/Ethiopia Nege News/:- አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ አሜሪካዊያን ዜጎች ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም የቱሪስት መዳረሻ አካባቢዎች ስለሚያደርጉት የጉዞ መመሪያ ዛሬ አውጥቷል።
ኤምባሲው ዛሬ ባወጣው የጉዞ ማስጠንቀቂ መግለጫ ላይ የአሜሪካ ዜጎች ኢትዮጵያ ውስጥ የቱሪስት መዳረሻ ወደ ሆኑ አካባቢዎች ጉዞ እንዳያደርጉ አሳስቧል። የጉዞ መግለጫው እንደምክኒያት ካስቀመጣቸው ምክንያቶች መካከል፤ ጥንታዊት እና ከፍተኛ የቱሪስት መዳረሻ በሆነችው ጎንደር ከተማ በአንድ ወር ብቻ 4 ጊዜ ሆቴሎችንና የግለሰቦች መኖሪያ ቤትን ያነጣጠረ የቦንብ ጥቃት መፈፀሙን ተከትሎ መሆኑን መግለጫው ጠቅሷል።
በአለፈው ዓመት የተካሔደው ፀረ መንግስ ተቃውሞ በተለይ በጎንደር እና አካባቢው የተቀሰቀሰው ተቃውሞ እስካሁን ያልበረደ ከመሆኑም ባሻገር መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማወጅ የጎንደሩ ህዝባዊ ተቃውሞ ዋነኛ ተጠቃሽ እንደነበር ይታወቃል።
አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ “የአሜሪካ ዜጎች” ወደ ጎንደንደር የሚያደርጉት ጉዞ ጥንቃቄ የተሞላበት እንዲሆንና አስገዳጅ ካልሆነ በስተቀር ወደ አካባቢው ጉዞ እንዳያደርጉ አሳስቧል።
የኢትዮጵያ መንግስት መግለጫውን ተከትሎ እስካሁን ያለው ነገር እንደሌለ ተጠቅሷል።