ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ዕውቀት መለዋወጫ መረብ
የትግሬ ነፍጠኛ፣ የሸዋ ፈረሰኛ፣ የጎጃም እግረኛ፣ የአማራ ስልተኛ ከብ ይቀላው፣ ያናፋው፣ ያንደገድገው ጀመር። ከእንዝርት የቀለለ የጁየ፣ ከነብር የፈጠነ ቤጌምድሬ፣ ከቋንጣ የደረቀ ትግሬ፣ ከአሞራ የረበበ ሽዌ፣ ከንብ የባሰ ጎጃሜ እያባረረ በየጎዳናው ዘለሰው። አውሬ የነጨው ነጭ መንጋ እየመሰለ በየዱር ሆዱን ገልብጦ ወደቀና የአሞራ ቀለብ ሆነ።
መጋቢት ፲፭ ቀን ፪ ሺህ ፱ ዓ. ም.
በወለላዬና በዶክተር ተድላ ሀሳብ ላይ ተጨማሪ፥ በቅድሚያ ክብር በደምና በአጥንታቸው አንድነት ሀገር ላቆዩልን ለአድዋው ጀግኖች በሙሉ፥ ወለላዬ በስዊድን የመቶ ሃያ አንደኛው ዓመት የአድዋን ድል መዘክርና በዝግጅቱ ላይ የነበሩትን ክስተቶች ስላሳወቁን ብቻ ሳይሆን ምላሽ በመስጠትዎና ለሚመለከተውም ጥሪ በማድረግዎ ምስጋናችን የላቀ ነው። በእኛም በኩል የመቶ ሃያ አንደኛው ዓመት የአድዋን ድል በመጣጥፎች ለመዘከር ዝግጅት በምናደረግበት ጊዜ አንዳንዶቻችን የእቴጌ ጣይቱን ታላቅ አስተዋጽዖ ለብቻው ማዘጋጀት ጀምረን፥ ነጥለን የምናወጣው ታሪክ ጎደሎ ሆኖ ስላገኘነው አድዋን ከመላው ጀግኖቹ ጋር መተረኩ የተሟላ ሆኖ አግኝተነዋል። /ሙሉውን ጽሁፍ ይህንን በመንካት ያንብቡ/