ባህር ዳር ባለገሩ የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ የቦንብ ፍንዳታ ተከሰተ

ባህር ዳር ባለገሩ የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ የቦንብ ፍንዳታ ተከሰተ

/Ethiopia Nege News/:- ዳሽን ቢራ ስሙን ወደ “ባላገሩ” መቀየሩን ተከትሎ የሙዚቃ ኮንሰርት በባህር ዳር ከተማ የተዘጋጀ ቢሆንም የሙዚቃ ዝግጁቱ ከመጀመሩ ጥቂት ደቂቃዎች ዘግይቶ በቦንብ ፍንዳታ በተኩስ እንደተናወጠ ከቦታው የነበሩ እማኞች አስረድተዋል።

” ክብር ለባላገሩ” በሚል መሪ ቃል በዳሽን ቢራ ድርጅት ስፖንሰርነት የሙዚቃ ኮንሰርት እንደሚዘጋጅ ከታወቀ ወዲህ የባህር ዳርና አካባቢው ወጣቶች የመንድሞቻችን ደም ሳይደርቅ ኮንሰርት ፈፅሞ ሊደረግ አይችልም በማለት በሶሻል ሚዲያ በኩል ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል። በኮንሰርቱ ላይ ሙሐሙድ አህመድ፤ ኩኩ ሰብስቤና አረጋኸኝ ወራሽ እንደሚሳተፉ ሲገለፅ የቆየ ቢሆንም ቦታው ላይ የተገኙት ኩኩና አረጋኸኝ መሆናቸው ታውቋል።

የተፈጠረውን የቦንብ ፍንዳታ ተከትሎ የመከላከያና ፌደራል ፖሊስ በአካባቢው የተገኘውን ወጣት በማሰር ላይ መሆናቸውን የአይን ምስክሮቻችን ጨምረው ገልፀዋል።

በጥረት ኢንዶውመንት ስር የሚተዳደረው ዳሸን ቢራ ፋብሪካ ለአማራ ህዝብ ሳይሆን በእጅ አዙር የህወሓት ንብረት ነው በማለት ህዝቡ ምርቱን ባለመጠቀሙ “ድርጅቱ” ከፍተኛ ኪሳራ ውስጥ መሆኑ የሚታወቅ ነው።

 /Ethiopia Nege April 27, 2017/

LEAVE A REPLY