“….. ኃይሌ የግል ህይወቱን በሚመለከት ደግ ነው፣ ጥሩ የቤተሰብ ሰው ነው፣ ቤተሰቡን የሚያከብር፤ ከዛም ውጪ ልጆቹንም የሚንከባከብ፤ ከዛም አልፎ ደግሞ ማንኛውንም ኢትዮጵያዊ …. በኢትዮጵያዊነቱ በመርዳርት የሚያምን ሰው ነው።”
ወ/ሮ እስከዳር አውላቸው 121ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በአል ዳላስ ውስጥ ሲከበር ከተናገሩት የተወሰደ
121ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል ባሳለፍነው ሳምንት በዳላስና ፎርትወርዝ የኢትዮጵያውያ ጉዳዮች የውይይት መድረክ ፎረም አዘጋጅቶ ፕ/ር ኃይሌ ላሬቦን በክብር እንግድነት ከተጋበዙት አንዱ መሆናቸው የሚታወስ ነው። በእለቱ ከባሌቤታቸው ጋር እንዲመጡ የተጋበዙት የፕ/ር ኃይሌ ላሬቦ ባለቤት ወ/ሮ እስከዳር አውላቸው በስፍራው ተገኝተው ዝግጅቱን ያዘጋጀው ፎረም በማመስገን በኢትዮጵያ ጉዳዮች በተለያየ ወቅት የግል አስተያየታቸውና ጥናታዊ ፅሁፋቸውን በሚያበረክቱት ባለቤታቸው ከሚደርሰው ዛቻና ማስፈራሪያ በተጨማሪ በመላው ቤተሰቡ የሚደርሰው ጫና ለታዳሚው አስረድተዋል። ይህ ተግባር ቀድማም የነበረ ቢሆንም በቅርቡ በኢሳትና በሌሎች ኢትዮጵያ ነክ በሆኑ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት አስተያየት ያልተደሰቱ ግለሰቦችና ቡድኖች በተደራጀ መልኩ በመላው ቤተሰብ ጫዋነት የጎደለው ድርጊት በመፈፀም ከፍተኛ ጫና ሲፈጥሩባቸው እንደነበር ገልፀዋል። በዚህ ሁሉ አስከፊ ወቅት ከባለቤታቸውና ከመላው ቤተሰብ ጎን መቆም አስፈላጊውን ሁሉ ሲያደርጉ የነበሩትን አመስግነዋል።