አልበለው ስል ብዙዎች መልስ ሰጡበት። አንደኛው አረካኝ። “ልክ ነህ! ሸማግሌና ሕጻን አንድ ነው! ልክ እንደረወረደ እውነቱ ይናገራል!” አለ። ይህን አይቼ “ቅርብኝ!” አላልኩትም።

****

የፈረንጅ አዲስ አመት ዋዜማ ዘወተር ቅዳሜና እሁድ እንደማደርገው ፕሌኖ(Pleno) የምትባል ከተማ ለመሔድ ባቡር ተሳፈርኩ። እዚያ ሰውም አገኛለሁ።ጋዜጦችም የማገላብጥበት መጽሐፍት ቤትም ቁጭ ብዬ የማነብበት Starbucks አለ። አንድ የማነበው The Orgin of Amharic  የሚል የዶክተር ግርማ ደመቀን መጽሐፍምይዣለሁ። ከባቡሩ ስወርድ ረስቼ ወረድኩ።  ሁለትን ይሁን ሶስት ወር ሙሉ አንዴ በብጫ ሌላ ጊዜ በሰማያዊ ሳቀልመው(Highlight)፣አናቱ፣እጎኑና ግርጌው ላይ ሁሉ ስጽፍበት የከረምኩት ጠፋ! ጠፋ! ። ዶክተር ግርማ ዛሬ እልክለሐልህ ብሏል።

ይህንና ይህንን ነው” ጦሴን ጡቡሳሴን ይዞት ይሕድ! ያልኩት

ማሳረጊያ

ከዚህ ከረዘመ “እንኳን አደረሰን!” ሳይሆን ንዝንዝ የሚሆን መስለኝ! ለዘንድሮ ገና ይኸው ይብቃና!

“ገና” ላልቶ ሲነብብ “ገና!” ማለትም ነው። የተሻለ ነገም አለ ማለት ነው!

ለተሻለ ነገ ያብቃን!

ከፋፋዮችን፤ከሐህዲዎችን፤ያትንንልልን! ያብንልን!

ኢትዮጵያ በነፃነትዋ ለዘለዓልለም ትኑር!

LEAVE A REPLY