እንደ ሳውዝ አፍሪካ እንስሶች በማያጌጡበት ህንጻ ከመታበይ ከነሙሉ ኩራታችንና በደሃ ጎጇችን መኖራችን የሚያኮራን ለምን እንደሆነ ሰሞኑን የነጻነትን እረሃብ አጋዚ ከቆፈረው የሞት ሸለቆ ያልተማሩት የሚሊኒሊክን ወጭት ሰባሪ ድኩማኖች ባይናቸው ብሌን እያዩት ነው ብለን ተስፋ እናደርጋለን። አፍሪካውያን በባሪያ ፍንገላ ውስጥ ኖረዋል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ የነርሱ ዝርያዎች ዛሬ ባህር ተሻግረው በነጭ ምድር አንገታቸውን ደፍተው “እኔ እከሌ ነኝ” ሳይሉ ይኖራሉ።
ሌላው ቢቀር መልካቸው በጣም ጠቆረ በሚል ምክንያት ከእስፔና ከፈረንሳይ አገር ከተጋዙ ነጭ እስረኞች ጋር በግዴታ እንዲዳቀሉ በመደረጋቸው ዛሬ በላቲን አሜሪካን ያሉት ወልጣቀኝ መልክ ያላቸው ህዝቦች የተፈጠሩበት ኩነት በጥቁሮች ላይ ሳይሆን በጥቁርነት ላይ የተፈጸመ ጀንፕሳይድ መሆኑ መራሩ እውነታ ነው። አንድ ጥቁር አሜሪካዊ እኔ አፍሪካን አሜሪካን ነኝ የሚለው አንድም ቋንጃውን ተቆርጦ ባህር ማዶ የተጔዘው ምንጅላቱ ከየትኛው የአፍሪካ አገር እንደተወሰደ ቆጥሮ ሊደርስበት ስለማይችል ነው።ደረትን ነፍቶ ኢትዮጵን አሜሪካን ብሎ ለመናገር ማንነት ካለው አገር በክብር መሄድ ይጠይቃል። አባቶቻችን ምስጋና ይግባቸውና ዛሬ እነ ጃዋርን ጨምሮ የባንዳዎቹ ልጆች ሳይቀሩ ማነህ ቢባሉ ማን መሆናቸውን፣ አያት ቅድማያት እንዳላቸው፤ ኮራ ብለው በአውሮፕላን ቀበቷቸውን አስረው የመጡ መሆናቸውን ማሰብ የሚችል ተፈጥሮ ካላቸው ይኽ ማንነት በምን ላይ የቆመ መሆኑን ቢያስቡት አይከስሩበትም። ዛሬ አጠገባቸው ያሉት ጥቁሮች እረፍት ቢያምራቸው ተሳፍረው የሚዱበት አገር፤ “ወገኔ; አመት በአሌ” ብለው የሚናፍቁት ማንነት የሌላቸው ናቸው::
አፍሪካውያን እንደ ማህበረሰብ ከቆሙበት ግዜ ጀምሮ መጀመሪያ በባሪያ ፍንገላ ዋጋ ከፍሉ። ባሪያ ፍንገላው በአዋጅ ተሻረ ሲባል መልኩን ቀይሮ በበርሊን ኮንፈረንስ አህጉሪቱን ኮሎኒያሊዝም ብለው እንደ ቅርጫ ስጋ ለመቃረጥ ተስማሙ። ድርጊቱም የሆነው በአስራ ስምንት ሰማንያ አራት ሲሆን ይኽ በሆነ በአስራ ስምንት አመታት ውስጥ ነጻ ሆና የቀረችው አንዲት አገር ኢትዮጵያ ነበረች። አፍሪካውያንን ሊግ ኦፍ ኔሽንን በመሳሰሉ አለማቀፍ መድረክ ለዘመናት ስንወከል የኖርን እኛ ነን። ከፓን አፍሪካኒዝም የተወለደው የአፍሪካ የነጻነት ጥያቄም እርሾው የአድዋ ድልና ከምስራቅ አፍሪካ የተነሳው የነጻነት ችቦ ነው። ስለዚህ እነርሱ የባርነት ጭራቃዊ ገጽታ አጥንታቸው ድረስ ዘልቆ የገባባቸው ቁስለኞች ናቸውና ባንዲራችን ባንዲራቸው የነጻነታቸው ምልክት አደረጔት እንጅ እንደ ዛሬዎቹ የኛ አገር ለምጻሞች አላፈሩበትም ወይንም በሶ አልቋጠሩባትም።
ዛሬ በእኛ አገር እንደ ኬንያ ኳኩዩ ኪሮስ የሚለው ማንነቱ ክርስቶፈር፣ ቶሎሳ መባሉ ቀርቶ ስቴፈንሰን የተባለ ሰው የለም ስንል እንዲሁ በነጻ ያለዋጋ ተጠብቆ የቆየ ነገር አይደለም:: ከኮሎኖያሊዝም ወደ አፓርታይድ ከአፓርታይድ ደግሞ የነጻነት ትግሉን ግማደ መስቀል መሸከም ወደተሳናቸው መጹጉዎች እጅ ወድቆ ከማንነቱም በታች ሰብአዊነቱ የተወሰደበት የሳውዝ አፍሪካ ህዝብ ቆንጨራውን ይዞ አደባባይ ቢወጣ፤ የአንድ ምስኪን አንገት ለመቁረጥ አጃቢ የሙዚቃ መሳሪያ ሲያስፈልገው ብናይ ምን ይደንቃል?! ወትሮም ነጮቹ ሲገዙዋቸው ከሰውነት በታች አውርደውና ሰብአዊነታቸውን ገፈው በራቁት ህሊና የለቀቋቸው ሆነዋልና የሚገርመን አይሆንም። ማንም አባቶቻችን የከፈሉትን ዋጋ መልኩን ለማየት የሚፈልግ ቢኖር በዚህ ሰአት በጆሃንስበርግ; በፕሪቶሪያና በደርባን ከተሞች ዘወር ዘወር ይበል።