ተመስገንን ሳየው /‎ታሪኩ ደሳለኝ/

ተመስገንን ሳየው /‎ታሪኩ ደሳለኝ/

መንግስት ካሳራው እስር ቤት ተመሰገን የለም ከለበት ግዜ አንስቶ ላሉት 5 ወራት ተመስገንን እንዳላየው ተከልክዬለው። በከለከልም ግን ዝዋይ እስር ቤት ሄጄ እደጁን አይቼው ከመመለስ አልተገደብኩም። እነሱም እኔን ከመመለስ አልተገደቡም። እንደ ልማዴ ዛሬም እስኪ ደግሞ ካሳዩኝ ላየው ካላሳዩኝ አጥሩን አይቼ እመለሳለሁ ብዬ ከቤቴ ስነሳ እንደወትሯዋ አናቴ የያዝኩትን የቋጠረችውን ስንቅ እየተመለከተች “ዛሬ ሚካኤል ነው እሱ የየካው ቅዱስ ሚካኤል ይከተልክ” አለችኝ “አሜን ብዬ” ምራቃቷን ይዤ ዝዋይ እስር ቤት እደጅ ተገነኘው።

ወደ በሩ ተጠጋው የቆሙት ወታደሮች አየኙ ከነዚህ ወታደሮች ጋር ባንነጋገርም ባይን እንተዋወቃለን በዙም ግዜም “ታሪኩ” አንተ መጠየቅ ተከልክለካል ብለው እደጁን እንዳላልፈወ አደርገውኛል። ዛሬ እያዩኝ ዝም አሉኝ እኔም እያየዋቸው ቆሜ ዝም አልኩኘ። አንደኛው ወታደር የታጠቀውን ጠብ-መንጃ ዝቅ አድርጉ መንገዱን ወደ ቀኝ ለቀቀለኝ። አላመንኩም ቀስ እያልኩ ወደ ፊት ሁለት እርመጃ ተራመድኩ ቆም አልኩ ስሜ አልተጠራም ሦስት አራት አምስት እርመጃ ተራመድኩ አላስቆሙኝም እርምጃዬ ሳላቆም አንግቴን አዙሬ ተመለከትኳቸው ጠብ-መንጃ ዝቅ አድርጉ የሳለፈኝ ወታደር ፈግግ ብሎ አየኝ እኔም ፈግግ እላለሁ ብዬ ሳኩኝ አንዴት አልስቅም!።

አድራሻዬን የማፅፍበት ቦታ ደረስኩ መታወቂያዬን አወጣሁ ወታደሮቹ “እንዴት ነህ ታሪኩ” አሉኝ “እንዴት ናቹ” አልኩኝ። መታወቂዬን እሰከማወጣ ሰሜን አድራሻዬን ፅፈው እየገበድ ነበር። የያስኩትን ስንቅ አስፈተሽኩ አንጀራውን አስር ቦታ ዘረጉት አጠፉት ቆራረጡት የተለመደ ነው፣ ወጡን በጭልፋ አገላበጡት አማሰሉት (ይሄ ወጥ ሲቁላላ እራሱ እንደዚህ የተማሰለ አይመስል) ይህም የተለመደ ነው፣ ተራው የገብስ ዳቦዎች ሆነ ደቦውን ሲቁራርሱት ገብሱ የሚወጣ ነው የሚመስለው ቢሆንም ይህም የተለመደ ነው፣ ወደ አፕልሎቹ ዙሩ “ግመጠው” አሉኝ አንዱን ገመጥኩ ሌሎቹን በሹካ ቦዳዳሷቸው ይህንንም ለመደነዋል፣ የቆሎው ተራ ደረሰ ትሪላይ አበጠሩት አንቀረቀቡት ይህም የተለመደ ነው።

እኔ ከአሀን አሁን ተመለስ ይላሉ ብዬ እየጠበኩ ያዝኩት ስንቅ ተፈትሾ አለቀ። አሁን የኔ ተራ ነው። ከውስጥ እግሬ እስከ ፀጉሬ ተፈተሽኩ ተበረበርኩ ደጋሚ ተፈትሽኩ። ይህ ሁሉ ቆሞ ሲቆጣጠር የነበረ የወታደር መኮንን “ገባ” አለኝ ለማረጋገጥ “ምን” አልኩኝ “ግባ” ደገመለኝ። እግሮቼ ስር የነበሩትን ስንቆች እፍስ ፍስ አድርጊ በሩጫ የታገዘ እርመጃ ተራምጄ ሀለተኛው ፍተሻ ገቢ ገባሁ። ተመስገን ያለበት ቦታ በልዩ ጥበቃ ስር ስለሆነ ድጋሚ ፍተሻ አለ። ከመጀመሪያው የባሳ ፍተሻ መደረጉን የሚገልፀው እንጀራውም ዳቦም ለፍርፈር የተዘጋጀ መምሰላቸው ነው። ይህን ፍተሻ አልፌ ተሜን የማገኝበት ቦታ ስደርስ አንድ ታሰሬ እየተጠየቁ አገኘዋቸው። ሳያቸው ፈገግ አልኩኝ። እኚህ ሰው ጄኔራል አሳምነው ናቸው። ተነስተው ስለም አሉኝ በአክብሮት ሰላምታቸውን መለስኩኝ።

ተሜ እስኪመጣ። አይኔን ከጄኔራል አሳምነው ሳላነሳ ቆየሁ። ከፊት ለፊታችን ከላው የበረት ግቢ ውስጥ አንድ ወታደር ከፊት አንድ ወታደር ከኃላ ሆኑ ተሜን ሲመጣ አየሁት ከተቀመጥኩበት ተነሳው ለአምስት ወራት አለየሁትም ወንድሜን አየሁት! በካኪው ሸሜዝ ላይ እስካርቡን አድርጉል ከፊቱ ወታደሩ ቢኖረም ለኔ ተሜ ነው የሚታየኝ እየቀረበኝ መጣ እኔ ሆድ ባሰኝ አይኔ አንባ አቀረረ ተሜ አጠገቤ ደረሰ ተቃቅፈን ሰለም ተባባለን። አየተያየን ቁጭ አለን። “ማዘር እንዴት ነች” አለኝ “ደና ነች” አልኩኝ። እሱ ጠየቀኝ እኔ ተጠየኩ። በቃ ማውራት አልቻልኩ አይን አይኑን እያየው የተፈቀደለን ሰዓት አለቀ። ከስርቤቱ በድስታ ወጣሁ።

ለናቴ ደወልኩላት “እማዬ ገባው አገኘውት” አልኳት እናቴ በሚርበተበት ደምፅ “ደና ነው ወይ” አለችኝ “ደና ነው” አልኩ ዝም አለቸኝ በስልኩ ውስጥ እናቴ ስታለቅስ ሰማሁ “ምንድን ነው” አልኳት”ደስ ብሎኝ ነው የኔ ሚካኤል አያሰፈረኝም” አለችኝ። እውነቷን ነው አልኩ። የተከለከልኩበትን ምክኒያት ሳለቅ ከአምስት ወር በኃለ ወዱን ወንድሜ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን አይቼው ተመለስኩ።
ሚያዛያ 12/09ዓ.ም

LEAVE A REPLY